Tag: long

  • እህቴ (ታህሳስ 1999)

    ከቼርች እንደመጣሁ እሁድ ቀን ከስአት

    ከጓደኞቼ ጋር በጭቃ ስጫወት

    ጥሩ ቤት ሰርቼ እህቴን ባስቀናት

    እንደ እኔ ቆንጆ ቤት መሥራት ስለአቃታት

    በጣም ተበሳጭታ ምንም ሳላስበው

    ያን የመሰለ ቤት በእግሯ አፈረሰችው

    እኔም ተናድጄ በእሷ መጥፎ ድርጊት

    ተንደርድሬ ስሄድ በዱላ ልመታት

    አባቴ ስለአየኝ አለኝ እንዳትነጸት

    ምክሩን ተቀብዬ ስመለስ በፍጥነት

    እሷን ጠራትና እንዲህ ሲል መከራት

    በጣም ያሳፍራል ያጠፋሽው ጥፋት

    የሱን ቤት ማፍረስሽ ተነስተሽ በቅናት

    ከአንች አይጠበቅም የዚህ አይነት ድርጊት

    አሁንም ቶሎ በይ ይቅርታ ጠይቂው

    የዚህ አይነት ጥፋት አይለምደኝም በይው

    በመጸከላችሁ ሰላም የሚወርደው

    ጥፋተኛነትሽን ስተቀበይ ነው

  • ማንንም አይፈራ (የካቲት 2000)

    የካቲት 25 ቀን 2000 ዓ.ም

    ከ ጌዲዮን በላይ

    የኤድስ በሽታ ምህረት የማያውቀው

    ወጣቱን በሙሉ ይኸዉ ጨፈጨፈው

    ይህ የወገን እልቂት ሲከሰት እያየን

    ከቶ ለምንድ ነው መጠንቀቅ ያቃተን ?

    እኛን አይነጸንም በሚል አጉል ምክንያት

    ይኸዉ ልናልቅ ነው ጎልማሳና ወጣት

    የኤድስ በሽታ ምህረት የማያውቀው

    ወጣቱን በሙሉ ይኸዉ ጨፈጨፈው

    ምንም ጊዜ ሳንሰጥ ከዛሬ ጀምረን

    የዚህን በሽታ ስርጭት ጸልገታን

    የሰው ልጆች ሁሉ ከምድር እንጠፋለን

    የኤድስ በሽታ ምህረት የማያውቀው

    ወጣቱን በሙሉ ይኸዉ ጨፈጨፈው

    የአገሬ ወጣቶች እባጸችሁ ስሙኝ

    መድሀኒት የለውም ይህ የኤድስ ወረርሽኝ

    ወይም መርጦ አይደለም ሰዎችን የሚያገኝ

    ኑሮአችን ጨልሞ መላ ቅጥ ጠፍቶብን

    ሀዘን መከራና ስቃይ እንዳይጎዳን

    የአሁን ድርጊታችን ኋላ እንዳይፀፅተን

    ከበሽታው መንስኤዎች መራቅ ነው ያለብን

    የኤድስ በሽታ ምህረት የማያውቀው

    ወጣቱን በሙሉ ይኸዉ ጨፈጨፈው

  • ዳዊት (ሐምሌ 1997)

