ኑሮ ያልተመቸው በለስ ያልቀናችው
የህይወት ትርጉሙ አልታይህ ያለው
ይህን አደርጋለሁ የሚል አቋም ጸለው
ሃሳቡ ግብ ሳይደርስ ማንም አያቆመው
ችግር ተደራርቦ እጅግ ሲያስመርረው
በደሉ በዝቶበት መሸከም ሲያቅተው
የሚሰማው አጥቶ ግፉ እጅ እጅ ሲለው
አይዞህ የሚል ጠፍቶ ሲሰቃይ ለብቻው
ግራ ቀኙ ገደል ሆኖ ሲያስጨንቀው
የነገው ቀን ልዩ ሌላ አልመስል ሲለው
ስለ ዛሬ ብቻ ስለ አሁኑአ ስዓት
እያብሰለሰለ ሲሞላ በጭንቀት
መጪው ጊዜ ተስፋ ይዞ እንደሚመጣ
መቀበል አቅቶት አማራጮች ሲያጣ
በአዕምሮው አጥብቦ በሳላት አለም ውስጥ
ምንም ቦታ የለኝ ብሎ ተስፋ ሲቆርጥ
ማስተዋል ሲያቅተው ዙሪያውን መመልከት
ክርክር ይይዛል ከእራሱ ጋር ሙግት
ለምን እኖራለሁ ብሎ መፈላሰፍ
የዛሬዋን እለት ፍፁም ላለማለፍ
በእሱው በእራሱ ላይ ውሳኔ ለመስጠት
መስሎ የታየውን መደርደር ምክንያት
ከዚያም በመቻኮል ተገፍቶ በስሜት
ወስኖ ይነሳል እራሱን ለማጥፋት
Leave a Reply