Category: 1991

  • ትዝብት (ጥር 1991)

    በበሳል አዕምሮ በደንብ ሲመረመር

    ይሆናል ለማለት በጣም የሚያስቸግር

    ህሊና ላለው ሰው እጅግ የሚያሳፍር

    የዝቅጠት ምልክት ተደርጎ የሚቆጠር

    የግል ፍላጎት ቅድሚያ የሚሰጥበት

    ይሉኝታና ሀፍረት የተዘነጉበት

    ስብዕና የሚባል ትርጉሙን ያጣበት

    ትግዕስት የሚፈትን እልህ ውስጥ የሚከት

    በሁሉም ረገድ ግልጽነት የሚባል የማይታይበት

    በህብረተሰቡ ተቀባይ ያልሆነ ህገወጥ ድርጊት

    ሰዎች ሲፈፅሙ ቀጥታ ለማየት እደሉ ሲገጥመን

    ወይም ቀደም ብለን መሆኑ እንደማይቀር ምልክት እያየን

    በራስ መውደድ ስሜት በፍርሃት ተውጠን

    ሙከራ ሳናደርግ ለማስቆም ድርጊቱን

    የፈለገው ይሁን በእኛ እስጸልመጡብን

    የሚል አቋም ይዘን ታዝበን ማለፉን

    ባህል አርገነዋል ሀቁን በቀጥታ መጋፈጥ ሲገባን

    የትዝብት አይነቶች በጣም ብዙ ናቸው

    በመጸከላቸው የጎላ ልዩነት የሚታይባቸው

    እንደሰው ባህርይ ሁሉንም ልዩዎች የሚያስመስላቸው

    ግልጽም ይሁን ድብቅ የግል መገለጫ ምንም ቢኖራቸው

    ትዝብትን እንደ ሀሳብ በጥልቀት ስንቃኘው

    የሰው ልጅ አዕምሮ ውስብስብ የሆነው

    በመሆኑ ምንጩ ዋናው መፈጠሪያው

    በጣም ያስቸግራል በደንብ ለመለየት አንዱን ከሌላኛው

    ትዝብት በተናጠል እንዲሁ በእራሱ ዋጋ ስለሌለው

    ከሀሜትነት የሚያልፍ ትርጉም የሚኖረው

    ህግን ለማስከበር ፍትህን ለማስፈን ውክልና ላለው

    አሊያም ተገቢ እርምጃ እንዲወስድ ስልጣን ለተሰጠው

    ቁልፍ ማስረጃና ሥራውን የሚያግዝ በመሆን ሲረዳው

    ከዚያም አልፎ ተርፎ ትምህርት ሲሆነው ነው

    በአንፃሩ ግን ደግሞ ይኸ ነው የሚባል ጸላመጣ ጥቅም

    ፋይዳ ቢስ የሆነ የፈሪዎች ቋንቋ ከመሆን አያልፍም

  • ወንበር (መጋቢት 1991)

    ጥቂቶቹ ብቻ የሚቀመጡብሽ

    አንቺ ጋር ለመድረስ ሰው የሚሻማብሽ

    እስኪ እንነጋገር አዋይኝ እባክሽ

    ተፈጥሮሽ እንዴት ነው አመለጸከትሽ?

    እኔ አልወድልሽም ይህን ዝምታሽን

    ፀባዩን ሳታውቂ ሳትጠራጠሪ ፍፁም ማንነቱን

    የመጣውን ሁሉ ችለሽ ማስቀመጡን

    ሊገባኝ አልቻለም ያንቺ መመዘኛ

    የምትመርጭበት ያንን ባለሳምንት አዲሱን ተረኛ

    ጥቅምሽ ማንነትሽ ግልፅ ያልሆነላቸው

    ግለኝነት ስሜት አንቆ የያዛቸው

    በንፁህ አይምሮ ማሰብ ያቃታቸው

    መሳሪያ ሊያደርጉሽ ለእኩይ አላማቸው

    አንቺን የሚመኙሽ በጣም ብዙ ናቸው

    በአንፃሩም እንዲሁ መልጸም ስራ መስራት የሚያስደስታቸው

    በጎ አመለጸከት ቅንነት ያላቸው

    የጊዜያዊ ደስታ የማይደልላቸው

    ለሌሎች ደህንነት የሚያስቡ አርቀው

    ህዝብን ለማገልገል የተነሱ ታጥቀው

    በእጅ የሚቆጠሩ በጣም ጥቂት ናቸው

    እባክሽ ንገሪኝ እስኪ ልጠይቅሽ

    ጥሩውን ከመጥፎው እንዴት ትልያለሽ?

    ወይስ!!!

    አንደበትሽ ታስሮ ግራ እየተጋባሽ

    ሲፈራረቁብሽ ዝም ብለሽ እያየሽ

    የመጡትን ሁሉ ታስተናግጃለሽ

    እስኪ ልጠይቅሽ ሚስጥርሽን ንገሪኝ

    አንቺ ጋር ሲቀመጥ ሰው ምን እንደሚያገኝ

    እኮ ለምንድነው የጠበቀ ፍቅርከ አንቺ የሚይዘው?

    ተለይቶሽ መኖር በጣም የሚከብደው

    ምን ብታስነኪው ነው የሙጥኝ የሚለው

    አንቺን ጥሎ መሄድ የማይታሰበው

    ተገዶ ጸልሆነ ጸንቺ የማይለየው

    ሌሎች እንዳይነኩሽ ታጥቆ የሚታገለው

    ምንድንው ሚስጥሩ አንቺን የሚያስፈቅር

    ህሊናን የሚያስት ልብን የሚሰውር

    ይሉኝታን አሽጦ ጸንቺ የሚያቆራኝ

    ሌላው ሰው አይንጸሽ የኔ ነሽ የሚያሰኝ

    ሆደ ሰፊ ሆነሽ ብዙ ታዝበሻል

    ሲወጡ ሲወርዱ ብዙዎችን አይተሻል

    ማንነታቸውን በደንብ ተረድተሻል

    ፀባያቸውንም መመዘን ችለሻል

    ብዙ ይኖርሻል የምታጫውቺኝ

    እንደ ሚስጥረኛ የምታጸፍይኝ

    ንገሪኝ እባክሽ ስለዚያ መሰላል

    ከምን እንደሰሩት ምን እንደሚመስል

    ላይሽ ላይ ለመውጣት ሁሉም ሲሞክረው

    እያንሸራተተ ስለሚመልሰው

    ጥቂቶችን ብቻ አንቺ ጋ የሚያደርሰው

    ከዚያም ከመቅስበት ስለሚሰወረው

    መውረድ እንዳይችሉ ስለሚያደርጋቸው

    ወደታች እያዩ ተውጠው በፍርሃት

    እንዳይመለሱ በዚያው በወጡበት

    ስለሚሳናቸው መሰላሉን ማግኘት

    ምርጫቸው ይሆናል ከአንቺ ጋር መቆየት

    በጣም ተስማምቶኛል እኔ አልወርድም ማለት

    ተራው የደረሰው በጣም የቸኮለው

    የወጡትን ወርደው ማየት የሚመኘው

    የአንቺን ነፃ መሆን ነቅቶ የሚጠብቀው

    መቀመጫ ሲያጣ ግራ ግብት ሲለው ቦታው ተይዞበት

    ወስኖ የነሳል ሊያስለቅቅ በጉልበት

    አንቺን ትተው መውረድ የማይታያቸው

    የማይችሉት ጠላት ሲደርስ ከፊታቸው

    መንገዱ መሄጃው ይጠፋባቸዋል

    ዙሪያው ገደል ሆኖ ያስፈራራቸዋል

    ከአንቺ መለየቱ ያስጨንቃቸዋል

    ምርጫቸው ይሆናል የሙጥኝ ማለት

    የመጣው ቢመጣ ጸንቺ መቆራኘት

    እስክ መጨረሻው አብሮ ለመቆየት

    ለመርሳት መሞከር የመጣውን ጠላት

    እራስን ማታለል አንቺን ላለማጣት

    በተጠንቀቅ መቆም ለመሰዋትነት

    ሁሉን መጠራጠር መመልከት በስጋት

    እውነትን ለማየት እጅግ በጣም መፍራት

    በተስፋ በመኖር ጥቂት ጊዜ መግዛት

    ይህ ከንቱ ሙከራ ስሜት የማይሰጠው

    አንቺ ጋር ለመድረስ ቆርጦ የተነሳው

    ጊዜና ጉልበቱን ላንቺ ያፈሰሰው

    አንቺን የእሱ ማድረግ አላማው የሆነው

    አዲሱ ፍቅርኛሽ አለሁልሽ ባይሽ

    ነቅቶ የሚጠብቅሽ የብቻው ሊያደርግሽ

    መንገዱን በመጥረግ ባለ ለሌለ ሃይሉ

    ፍፁም ሲመቻቹ ሁኔታዎች ሁሉ

    ያሰበውን ሳይዝ ማንም አይመልሰው

    ለአንቺ ሲል ለመሞት በጣም ዝግጁ ነው

    ጸንቺ መለየቱ ሞት የመሰላቸው

    ያለውድ በግድ ሲለቁሽ ተገፍተው

    ይሰባበራሉ ተሽቀንጥረው ወድቀው

    ለመፀፀት እንኳን ጊዜው ሳይኖራቸው

  • አንገት (ታህሳስ 1991)

    ያንገት ጠቀሜታ ያልገባን ብዙ ነን

    የማንመለከት ግራ ቀኝ እያልን

    ከፊት ለፊት ብቻ የምናይ አፍጥጠን

    ወደሗላ ዞረን ጭራሽ የማንቃኝ

    በፈጠርነው አለም በህልም የምንዋኝ

    ፍፁም የምንረሳ ማንነታችንን

    ጊዜያዊ ደስታና ጥቅም የሚገዙን

    መርህ ያደረግነው ሆድ አምላክነቱን

    አንገት መፈጠሩ አዙሮ ለማየት መሆኑን እረስተን

    በደመነፍስ ያለን ተነድተን በስሜት

    ጥሩውን ከመጥፎ ያቃተን መለየት

    በጣም ብዙዎች ነን አርቀን የማናይ

    ስሜት የማይሰጠን የሌላው ሰው ጉዳይ

    ሁሌ የሚመስለን በኛ የማይደርሱ መከራና ስቃይ

    ለኛ የሚል ቋንቋ ፍፁም የማይገባን

    አዕምሮአችን ዞሮ የማናመዛዝን

    ማሰብ የተሳነን ሁሌ ለእኔ የምንል

    የመኖር ትርጉሙን መረዳት ያቃተን

    የራሳችን ጉዳይ ሁል ጊዜ ሌት ተቀን ፋታ የማይሰጠን

    የምናብሰለስል በተንኮል ተሞልተን

    ሌሎች ሲቸገሩ ፀጥታን የምንመርጥ ጆሮአችንን ደፍነን

    በጣም ብዙዎች ነን ለኔ ከሚል ቃል ውጭ ሌላ የማይጥመን

    በጥቅም ታውሮ ሁሌ መስገብገቡ

    ለብቻ መኖሩ ለራስ እያሰቡ

    ፍፁም ተለይቶ ከህብረተሰቡ

    ስብዕናን መጸድ ነው ተፈጥሮን መጋፋት

    ጭራሽ ያለማወቅ የሰውን ማንነት

    በጣም መጠራጠር የአዕምሮውን ብስለት

    ሰውን ማመሳሰል ከእንስሳት ጸራዊት

    ግለኝነት በጣም የተወገዘ ነው በታሪክ በባህል

    ይህን በማስመልከት በሃገራችን አለ አንድ ጥሩ ብሂል

    ብቻውን የበላ ብቻውን ይሞታል

    ተብሎ የሚነገር ስለ ግለኝነት

    በምሳሌነቱ ወደር የሌለለት

    መስታወት የሚሆን ለሚጠቀምበት

    የሰው ልጅ በህብረት መኖር እንዳለበት

    ለሚገባው ሁሉ ሰጪ ጥሩ ትምርት

    የምንኖርባት ይህች ምድራዊ አለም

    የብድር መሆኗን መርሳት የለብንም

    ለመቀበል መስጠት ለማጨድም መዝራት

    እንደሚያስፈልጉ መታወቅ አለበት

    ለእኔ በሚል ፈሊጥ የራስን በር ዘግቶ

    በደንታ ቢስነት ሌላውን ረስቶ

    መኖር ለራስ ብቻ የሚለው ተኩራርቶ

    የሚያደርገው ሲያጣ ችግር ሲያግጠመው

    ቀኑ ጨልሞበት ሲያጥርበት ማጣፊያው

    መቅረብ ይጀምራል የማያውቀውን ሰው

    ቅብጥብጥ ማለት ችግሩን ሊያዋየው

    ቅልብጭ ያለ መፍትሄ በቶሎ እንዲሰጠው

    ያደረገው ድርጊት ምስከር ሆኖበት

    በችግሩ ጊዜ ሲያጣ የሚደርስለት

    ማሰብ ይጀምራል ስለ እራሱ ህይወት

    ላለፈው ድርጊቱ ከልብ መፀፀት

    ማንነቱን ክዶ ሸፋፍኖ ስራውን

    መረዳት ሲጀምር መኖር እንደማይችል ከእንግዲህ ብቻውን

    ያኔ ይጀምራል አዙሮ መመልከት

    ከሰው ጋር ለመኖር አዕምሮውን መክፈት

    ጠልቆ መመራመር ስለ ሰው ማንነት

    ግለኝነትንም አጥብቆ መዋጋት

  • እኛ እንሻላለን (ሐምሌ 1991)

    ይኸ የእኛ ትውልድ ፍጹም ያልታደለው

    ምነው ከእራሱ ጋር መታረቅ አቃተው

    ንትርክ ያበዛል በሆነ ባልሆነው

    የሌላውን ሀሳብ በደንብ ለመረዳት

    በሰከነ መንፈስ ትግዕስት በሞላበት

    እየተደማመጥን ሳናደርግ ውይይት

    ልዩነታችንን ሳንሞክር ለመፍታት

    የሃሳብ ልዩነት ቀርቦ እንደ ምክንያት

    መቻቻል አቅቶን ተገፍተን በስሜት

    በአስተሳሰባቸው ከእኛ ለተለዩት

    እውቅና መስጠቱን ቆጥረን እንደ ውርደት

    የተለየ ሃሳብ ፍጹም ላለመስማት

    እኛ እነሱ ብለን ተከፍለን ለሁለት

    አጥፍተን ለመጥፋት ቆርጠን በመነሳት

    ስንፈጽም ይታያል በጣም ብዙ ስህተት

    ከእኛ ጎን ያልቆሙት ፀረ ህዝብ ናቸው

    ህዝብ ይከፋፍላል አስተሳሰባቸው

    ፈጽሞ አይገባም ዕድል ሊሰጣቸው

    አማራጭ የለውም የእኛ አቋም ገዥ ነው

    የሚል አስተሳሰብ ይዘን በመነሳት

    እኛን ፍጹም ታማኝ ሌሎችን ግን ጠላት

    አድርገን ስናቀርብ በየደረስንበት

    በመጸከላቸን ይታይ የነበረው የሃሳብ ልዩነት

    በጣም እንዲሰፋ ሁኔታውን ሁሉ አመቻችተንለት

    ከዚያም እየፈለግን ሰንጸላ ምክንያት

    በቂም በቀል መንፈስ የሰውን ስም ማጥፋት

    መስሎ ይታየናል ጥሩ የትግል ስልት

    በዚህ አያቆምም የምንሠራው ጥፋት

    ጊዜ ሳናጠፋ ፈጥነን እንከፍትና የወሬ ጦርነት

    የእኛ ተቀናቃኝ ሆነው የተነሱት

    ሌላ አላማ ይዘው ትግል ውስጥ የገቡት

    ዘለቄታ ያለው ጥሩ ለውጥ ለማምጣት

    ወይም ለችግሮች እልባት ለመስጠት

    ፍጹም የሌላቸው ችሎታና ብቃት

    አድርጎ ተራው ህዝብ አነሱን በማየት

    ከዚያም ተጠራጥሮ ጥላቻ እንዲያድርበት

    እንግተዋለን መስሎ የታየንን አሳማኝ ምክንያት

    ያሏቸው እቅዶች ፋይዳ እንደሌላቸው

    ጨለምተኛ ባህል አንቆ እንደያዛቸው

    የህዝብ ጥያቄ ደንታ የማይሰጣቸው

    ለግል ጥቅማቸው የተነሱ ቆርጠው

    ይሉኝታ የሚባል ያልፈጠረባቸው

    እንደሆኑ አድርገን በዙ አሳጥተናቸው

    አቋማቸው ከእኛ የተለየበትን

    ምክንያት እንድንሰጥ ጥሪ ሲቀርብልን

    አሳማኝ የሆነ ማስረጃ አያይዝን

    አጥጋቢ የሆነ መልስ መስጠት ሲያቅተን

    እንዲሁ በግምት ተነስተን በጭፍን

    እኛን የህዝብ ዘብ እንከን የሌለብን

    እነሱን ጠላቶች አድርገን ማቅረቡን

    በጣም ስለሚቀል እንመርጠዋለን

    በወሬው ዘመቻ በደንብ ገፍተን ሄደን

    እኛ ከእነሱ ይልቅ የተሻልን እንደሆን

    የሚያሳይ ምክንያት እንደረድራልን

    ራዕያችን ፍጹም አይቀራረብም

    እኛ ለህዝብ ጥቅም ጥብቅና ስንቆም

    እነሱ በአንጻሩ ስለሚገፋፉ በጥላቻና ቂም

    ደጸማም ጠንጸራም ጎኑን ለመገምገም

    ምንም ሳይሞክሩ ቶሎ በሽቅድድም

    እኛ የምንለውን በጅምላ መቃወም

    የምንሰራውን ተከታትለው ማውደም

    ይህ ነው ተግባራቸው የሚታወቁበት

    ዋናው አላማቸው አርገው ያነገቡት

    አገራዊ ራዕይ ምን እንደሁ አያውቁም

    ድርጊታቸው ሁሉ ምንም ህዝባዊነት አይታይበትም

    በእነሱ ላይ እምነት ሊጣል አይገባም

    በሁሉም መስፈርቶች እኛ እንሻላለን

    ስለዚህ ሁሉንም ለእኛ ብትተውልን

    ያሉትን ችግሮች በሙሉ እንፈታለን

    መሰረታዊ ለውጥ ቶሎ እናመጣለን

    ብለን ያለማፈር እየወቀስናቸው ተቀናቃኞችን

    እንከን የለሽ መስለን ለህዝብ እንቀርባለን

  • ማሙሽ (ጥቅምት 1991)

