ትዝታን ሰንቆ እንዲያስቀምጥልን
የህይወትን ጉዞ ቀጥ አርጎ እንዲያቆየን
ታሪክ ለመዘከር እንዲያገለግለን
የፎቶ ቴክኒክን ላበረከተልን
ለዚያ ለተረሳው ባለውለታችን
ለፈረንሳዩ ሰው ኒኤፒስ ለሚባለው
በአዳም ዘር ስም ሁሉ ምስጋና ይድረሰው
የዚህ ሰው ፈጠራ ይፋ ከሆነበት
ይኸው ተቆጥረዋል ሁለት ምዕተአመተታት
ረዥም በሆነው በዚህ የታሪክ ወቅት
የፎቶ ቴክኒክን በጣም ያሻሻሉት
ለአሁኑ ደረጃው እንዲደርስ ያበቁት
በህይወት ያሉና እንዲሁም የሞቱት
ምስጋና ይግባቸው ሁሉም ላደረጉት
በዚህ በእኛ ዘመን ይህን ሁሉ እረስተን
ያልሆንነውን መስለን መታየት እያሰብን
የእራሳችን ምስል ታትሞ ሲሰጠን
እኛን አይመስለንም ብለን እየዋሸን
ጭራሽ በማናውቀው በሰው ሥራ ገብተን
አስተያየት ስንሰጥ ምንም ቅር አይለን
በፎቶ የምናየው ምስል ደስ ጸላለን
ወይም ለመደበቅ የምንፈልገውን
ቁልጭ አርጎ እንዳለ በግልጽ ጸሳየብን
አልያም ያረጀን በእድሜአችን የገፋን
ወይም በብስጭት በሀዘን የተጎዳን
አድርጎ አቅርቦናል የሚል እምነት ጸለን
እንዲያው በአጠቃላይ ፍፁም ጸልተስማማን
የምንፈልገውን መሆን ጸልቻለልን
እውነቱን እንዳለ መቀበል ሲገባን
ፎቶው ጭራሽ እኛን አይመስለንም ብለን
የዚህ አይነት አቋም ለምን እንደወሰድን
ፎቶውን የሚያዩት ሰዎች እንዲያምኑልን
መሰረት የሌለው ምክንያት ፍለጋ እንባዝናለን
አንዴ ጸሜራውን ችግር እንዳለበት
እስከ ዛሬ ድረስ አንዴ እንኳን በስህተት
ጥሩ የሚባል ፎቶ እንዳልተነሳበት
መረዳት እንደቻልን በቅርብ ከሚያውቁት
በይፋ ስንለፍ ያለምንም ሀፍረት
ሌላ ጊዜ ደግሞ ያንን ፎቶ አንሽውን
ስሙን ስናጠፋው ከመሬት ተነስተን
የሙያ ብቃቱን በተመለከተ ጥርጣሬ እንዳለን
ጤነኛ ነው ብለን ፍፁም እንደማናምን
ወይም ሆነ ብሎ ፎቶውን በተንኮል እንዳበላሸብን
አሳማኝ የሆነ መረጃ እንዳገኘን
እንዲሁ በድፍረት ስናወራ ፈጥረን
ውስብስብ ችግር ውስጥ እንዘፈቃለን
ያልሆንነውን መስለን መታየት ፈልገን
በደንብ ሳናስበው እንደ ቀልድ ዝም ብለን
የጀመርነው ውሸት ተጠናውቶ ይዞን
ማንነታችንን አምነን ለመቀበል በጣም ሲቸግረን
ከዚያም አልፎ ተርፎ ሰዎች ሲታዘቡን
የምንይዘውና የምንጨብጠው መላው ሲጠፋብን
ይበልጥ እየዋሸን ከእውነት እየራቅን
በአጉል ድርጊታችን ብዙ ገፍተንበት
ከሰዎች በማለፍ እራሳችንንም በጣም እያታለልን
ያለምንም ችግር መኖር እንችላለን የሚል አቋም ይዘን
ደፋ ቀና ብንል ውጤት አይኖረውም ይኸ ጥረታችን
ትዝብትና ቅሌት ይሆናል ትርፋችን
Leave a Reply