    ያ ዳዊት መንግስቱ የጅጅጋው ወጣት

    ፍቅር አይነጸኝም ብሎ ባወራበት

    በዚያው በምላሱ ሴት ሲለምንበት

    በጣም ያስደስታል ሲያለቅስ መመልከት

    የተናገረውን ጭራሹን ረስቶት

    ህይወቱን ከሴት ጋር ይኸው አቆራኝቶት

    ብሞት ይሻለኛል ሰላምን ከማጣት

    እያለ ያወራል ያለምንም ሀፍረት

    ቋንቋው ተቀይሮ ሰላም ብቻ ሆኗል

    ዘመድ መጠየቁን ጭራሹን አቁሟል

    በስልክ እንዳይገኝ ስልኩ እየደወለ ዝም ብሎ ያየዋል

    እሷ ስትደውል ቶኑን ይለየዋል

    ሮጦ ተነስቶ ቶሎ ያነሳዋል

    የእሷን ድምጽ መስማት ደስታ ይሰጠዋል

    ቶሎ ነይ እኔ ጋ እያለ ደጋግሞ ግብዣውን ያቀርባል

    እንዲያው በአጠቃላይ እጁን ለእሷ ሰጥቷል

    ይህ አዲስ ፀባዩ ማንም የማያውቀው

    ወዳጅ ዘመዶቹን ምንም ቢገርማቸው

    ለእሱ የጠበቀ ፍቅር ስላላቸው

    ይለምኑለታል ፈጣሪን ደጋግመው

    ሁለቱን ፍቅረኞች እንዲባርጸቸው

    በትዳር ሰንሰለት እንዲያቆራኛቸው

    ሁሉም የሚያውቀው ሰው ለእሱ የሚመኝለት

    ልቡን የሰወረው ይህ የፍቅር ህይወት

    በደንብ የሚያረጸው ደስታ የሚያስገኝለት

    ምንም አይነት ችግር የማያመጣበት

    ፍላጎቱ ሁሉ የሚፈፀምበት

    ወልዶ የሚስምበት ሰላም የሞላበት

    እንዲሆንለት ነው ጥሩ የሚባል ህይወት

    ከ ወ/ሮ ሜላት መንግስቱ እና ከ ፕ/ር በላይ ጸሣ

  • ስምንተኛው ሺህ (ጥቅምት 2001)