    ሰው ለምርጫ ሲቀርብ ህዝብ ለማገልገል

    ሰዎች አያውቁኝም አይመርጡኝም በሚል

    ወይም ከተመረጥኩ ማንም አያስታውስ የገባሁትን ቃል

    በማለት ተነስቶ ሁሉን አደርጋለሁ ብሎ ቃል ይገባል

    ይህን እያወቀ አንተን መራጩን ህዝብ ሊያታልል ሲሞክር

    በጥሩ አነጋገር ሊስብህ ሲጣጣር

    ሌት ከቀን ስለአንተ አስባለሁ ሲልህ

    በጭራሽ አትስጋ ፍፁም ቅር አይበልህ

    ገና ለወደፊት ምን ይመጣል ብለህ

    ብዙ ሀሳብ አይግባህ እኔ አለሁ ከጎንህ

    ብሎ በምርጥ ቃላት ሲሸነጋግልህ

    ስህተት ውስጥ እንዳትወድቅ መጠንቀቅ አለብህ

    ይህ ላንተ ቆሜያለሁ አስብልሀለሁ ብሎ የሚያወራው

    ቀላል ሰው አይደለም የሩቅ አላማ አለው

    ሰው እንዳያውቅበት በሚስጥር የያዘው

    አጋጣሚ ሲያገኝ ገሃድ የሚያወጣው

    የሚያነበንበው በግልፅ የሚሰብከው

    ፍትህ እኩልነት ሰላም ብልፅገናን ሰፍነው ለማየት ነው

    ሃሳቡ እስኪሳጸ እቅዱ እስኪፈፀም

    ጸንደበቱ ፍፁም ሌላ ቃል አይወጣም

    ይህ ሁሉ ውትውታ በቂ አልመስልህ ሲለው

    ሌላ እቅድ ያወጣል አንተ እንድትመርጠው

    ጭራሽ እንደሌለህ ማሰቢያ ጭነቀላት

    እንደማትችል ሁሉ ሃሳብን ለመግለፅ በራስህ እንደበት

    ያ ላንተ አስባለሁ እጨነቃለሁ ባይ

    ለእኔ ተወው ይላል የራስህን ጉዳይ

    እየደጋገመ እጅ እጅ እስከሚልህ

    ለህዝብ እንደቆመ መግለጫ እየሰጠህ

    እያዥጎደጎደ ምርጥ ምርጥ ቃላትን

    ሊያሳምን ሲþሞክር ትልቅ ሰውነቱን

    የሱን ጎበዝነት ያላማ ፅናቱን

    ቀጠል ያደርግና

    እኔ ነኝ የማውቀው መሆን ያለበትን

    የህዝብ ችግሮች የሚፈቱበትን

    በጣም በአጭረ ጊዜ ጥሩ ለውጥ ለማየት

    እናንተ አትድከሙ ሁሉን ለኔ ተውት

    ወሰን የለሽ ስልጣን ስጡኝ ሃላፊነት

    ማለት ይጀምራል ደጋግሞ መወትወት

    አጋጣሚ አግኝቶ ስልጣን ከጨበጠ

    አጭበርባሪ የለም ከሱ የበለጠ

    ሰውን ለመመዘን ባዘጋጀው መስፈርት

    እሱ ነው አዋቂ ብቸኛው ሳይንቲስት

    ሁሉም ሰው ማሙሽ ነው አርቆ የማያስብ

    ሊታለል የሚችል ያለምንም ገደብ

    ስለዚህ ይሆናል ፈላጭ ቆራጭ ዳኛ

    ማንም የማያዘው የስልጣን ቀበኛ

    እሱን ለሚቃወም ጭራሽ የማይተኛ

    ይሉኝታ የሌለው ትልቅ ወንጀለኛ

    ለረጅም ዘመናት ደብቆ የያዘው

    ይወጣል ፀባዩ ፍፁም እውነተኛው

    መስገብገብ ያበዛል ሀብት ለማጸበት

    በስልጣን መባለግ ሁሉን ለእኔ ማለት

    ተቃዋሚን ማፈን በሃይል ዝም ማሰኘት

    የቀረውንም ህዝብ መሸንገል በቃላት

    ሁሌ እየመሰለዉ የማይነቃበት

    ችግሩ ብዙ ነዉ ጊዜ ስጡኝ ማለት

    ሽንገላዉ ድለላዉ ብሶቱ ሲበዛ

    ማሙሽ የተባለዉ ይነሳል በቁጣ አይደም የዋዛ

    በስሙ የሚነግድ ያኔ ወየዉለት

    ማጣፊያዉ ያጥረዋል ይወጣል በፍርሀት

    በብልጣብልጥነት ለሚያደርሰዉ ጥፋት

    የእጁን ያገኘዋል ተገቢዉን ቅጣት

  • መሀል ሰፋሪ (ጥር 1991)

    የማይቀራረብ ወይም ተቃራኒ ሀሳብ አራማጆች

    ቡድኖችም ሆኑ ወይም ግለሰቦች

    በሃሳብ ሲፋጩ ጎራ በመለየት

    ሁለቱም ወገኖች እንዳይቀየሙት

    ወይ እንዳይፈርጁት በወገንተኛነት

    ማንንም አልደግፍ የሁሉም ነኝ ማለት

    ያለአዋቂነት ነው እጅጉን መሳሳት

    መሀል ሰፋሪ ሰው ግልፅ አቋም የለውም

    ከአንዱ ጋር መወገን የሚያሳጣው ጥቅም

    ስለሚያሳስበው ለመጽናት በአንድ አቋም

    ድፍረቱ አይኖረውም ይላል ወለም ዘለም

    በዚህ የተነሳ ምክንያት ከመስጠት ወደ ኋላ አይልም

    በመጸከላቸው የረባ ልዩነት ጭራሽ አላየሁም

    አንዳቸው ከሌላው ይሻላሉ ብዬ በፍጹም አላምንም

    የፈለገው ይምጣ አንዱን ከሌላው ጋር አላበላልጥም

    ብሎ ሃሳቡን ሲገልጽ ሁሉም እንዲሰሙት

    ለማመቻቸት ነው ለማግኘት ሙሉ እምነት

    ገለልተኛ አድርገው እንዲመለከቱት

    አንዱ ወገን ሲጎዳ እኔን ምን አገባኝ

    ዝም ብዬ ማየት ነው በእኔ እስጸልመጡብኝ

    በመጸከላቸው የፈለገው ይሁን አያሳስበኝም

    እስጸልነኩኝ ድረስ ስሜት አይሰጠኝም

    አስቸጋሪውን ወቅት በጣም ተጠንቅቄ አሳልፈዋለሁ

    ከማንም ሳልወግን ሁሉንም በእኩል አይን እመለከታለሁ

    ማን እንደሚያሸንፍ በሂደት ቀስ ብዬ እከታተላለሁ

    የሚል አቋም ይዞ ምን እንደሚመጣ ለማየት መወሰን

    በደንብ ለይቶለት እስኪታወቅ ድረስ አሸናፊው ወገን

    በልቡ እያወቀው ወላዋይነቱን እንደማይገፋበት

    የኋላ የኋላ ከአንዱ ጋር መወገን እንደሚኖርበት

    አንደኛውን ወገን መምረጥ በሚገባው በወሳኙ ሰአት

    ቶሎ እንደሚጠጋ የሃይል ሚዛኑ ወደሚደፋበት

    ይህ አመለጸከት የዚህ አይነት ድርጊት

    ሌላ ስም የለውም አድርባይነት ነው እራስ ወዳድነት

    ጽኑ አቋም ለመያዝ እጅግ በጣም መፍራት

    ህሊናን በመሸጥ ለጥቅም መገዛት

    ሌሎችን በመጉዳት ሁሌ ለእኔ ማለት

    መሀል ሰፋሪነት ወይም መወላወል

    እንደ አቋም ሲፈተሽ ብዥታን ይፈጥራል

    ምክንያቱን ማወቅ በጣም ያስቸግራል

    በሌላ በኩል ግን በደንብ ለሚያስተውል

    የሚያስተላልፈው መልዕክት ይኖረዋል

    የሰውን ተፈጥሮ ለማወቅ ይጠቅማል

    የሰው ልጅ ሁለት አፍ እንዳለው ያሳያል

    ስለሆነ ጉዳይ ሃሳቡን ሲገልጽ ለተለያየ አጸል

    አንዴ ጥሩ ነገር ሌላ ጊዜ መጥፎ አርጎ ያቀርበዋል

    እንደየሁኔታው የያዘውን አቋም ይቀያይረዋል

    አቋም ያለማያዝ መሀል ሰፋሪነት

    እየሆነ መጥቷል የፖለቲጸ ስልት

    በደንብ ሲመረመር ሲፈተሽ በጥልቀት

    መጥፎ ባህርይ ነው መሀል ሰፋሪነት

    የሰው ልጅ ድክመቶች የሚገለጡበት

    የብልጣብልጥነት የእራስ ወዳድነት

    የወላዋይነት የፍርሀት የቅሌት

    እንዲያው በአጠቃላይ የዝቅጠት ምልክት

    እውነት የሆነውን የሰውን ማንነት

    ቁልጭ አርጎ የሚያሳይ ልክ እንደ መስታወት