ትዝብት (ጥር 1991)

በበሳል አዕምሮ በደንብ ሲመረመር

ይሆናል ለማለት በጣም የሚያስቸግር

ህሊና ላለው ሰው እጅግ የሚያሳፍር

የዝቅጠት ምልክት ተደርጎ የሚቆጠር

የግል ፍላጎት ቅድሚያ የሚሰጥበት

ይሉኝታና ሀፍረት የተዘነጉበት

ስብዕና የሚባል ትርጉሙን ያጣበት

ትግዕስት የሚፈትን እልህ ውስጥ የሚከት

በሁሉም ረገድ ግልጽነት የሚባል የማይታይበት

በህብረተሰቡ ተቀባይ ያልሆነ ህገወጥ ድርጊት

ሰዎች ሲፈፅሙ ቀጥታ ለማየት እደሉ ሲገጥመን

ወይም ቀደም ብለን መሆኑ እንደማይቀር ምልክት እያየን

በራስ መውደድ ስሜት በፍርሃት ተውጠን

ሙከራ ሳናደርግ ለማስቆም ድርጊቱን

የፈለገው ይሁን በእኛ እስጸልመጡብን

የሚል አቋም ይዘን ታዝበን ማለፉን

ባህል አርገነዋል ሀቁን በቀጥታ መጋፈጥ ሲገባን

የትዝብት አይነቶች በጣም ብዙ ናቸው

በመጸከላቸው የጎላ ልዩነት የሚታይባቸው

እንደሰው ባህርይ ሁሉንም ልዩዎች የሚያስመስላቸው

ግልጽም ይሁን ድብቅ የግል መገለጫ ምንም ቢኖራቸው

ትዝብትን እንደ ሀሳብ በጥልቀት ስንቃኘው

የሰው ልጅ አዕምሮ ውስብስብ የሆነው

በመሆኑ ምንጩ ዋናው መፈጠሪያው

በጣም ያስቸግራል በደንብ ለመለየት አንዱን ከሌላኛው

ትዝብት በተናጠል እንዲሁ በእራሱ ዋጋ ስለሌለው

ከሀሜትነት የሚያልፍ ትርጉም የሚኖረው

ህግን ለማስከበር ፍትህን ለማስፈን ውክልና ላለው

አሊያም ተገቢ እርምጃ እንዲወስድ ስልጣን ለተሰጠው

ቁልፍ ማስረጃና ሥራውን የሚያግዝ በመሆን ሲረዳው

ከዚያም አልፎ ተርፎ ትምህርት ሲሆነው ነው

በአንፃሩ ግን ደግሞ ይኸ ነው የሚባል ጸላመጣ ጥቅም

ፋይዳ ቢስ የሆነ የፈሪዎች ቋንቋ ከመሆን አያልፍም

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *