የሆዴ በሽታ (መጋቢት 1996)

ችግሬን ማን አየው የውስጥ በሽታዬን

እኔ ሆዴን አሞኝ አከሙኝ ራሴን

ሳይታወቅልኝ ዋናው በሽታዬ

ይኸው እንዲሁ አለሁ ጠንቶብኝ ስቃዬ

በይሆናል ብቻ መድሃኒት ሲሰጡኝ

እንኳንስ ሊሻለኝ የበለጠ አመመኝ

ተስፋ ባለመቁረጥ ቀርቤ እንደገና

ምንም አልተሻለኝ በሽታዬ ጠና

ፋይዳ ቢስ ሆነብኝ የናንት ህክምና

የሚያመኝ ሆዴን ነው እባጸችሁ እርዱኝ

በውስጡ የያዝኩት ነገር እየበላኝ

ብችለው ብችለው ይበልጥ ባሰብኝ

እያደር ጠንክሮ በጣም አቃጠለኝ

አውጡና ጣሉልኝ ሰላም እንዲሰጠኝ

ብዬ አስተዛዝኜ ልመናዬን ባቀርብ

ብለው መለሱልኝ አይተንሃል በደንብ

ሆድህ ጤኘኛ ነው በሽታ አያውቀውም

የስቃይህ መንስዔ ፍፁም ሌላ አይደለም

እንሰጥሃለን መድሃኒት ቀይረን

የራስህን ህመም በቶሎ የሚያድን

ብለው እንደገና መድሃኒት ሲሰጡኝ

ምንም ሳላጓድል ሁሉንም ወሰድኩኝ

የታዘዘልኝን መድሃኒት ስጨርስ

የሆዴ በሽታ ስቃዬ ሳይቀንስ

ድሮ ያልነበረ ጭራሽ የማላውቀው

ከባድ የራስ ምታት ራሴን ፈለጠው

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *