ህያው መልዕክት (ነሐሴ 2000)

ያ ትልቁ ነብይ እየሱስ ክርስቶስ

መስቀል ላይ እያለ ስቅስቅ ብሎ ሲያለቅስ

ሊማፀን አይደለም ፍጻሜው እንዳይደርስ

መፈፀም ያለበት መሆን የሚገባው

ማንም ሊለውጠው አልያም ሊያስቀረው

እንደማይቻለው ቀድሞ ስለአወቀው

እጣውን በፀጋ ነው የተቀበለው

ህይወቱ ለህልፈት በተዳረገባት

በመጨረሻዋ በዚያች ወሳኝ ሰአት

ለአዳም ዘር ሁሉ ነው ያደረገው ፀሎት

የሰው ልጆች ሁሉ ሀጢያት አስክሮአቸው

በስሜት ተገፍተው ማሰብ ተስኖአቸው

የሚያደርጉት ሁሉ ግራ እያጋባቸው

ይይዝ ይጨብጡት ስለጠፋባቸው

እባክህ አባቴ አንተ ይቅር በላቸው

ብሎ በንፁህ ልብ በጣም አዝኖላቸው

ታላቁ ፈጣሪ ሁሌ እንዲያስባቸው

መልሶ መላልሶ ፀሎት አርጎላቸው

ከዚያም አልፎ ተርፎ ዘመን የማይሽረው

እውነተኛ ፍቅሩን በእንባው ገልፆላቸው

ለእናንተ ብዬ ነው እንዲህ የማነባው

ይኸው ተፈፀመ የሚል ህያው መልዕክት ጥሎ ነው የሄደው

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *