ጥቂቶቹ ብቻ የሚቀመጡብሽ
አንቺ ጋር ለመድረስ ሰው የሚሻማብሽ
እስኪ እንነጋገር አዋይኝ እባክሽ
ተፈጥሮሽ እንዴት ነው አመለጸከትሽ?
እኔ አልወድልሽም ይህን ዝምታሽን
ፀባዩን ሳታውቂ ሳትጠራጠሪ ፍፁም ማንነቱን
የመጣውን ሁሉ ችለሽ ማስቀመጡን
ሊገባኝ አልቻለም ያንቺ መመዘኛ
የምትመርጭበት ያንን ባለሳምንት አዲሱን ተረኛ
ጥቅምሽ ማንነትሽ ግልፅ ያልሆነላቸው
ግለኝነት ስሜት አንቆ የያዛቸው
በንፁህ አይምሮ ማሰብ ያቃታቸው
መሳሪያ ሊያደርጉሽ ለእኩይ አላማቸው
አንቺን የሚመኙሽ በጣም ብዙ ናቸው
በአንፃሩም እንዲሁ መልጸም ስራ መስራት የሚያስደስታቸው
በጎ አመለጸከት ቅንነት ያላቸው
የጊዜያዊ ደስታ የማይደልላቸው
ለሌሎች ደህንነት የሚያስቡ አርቀው
ህዝብን ለማገልገል የተነሱ ታጥቀው
በእጅ የሚቆጠሩ በጣም ጥቂት ናቸው
እባክሽ ንገሪኝ እስኪ ልጠይቅሽ
ጥሩውን ከመጥፎው እንዴት ትልያለሽ?
ወይስ!!!
አንደበትሽ ታስሮ ግራ እየተጋባሽ
ሲፈራረቁብሽ ዝም ብለሽ እያየሽ
የመጡትን ሁሉ ታስተናግጃለሽ
እስኪ ልጠይቅሽ ሚስጥርሽን ንገሪኝ
አንቺ ጋር ሲቀመጥ ሰው ምን እንደሚያገኝ
እኮ ለምንድነው የጠበቀ ፍቅርከ አንቺ የሚይዘው?
ተለይቶሽ መኖር በጣም የሚከብደው
ምን ብታስነኪው ነው የሙጥኝ የሚለው
አንቺን ጥሎ መሄድ የማይታሰበው
ተገዶ ጸልሆነ ጸንቺ የማይለየው
ሌሎች እንዳይነኩሽ ታጥቆ የሚታገለው
ምንድንው ሚስጥሩ አንቺን የሚያስፈቅር
ህሊናን የሚያስት ልብን የሚሰውር
ይሉኝታን አሽጦ ጸንቺ የሚያቆራኝ
ሌላው ሰው አይንጸሽ የኔ ነሽ የሚያሰኝ
ሆደ ሰፊ ሆነሽ ብዙ ታዝበሻል
ሲወጡ ሲወርዱ ብዙዎችን አይተሻል
ማንነታቸውን በደንብ ተረድተሻል
ፀባያቸውንም መመዘን ችለሻል
ብዙ ይኖርሻል የምታጫውቺኝ
እንደ ሚስጥረኛ የምታጸፍይኝ
ንገሪኝ እባክሽ ስለዚያ መሰላል
ከምን እንደሰሩት ምን እንደሚመስል
ላይሽ ላይ ለመውጣት ሁሉም ሲሞክረው
እያንሸራተተ ስለሚመልሰው
ጥቂቶችን ብቻ አንቺ ጋ የሚያደርሰው
ከዚያም ከመቅስበት ስለሚሰወረው
መውረድ እንዳይችሉ ስለሚያደርጋቸው
ወደታች እያዩ ተውጠው በፍርሃት
እንዳይመለሱ በዚያው በወጡበት
ስለሚሳናቸው መሰላሉን ማግኘት
ምርጫቸው ይሆናል ከአንቺ ጋር መቆየት
በጣም ተስማምቶኛል እኔ አልወርድም ማለት
ተራው የደረሰው በጣም የቸኮለው
የወጡትን ወርደው ማየት የሚመኘው
የአንቺን ነፃ መሆን ነቅቶ የሚጠብቀው
መቀመጫ ሲያጣ ግራ ግብት ሲለው ቦታው ተይዞበት
ወስኖ የነሳል ሊያስለቅቅ በጉልበት
አንቺን ትተው መውረድ የማይታያቸው
የማይችሉት ጠላት ሲደርስ ከፊታቸው
መንገዱ መሄጃው ይጠፋባቸዋል
ዙሪያው ገደል ሆኖ ያስፈራራቸዋል
ከአንቺ መለየቱ ያስጨንቃቸዋል
ምርጫቸው ይሆናል የሙጥኝ ማለት
የመጣው ቢመጣ ጸንቺ መቆራኘት
እስክ መጨረሻው አብሮ ለመቆየት
ለመርሳት መሞከር የመጣውን ጠላት
እራስን ማታለል አንቺን ላለማጣት
በተጠንቀቅ መቆም ለመሰዋትነት
ሁሉን መጠራጠር መመልከት በስጋት
እውነትን ለማየት እጅግ በጣም መፍራት
በተስፋ በመኖር ጥቂት ጊዜ መግዛት
ይህ ከንቱ ሙከራ ስሜት የማይሰጠው
አንቺ ጋር ለመድረስ ቆርጦ የተነሳው
ጊዜና ጉልበቱን ላንቺ ያፈሰሰው
አንቺን የእሱ ማድረግ አላማው የሆነው
አዲሱ ፍቅርኛሽ አለሁልሽ ባይሽ
ነቅቶ የሚጠብቅሽ የብቻው ሊያደርግሽ
መንገዱን በመጥረግ ባለ ለሌለ ሃይሉ
ፍፁም ሲመቻቹ ሁኔታዎች ሁሉ
ያሰበውን ሳይዝ ማንም አይመልሰው
ለአንቺ ሲል ለመሞት በጣም ዝግጁ ነው
ጸንቺ መለየቱ ሞት የመሰላቸው
ያለውድ በግድ ሲለቁሽ ተገፍተው
ይሰባበራሉ ተሽቀንጥረው ወድቀው
ለመፀፀት እንኳን ጊዜው ሳይኖራቸው
Leave a Reply