ይኸ የእኛ ትውልድ ፍጹም ያልታደለው
ምነው ከእራሱ ጋር መታረቅ አቃተው
ንትርክ ያበዛል በሆነ ባልሆነው
የሌላውን ሀሳብ በደንብ ለመረዳት
በሰከነ መንፈስ ትግዕስት በሞላበት
እየተደማመጥን ሳናደርግ ውይይት
ልዩነታችንን ሳንሞክር ለመፍታት
የሃሳብ ልዩነት ቀርቦ እንደ ምክንያት
መቻቻል አቅቶን ተገፍተን በስሜት
በአስተሳሰባቸው ከእኛ ለተለዩት
እውቅና መስጠቱን ቆጥረን እንደ ውርደት
የተለየ ሃሳብ ፍጹም ላለመስማት
እኛ እነሱ ብለን ተከፍለን ለሁለት
አጥፍተን ለመጥፋት ቆርጠን በመነሳት
ስንፈጽም ይታያል በጣም ብዙ ስህተት
ከእኛ ጎን ያልቆሙት ፀረ ህዝብ ናቸው
ህዝብ ይከፋፍላል አስተሳሰባቸው
ፈጽሞ አይገባም ዕድል ሊሰጣቸው
አማራጭ የለውም የእኛ አቋም ገዥ ነው
የሚል አስተሳሰብ ይዘን በመነሳት
እኛን ፍጹም ታማኝ ሌሎችን ግን ጠላት
አድርገን ስናቀርብ በየደረስንበት
በመጸከላቸን ይታይ የነበረው የሃሳብ ልዩነት
በጣም እንዲሰፋ ሁኔታውን ሁሉ አመቻችተንለት
ከዚያም እየፈለግን ሰንጸላ ምክንያት
በቂም በቀል መንፈስ የሰውን ስም ማጥፋት
መስሎ ይታየናል ጥሩ የትግል ስልት
በዚህ አያቆምም የምንሠራው ጥፋት
ጊዜ ሳናጠፋ ፈጥነን እንከፍትና የወሬ ጦርነት
የእኛ ተቀናቃኝ ሆነው የተነሱት
ሌላ አላማ ይዘው ትግል ውስጥ የገቡት
ዘለቄታ ያለው ጥሩ ለውጥ ለማምጣት
ወይም ለችግሮች እልባት ለመስጠት
ፍጹም የሌላቸው ችሎታና ብቃት
አድርጎ ተራው ህዝብ አነሱን በማየት
ከዚያም ተጠራጥሮ ጥላቻ እንዲያድርበት
እንግተዋለን መስሎ የታየንን አሳማኝ ምክንያት
ያሏቸው እቅዶች ፋይዳ እንደሌላቸው
ጨለምተኛ ባህል አንቆ እንደያዛቸው
የህዝብ ጥያቄ ደንታ የማይሰጣቸው
ለግል ጥቅማቸው የተነሱ ቆርጠው
ይሉኝታ የሚባል ያልፈጠረባቸው
እንደሆኑ አድርገን በዙ አሳጥተናቸው
አቋማቸው ከእኛ የተለየበትን
ምክንያት እንድንሰጥ ጥሪ ሲቀርብልን
አሳማኝ የሆነ ማስረጃ አያይዝን
አጥጋቢ የሆነ መልስ መስጠት ሲያቅተን
እንዲሁ በግምት ተነስተን በጭፍን
እኛን የህዝብ ዘብ እንከን የሌለብን
እነሱን ጠላቶች አድርገን ማቅረቡን
በጣም ስለሚቀል እንመርጠዋለን
በወሬው ዘመቻ በደንብ ገፍተን ሄደን
እኛ ከእነሱ ይልቅ የተሻልን እንደሆን
የሚያሳይ ምክንያት እንደረድራልን
ራዕያችን ፍጹም አይቀራረብም
እኛ ለህዝብ ጥቅም ጥብቅና ስንቆም
እነሱ በአንጻሩ ስለሚገፋፉ በጥላቻና ቂም
ደጸማም ጠንጸራም ጎኑን ለመገምገም
ምንም ሳይሞክሩ ቶሎ በሽቅድድም
እኛ የምንለውን በጅምላ መቃወም
የምንሰራውን ተከታትለው ማውደም
ይህ ነው ተግባራቸው የሚታወቁበት
ዋናው አላማቸው አርገው ያነገቡት
አገራዊ ራዕይ ምን እንደሁ አያውቁም
ድርጊታቸው ሁሉ ምንም ህዝባዊነት አይታይበትም
በእነሱ ላይ እምነት ሊጣል አይገባም
በሁሉም መስፈርቶች እኛ እንሻላለን
ስለዚህ ሁሉንም ለእኛ ብትተውልን
ያሉትን ችግሮች በሙሉ እንፈታለን
መሰረታዊ ለውጥ ቶሎ እናመጣለን
ብለን ያለማፈር እየወቀስናቸው ተቀናቃኞችን
እንከን የለሽ መስለን ለህዝብ እንቀርባለን
Leave a Reply