ከእለታት አንድ ቀን በደንብ የማላውቀው
አንድ ሰው መጣና አለኝ ስምህ ማነው
በዚህ ሰው ጥያቄ ግራ በመጋባት
ስሜን ለምን ማወቅ አስፈለገህ አልኩት
የመለስኩለት መልስ ስላስደነገጠው
መልሴን እንደሰማ ፈገግ ብሎ እያየኝ
ይቅርታ አድርግልኝ አጥፍቻለሁ አለኝ
ከዚያም በመቀጠል ዘርግቶ ቀኝ እጁን
አለ እንተዋወቅ ነግሮኝ ማንነቱን
እጁን ጨበጥኩና ስገልጽለት ስሜን
ትኩር ብሎ እያየኝ ለቀቅ አርጎት እጄን
ስምህን ስሰማ የማውቅህ መሠለኝ
በመልክ ደግሞ ሳይህ ጥርጣሬ ገባኝ
ያንተ ስም በፍጹም ለእኔ እንግዳ አይደለም
ግን በእርግጠኝነት የት እንደሰማሁት መናገር አልችልም
ይህን ብሎ ወዲያው አይን አይኔን እያየ መልሴን ሲጠባበቅ
ምንም ሰፈራችን አንድ እንደሆነም ባውቅ
ጭራሽ አይመስለኝም ከዛሬ ቀን በፊት የምንተዋወቅ
ብዬ ተናግሬ ሳልጨርስ ሃሳቤን
ቀበል አረገና ቀጠለ ማውራቱን
በጣም ያስገርማል የእኔና አንተ ነገር
ለረዠም ዘመናት ስንኖር አንድ ሰፈር
ሰላምታ ሳይኖረን ሳንጫወት አብረን
ዛሬ ባጋጣሚ በድንገት ተዋወቅን
የቅርብ ጓደኛ ወይ ዘመድ የሚባል
እዚህ ስለሌለኝ ብቸኛ መሆኑ በጣም ሰልችቶኛል
ስለዚህ እባክህ ያለፈውን ትተን
እየተመጸከርን የእረፍት ጊዜያችንን
አብረን በመጫወት ማሳለፍ አለብን
እያለ ሲያግባባኝ ጓደኛ እንድሆነው
ተወኝ አልፈልግም ሰልችቶኛል ስለው
ብሎ መለሰልኝ እባክህ ሞኝ አትሁን መጫወት ጥሩ ነው
ብቸኛ መሆኑ ብዙ መዘዝ አለው
የሰው ልጅ ያለ ሰው ጭራሸ ዋጋም የለው
ምንም አይጎዳህም የኔ ጓደኝነት እባክህ ሞክረው
እያለ መላልሶ ስለወተወተኝ
እሽ ልሞክረው ብዬ ተስማማሁኝ
እንዲህ ተጀምሮ ጓደኝነታችን
ብዙ ጊዜ ሳንቆይ መስማማት አቃተን
ጨዋታ ስንጀምር ይለኛል አፍ አፌን
እኔን ብቻ ስማኝ አድርግ የምልህን
እንዳትጠይቀኝ ብለህ እንዴት ለምን
እያለ ደጋግሞ ሲገልጽ ፍላጎቱን
በደንብ ተረዳሁት የውስጥ ስሜቱን
ድብቅ ስብዕናውን የእውነት ማንነቱን
እንዲሁም አስተዋልኩ በመጸከላችን እንዳለ ልዩነት
ጨርሶ እንደማያምን በእኔ ጓደኝነት
ለይስሙላ ብቻ መስሎ ለመታየት
እንደሚሽቀዳደም ወዳጅ ነኝ ለማለት
ትውውቅ ስናደርግ የተባባልነውን
ተሳስበን ተፋቅረን እንኑር ተከባብረን
ብለን ሁለታችን የተስማማነውን
ይህን የጋራ አቋም በመተው ወደ ጎን
ሌላ ሃሳብ አመጣ እኔ ያልጠበቅሁትን
ከልምድ አንፃር ሳየው እኩል ስላይደለን
አንተ ተከተለኝ እኔ መሪ ልሁን
በማለት እቅጩን ነግሮኝ ያሰበውን
ፋታ እንኳን ሳይሰጠኝ ለመግለጽ ሃሳቤን
አመለጸከቱን በእኔ ላይ ሲጭነው
አዲስ ሰው ሆነብኝ ጭራሽ የማላውቀው
በዚህ አይነት መንገድ ቶሎ ተረሳና ጓደኝነታችን
ህጉንና ደንቡን ስቶ ጫዋታችን
እንፋጠጥ ጀመር መቻቻል አቅቶን
እስክናምን ድረስ በስሜት ተገፍተን
አንድ ጋ አብረን መኖር አንችልም ብለን
ቁርጥ አቋም በመያዝ ወስነን ተነስተን
አንዱ አንዱን ለማጥፋት እንሯሯጣለን
በዚህም ድርጊታችን ከፍተኛ ጉዳት እናስከትላለን
በሁለቱም ወገን ቶሎ የማይጠፋ ጠባሳ እንተዋለን
የእኛ አልበቃ ብሎ ሌሎችንም ሰላም እንነሳቸዋለን