    አብዛኛው እድሜዬን ኑሮን እየታገልኩ

    ማሸነፍ ባልችልም ተስፋ ስላልቆረጥኩ

    በደመ ነፍስ ብቻ እየተፍጨረጨርኩ

    ብዙ መከራና ስቃይ ስለአሳለፍኩ

    ኑሮዬን እንደ አዲስ ልጀምር ስለአሰብኩ

    ቀደም ባለው ጊዜ አለሁ ባይ አጥቼ

    የደረሰብኝን የሆንኩትን ሁሉ ወደ ኋላ ትቼ

    በሰዎች ላይ ላልደርስ ምዬ ተገዝቼ

    ስሜቴን አፍኜ አንገቴን ደፍቼ

    ጠብና ትንኮሳን ከሩቅ እየሸሸሁ

    ነገሮችን ሁሉ በጥሞና እያየሁ

    በጣም ተጠንቅቄ ስመራ ህይወቴን

    በደንብ ያልተረዱት ድርጊቴና ሀሳቤን

    ሰዎችን የምንቅ ኩራት የወጠረኝ

    አልያም አውቆ አበድ አድርገው ቆጥረውኝ

    ምክንያት ፈልገው ስሜቴን ሲጎዱት

    ትግዕስቴን ደጋግመው በጣም ሲፈትኑት

    ወይም ስሜን አውቀው በከንቱ ሲያጠፉት

    ለእኩይ ድርጊታቸው አፀፋ ከመስጠት

    የፈለገው ይምጣ በሚል አይነት ስሜት

    በንቀት እያየሁ ዝም ብዬ ሳልፋቸው

    ክንፍ የሌለው እርግብ መብረር የተሳነው

    አድርገው ቆጥረውኝ መሄጃ የሌለው

    ተዉ ባይ በሌለበት እስኪያንገሸግሸኝ

    በበደል ላይ በደል ሲደራርቡብኝ

    ለማን አቤት ብዬ ሰላም እንደማገኝ

    ወይስ ምን ብሠራ እንደሚራሩልኝ

    አውጥቼና አውርጄ መፍትሔ ሲጠፋብኝ

    እንዲህ ከምሰቃይ ምነው ባልፈጠርከኝ

    ብዬ በማማረር ፈጣሪን ወቀስኩኝ

    ከዚያም ብስጭቴ በረድ ሲልልኝ

    እግዜርን መውቀሴ አውቆ እንደበደለኝ

    ጥቅም እንደሌለው ስለተረዳሁኝ

    ከሁሉም በላይ ግን ጥሎ የማይጥለኝ

    ኃያሉ ፈጣሪ አብሮኝ አጠገቤ መኖሩ ተሰምቶኝ

    ምንም ባስቀይመው ልጁ ስለሆንኩኝ

    ይቅር እንደሚለኝ ሙሉ እምነት አድሮብኝ

    ይህን መከራየን አንተው አቅልልኝ

    በማለት መልሼ በጣም ተማፅኘው

    ቀሪ ህይወቴንም እሱ እንዲባርከው

    በተደጋጋሚ ሳልሰለች ለምኜው

    በጣም ስረጋጋ ሁሉን ለእሱ ትቼው

    የእኔ ሰላም ማግኜት ያላስደሰታቸው

    ያደረጉት ሁሉ አልበቃ ብሏቸው

    በህይወት መኖሬ ቁጭት ፈጥሮባቸው

    ከምድር ገጽ ላይ እንድጠፋላቸው

    እጅግ ሲጨነቁ ሲደክሙ ሳያቸው

    የሰው ልጅ ጭካኔ ወሰን እንደሌለው

    በህይወት ዘመኔ በእኔ የደረሰው

    ትምህርት ሰጥቶኛል ሁል ግዜ የማረሳው

    በዚህ የተነሳ በጥሞና ሳየው

    የዚህ አይነት ኑሮ ውሸት የበዛበት

    ክፋትና ተንኮል ስር የሰደዱበት

    ሰው እርስ በእራሱ የሚጫረስበት

    ትርጉም ስለሌለው ለሰው ልጆች ህይወት

    እስከዘላለሙ ሀጢያት የሚባለው ከስሞ የሚጠፋበት

    ያ ስምንተኛው ሺህ የአለማችን ህልፈት

    እንዲሆን ፀለይኩኝ አሁን ከመቅፅበት

  • ህያው መልዕክት (ነሐሴ 2000)

    ያ ትልቁ ነብይ እየሱስ ክርስቶስ

    መስቀል ላይ እያለ ስቅስቅ ብሎ ሲያለቅስ

    ሊማፀን አይደለም ፍጻሜው እንዳይደርስ

    መፈፀም ያለበት መሆን የሚገባው

    ማንም ሊለውጠው አልያም ሊያስቀረው

    እንደማይቻለው ቀድሞ ስለአወቀው

    እጣውን በፀጋ ነው የተቀበለው

    ህይወቱ ለህልፈት በተዳረገባት

    በመጨረሻዋ በዚያች ወሳኝ ሰአት

    ለአዳም ዘር ሁሉ ነው ያደረገው ፀሎት

    የሰው ልጆች ሁሉ ሀጢያት አስክሮአቸው

    በስሜት ተገፍተው ማሰብ ተስኖአቸው

    የሚያደርጉት ሁሉ ግራ እያጋባቸው

    ይይዝ ይጨብጡት ስለጠፋባቸው

    እባክህ አባቴ አንተ ይቅር በላቸው

    ብሎ በንፁህ ልብ በጣም አዝኖላቸው

    ታላቁ ፈጣሪ ሁሌ እንዲያስባቸው

    መልሶ መላልሶ ፀሎት አርጎላቸው

    ከዚያም አልፎ ተርፎ ዘመን የማይሽረው

    እውነተኛ ፍቅሩን በእንባው ገልፆላቸው

    ለእናንተ ብዬ ነው እንዲህ የማነባው

    ይኸው ተፈፀመ የሚል ህያው መልዕክት ጥሎ ነው የሄደው

  • ማልቀስ እንደ ወንጀል (ነሐሴ 2000)

    በስልሳዎቹና ሰባዎቹ አመታት

    ልጃቸውን ገለው የመንግስት አካላት

    ሀዘን ቁጭ ብላችሁ እንዳንመለከት

    ወይም ስታለቅሱ አንፈልግም ማየት

    እያሉ በድፍረት ለቅርብ ዘመዶች ለእናትና ለአባት

    ሀይለ ቃል ያዘለ ማስጠንቀቂያ መስጠት

    ከዚያም አልፎ ተርፎ ያለምንም ሀፍረት

    የጥይቱን ዋጋ እንድትከፍሉ ማለት

    በጽሁፍ የሌለ አንቀጽ ያልወጣለት

    ነገር ግን ሰው ሁሉ አንድ ቀን በሂደት

    እንደማይቀርለት አውቆ በተጠንቀቅ መጠበቅ ያለበት

    ይግባኝ የሌለበት ፍርድ ሆኖ ነበር ለጥቂት አመታት

    ያብራካቸው ክፋይ ወልደው ያሳደጉት

    ውድ ልጃቸውን ያለፍርድ ገድለውት

    አታልቅሱ የሚል ቀጭን ትዕዛዝ መስጠት

    አረመኔነት ነው ርህራሄ ማጣት

    ሀዘንና ለቅሶን የከለከሉበት ትልቁ ምክንያት

    የሌሎች ወላጆች ከዚህ ቀስምው ትምህርት

    ልጆቻቸው ሁሉ እንዳይሰለፍ በተቃዋሚነት

    እንዲያገለግል ነው በማስፈራሪያነት

    በፍጹም ጭካኔ ማን አለብኝነት

    ሆን ብሎ የሟቹን ወላጀች ለመጉዳት

    የልጃቸውን ሞት ፈጽሞ እንዳይረሱት

    ባስታወሱት ቁጥር እንዲሆንባቸው የዘለአለም ፀፀት

    ፋታ እንዲያሳጣቸው ልክ እንደ እግር እሳት

    የማድረግ እርምጃ ኢሰብአዊ ድርጊት

    በታሪክ ያልታየ ተው ባይ የጠፋበት

    ያለምንም ገደብ ህግ የሚጣስበት

    መረን የለቀቀ ስርአተ አልበኝነት

    ተንሰራፍቶ ነበር በሀገራችን ውስጥ በሁሉም ማዕዘናት

  • ደስታ ወይስ ሀዘን (ነሐሴ 2000)

    የሰው ልጅ ስሜቱን የሚገልጽባቸው

    ድርጊቶች ልዩና በጣም ብዙ ናቸው

    ሀዘንን በለቅሶ ደስታን ደግሞ በሳቅ

    ምንም ብዙ ጊዜ እንደሚገልጽ ብናውቅ

    አልፎአልፎ ይታያል ፍጹም ሳይጠበቅ

    እኒህ ስሜቶቹ ሲሉበት ድብልቅልቅ

    አንዳንዴ በድንገት ምክንያቱን ሳናውቅ

    እናገኘዋለን በደስታ ተሞልቶ በጣም ሲንሰቀሰቅ

    ወይም ከልብ አዝኖ ከት ብሎ ሲስቅ

    በደንብ አስተውለን በጥልቀት ካየነው

    ደስታ የሀዘን ምንጭ ሊሆን የሚችለው

    ከባድ ድንጋጤ ሲጨመርበት ነው

    የሰው ልጅ ለእራሱ በጣም የሚመኘው

    በአንፃሩ ግን ደግሞ ደጋግሞ ሲያስበው

    ፈጽሞ ይሆናል ብሎ የማይገምተው

    አይሳካም ብሎ ቀልቡ የነገረው

    እየቆየም ሲሄድ ተስፋ ያሰቆረጠው

    በህይወቱ ውስጥ ግን ትልቅ ቦታ ያለው

    በጉጉት ውጤቱን የሚጠባበቀው

    አንድ ብርቱ ድርጊት ወሳኝ ነው የሚለው

    ድንገት ሲሰምርለት ምንም ሳያስበው

    መሆን የለበትም ያለ እስኪያስመስለው

    ድንግጥ ሲል ይታያል ግራ ግብት ሲለው

    ሰው የሚለውና እሱም በአይኑ ያየው

    እውነት አልመስል ብሎት እያጠራጠረው

    አምኖ ለመቀበል ሲለሚቸግረው

    ፍጹም ያልጠበቀው ጥሩ እድል ሲገጥመው

    በደስታ ተሞልቶ መፈንደቅ ሲገባው

    ተመልካችን ሁሉ ግራ እስከሚገባው

    ስቅስቅ ብሎ አልቅሶ ፊቱን ያጥባል በእንባው

  • ፍቅር እንደ ሀጢያት (ነሐሴ 2000)

    የሰውን አዕምሮ ይከብዳል መረዳት

    ቀልቤ አንተ ላይ አርፏል አፈቀርኩህ ሲሉት

    ይህ ለምን ይሆናል በሚል አይነት ስሜት

    መታበይ ያበዛል መወጠር በኩራት

    ሀሳቡን ከመግለጥ ምላሹን ከመስጠት

    አፈቀርኩህ ባይዋን ያዋረዳት መስሎት

    እገሊት ከእኔ ጋር ፍቅር ስለያዛት

    ወደድኩህ አለችኝ ያለምንም ሀፍረት

    ምን አይነት ዘመን ነው ይህ የምንኖርበት

    ወንዱ አንገቱን ደፍቶ ስርዓት በያዘበት

    ሴቷ በአንተ ፍቅር ተይዠ ከምሞት

    አለሁ በለኝ እና ሰላም ላግኝበት

    ብላ ያለማፈር የምትለምንበት

    እያለ ያወራል ጆሮ ለሚሰጠው በየደረሰበት

    ከልብ የምትወድ የፍቅር ሰው ማግኜት

    በጣም ከባድና ፈተና የበዛበት

    መሆኑን መረዳት በፍጹም ተስኖት

    ማፍቀሯን በገሀድ የገለጸችለት

    ጭራሽ የማትረባ ሰው አርጎ ፈርጇት

    ለእኔ ትሆናለች ብሎ የሚመርጣት

    የሚወዳትን ሰው ፈልጎ ለማግኘት

    በእሱ ከደረሰው ሰዎች ቀስመው ትምህርት

    ኑሮአቸው እንዲሆን ደስታ የሞላበት

    ምክሩን

  • የፍቅር ረመጥ (ነሐሴ 2000)

    ምንም ሳያስበው አንድ ቀን በድንገት

    ቀልቡን የምትስብ ድንግጥ የሚልላት

    በአጠገቡ ብታልፍ መልከመልካም ወጣት

    በአይኑ ይሸኛታል በልቡ እያጀባት

    ንግግር ሳይኖረው ሰላምታ ሳይሰጣት

    ፀባይዋን ሳያውቅ በሩቁ ብቻ እይቷት

    ውበት ቁመናዋ እጅግ በጣም ማርኮት

    የትዳር ጓደኛው እንድትሆን ሲመኛት

    አጋጣሚ ሲያገኝ ጊዜ ሲፈቅድለት

    አይጠራጠርም የእሱ እንደሚያደርጋት

    ያች ያፈቀራት ሰው ልቡ የፈቀዳት

    ባለትዳር ትሁን ፍቅረኛ ይኑራት

    ወይም የእሷን ፈቃድ ምንም ሳይጠይቃት

    እሱ እንደፈለገ የሚያሽከረክራት

    ትዕዛዙን አክባሪ እሽ የሚቀናት

    ፍጹም የዋህና ቅን አድርጎ እያያት

    የእራሱን ፍላጎት ብቻ በመመልከት

    ማፍቀሬን አውጥቼ እኔ ስገልጽላት

    ወደደችም ጠላች መቀበል አለባት

    በማለት የግሉ የብቻው ሊያደርጋት

    እንደ እቃ የእኔ ነሽ ብሎ ሲገልጽላት

    ማፍቀር የማትችል ስሜትም የሌላት

    ወይም ይህን አርጊ ተብሎ ሲነገራት

    ምንም ሳትጠይቅ መፈፀም ያለባት

    የሰው አሻንጉሊት አድርጎ ቆጥሮአት

    ከእኔ ጋር ተስማምተሽ ትዳር ከመመስረት

    የተለየ ሌላ አማራጭ የለሽም ብሎ ሲያስፈራራት

    እሷም ይህን ሀሳብ ውድቅ ስታደርግበት

    ያለፍላጎቷ በግድ ጠልፎ ማግባት

    ስብዕናን መካድ ነው ፍጹም እንስሳነት

    ወንጀል እየሰሩ በሰው ስቃይ መርካት

    ይህ አረመኔነት ርህራሄ ማጣት

    ጭራሽ አይለይም ህሊናን ከመሳት

    ጭካኔና በቀል ሆን ብሎ ከመዝራት

    በእርጋታ ካየነው ሁሉንም በትግዕስት

    ሁኔታዎች ሰምረው ጊዜ ሲፈቅድለት

    ሆን ብሎ እያወቀ የፈፀመው ድርጊት

    እጥፍ ድርብ ሆኖ ልክ እንደ እግር እሳት

    በጣም አስጨንቆ ሰላም አሳጥቶት

    ፋታ አልሰጥህ ሲለው ስቃይ ሲበዛበት

    ይቆይ እንደሁ እንጂ አንድ ቀን በሂደት

    ያለፈ ህይወቱን መለስ ብሎ ቃኝቶት

    መፀፀቱ አይቀርም በፈፀመው ድርጊት

    የሰዎችን ስሜት እንዲሁም ፍላጎት

    በደንብ ሳይረዱ ወይ ሳይሰጡት ትኩረት

    እንዲያው በአጠቃላይ በደንታ ቢስነት

    እንዲሁም በትዕቢት ማን አለብኝነት

    በሀይል አስገድዶ ሚስት ጠልፎ ማግባት

    አለአዋቂነት ነው በጣም ከባድ ስህተት

    ረመጥ እሳት ውስጥ አይን እያየ መግባት

    ማርከሻ የሌለው መርዝ አውቆ መጠጣት

  • እንባ (ሐምሌ 2000)

    ሰው አገር ሰላም ነው ብሎ በሙሉ እምነት

    ያለምንም ሀሳብ በተቀመጠበት

    ጭራሽ ለምን እንደሁ በማያውቀው ምክንያት

    ሰዎች የእሱን ክፉ ውድቀት ሲመኙለት

    ያልሠራውን ሠራህ በማለት ሲከሱት

    ሆን ብለው ደጋግመው በነገር ሲወጉት

    ፋታ አሳጥተውት ሰላሙን ሲነሱት

    ምነው ባልተፈጠርኩ እስኪል ሲያበሳጩት

    ስቃዩን አብዝተው ተስፋ ሲያስቆርጡት

    በመሸነፍ ስሜት መላ ቅጥ ጠፍቶበት

    የዉሸት ሳቅ ይስቃል ሳያስበው ድንገት

    ከዚያም መለስ ብሎ ጊዜ ሳይወስድበት

    የገዛ ድርጊቱ በጣም አስገርሞት

    ለካስ እንደዚህ ነው ወዶ አይስቁም ማለት

    አንጀት እያረረ ፈገግታ ማሳየት

    በማለት በልቡ እራሱን ታዝቦት

    ምንም ጊዜ ሳይወስድ በመጽናናት ስሜት

    ውስጣዊ ስሜቱን ሰዎች ካወቁበት

    ደካማ ነው ብለው እንዳይታዘቡት

    ወይም የማይወዱት ሊያዩት የማይፈቅዱት

    ሁኔታው አይተው ጮቤ እንዳይረግጡበት

    ብሶቱን አፍኖ እምቅ አርጎ ይዞት

    ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰበት

    ፍጹም ደስተኛ መስሎ ለመታየት

    ሳቅና ፈገግታ ፊቱን አፍክተውት

    እራሱን አታሎ ሌሎችን ሲያሳስት

    እንዲያው በአጠቃላይ ያለምንም ሀፍረት

    ያልሆነውን ሆኖ ሲቀርብ እሌሎች ፊት

    በጣም ያሳዝናል የዚህ አይነት ፍጥረት

    ፍጹም ወሰን የለሽ ይሉኝታ ቢስነት

    ሌላ ጊዜ ደግሞ ስናየው በቅርበት

    የሆነውን ሁሉ በጭራሽ ረስቶት

    ስሜት የሚነካ ወይ አሳዛኝ ክስተት

    ምንም ሳያስበው ድንገት ሲደርስበት

    በድንጋጤ ሀይል ማስመሰሉን ትቶት

    እንባውን መቋጠር በፍጹም ተስኖት

    ገንፍሎ ጉንጩ ላይ ሲፈስስ እንደ ጅረት

    በውስጡ ያለውን እውነተኛ ስሜት

    ሀዘኑን ፈንቅሎ ስለሚያወጣለት

    እርካታ ያገኛል የመንፈስ ነፃነት