Tag: 1999

  • እህቴ (ታህሳስ 1999)

    ከቼርች እንደመጣሁ እሁድ ቀን ከስአት

    ከጓደኞቼ ጋር በጭቃ ስጫወት

    ጥሩ ቤት ሰርቼ እህቴን ባስቀናት

    እንደ እኔ ቆንጆ ቤት መሥራት ስለአቃታት

    በጣም ተበሳጭታ ምንም ሳላስበው

    ያን የመሰለ ቤት በእግሯ አፈረሰችው

    እኔም ተናድጄ በእሷ መጥፎ ድርጊት

    ተንደርድሬ ስሄድ በዱላ ልመታት

    አባቴ ስለአየኝ አለኝ እንዳትነጸት

    ምክሩን ተቀብዬ ስመለስ በፍጥነት

    እሷን ጠራትና እንዲህ ሲል መከራት

    በጣም ያሳፍራል ያጠፋሽው ጥፋት

    የሱን ቤት ማፍረስሽ ተነስተሽ በቅናት

    ከአንች አይጠበቅም የዚህ አይነት ድርጊት

    አሁንም ቶሎ በይ ይቅርታ ጠይቂው

    የዚህ አይነት ጥፋት አይለምደኝም በይው

    በመጸከላችሁ ሰላም የሚወርደው

    ጥፋተኛነትሽን ስተቀበይ ነው

  • ትምህርት፣ጨዋታ፣ እናት፣ ሳንቡሳ (ህዳር 1999)

    በጠዋት ማለዳ ቁርሴን እንደበላሁ

    ወደ ትምህርት ቤት በቶሎ እሄዳለሁ

    ከክፍል ስወጣ ጨርሼ ትምህርቴን

    እጫወተዋለሁ ያን ዥዋዥዌዬን

    ከቤቴ ስወጣ ጠዋት በማለዳ

    እናቴን አየሁዋት ውሀ ስትቀዳ

    ቁርስ ብላ ብላ ሰታቀርብልኝ

    ይህን ስላለችኝ እኔም ደስ አለኝ

    በጠዋት ማለዳ ከቤቴ ስወጣ

    እናቴን አየኋት ወደ እኔ ስትመጣ

    እንኳን መጣሽልኝ ብዬ ሄጄ ሳቅፋት

    እሷም በእኔ ድርጊት ደስታ ተሰማት

    ከዚያም ቀስ ብላ እጇን ስታሳየኝ

    ለጸስ ሳንቡሳ ነው የመጣች ይዛልኝ

  • ሆያ ሆዬ (ነሐሴ 1999)

    በዚያ ወጣትነት አፍላ ዘመናችን

    ከእኩዮቻችን ጋር አመት በአል ጠብቀን

    ብዙ ሳንደክም የገንዘብ ማግኛችን

    ሆያ ሆዬ ነበር ዋናው ጭፈራችን

    ስልቸት እስከሚለን መልሰን መላልሰን

    ስናንጎራጉረው ከቤት ቤት እየዞርን

    ያስደስተን ነበር የልጅ ድርጊታችን

    ከአመታት በኋላ በአዛውንት እድሜአችን

    ክፉም ደግም ጊዜ ሲፈራረቅ አይተን

    ምንም እንደማናውቅ ኑሮ እንዳልፈተነን

    የልጅነት ልማድ ተጠናውቶ ይዞን

    አሁንም እንደ ጥንት ልክ እንደ ዱሮአችን

    በነጋ በጠባ ሰው እስኪታዘበን

    ሆያ ሆዬ ብቻ ሆኗል ዘፈናችን

  • ፎቶግራፍ (ህዳር 1999)

    ትዝታን ሰንቆ እንዲያስቀምጥልን

    የህይወትን ጉዞ ቀጥ አርጎ እንዲያቆየን

    ታሪክ ለመዘከር እንዲያገለግለን

    የፎቶ ቴክኒክን ላበረከተልን

    ለዚያ ለተረሳው ባለውለታችን

    ለፈረንሳዩ ሰው ኒኤፒስ ለሚባለው

    በአዳም ዘር ስም ሁሉ ምስጋና ይድረሰው

    የዚህ ሰው ፈጠራ ይፋ ከሆነበት

    ይኸው ተቆጥረዋል ሁለት ምዕተአመተታት

    ረዥም በሆነው በዚህ የታሪክ ወቅት

    የፎቶ ቴክኒክን በጣም ያሻሻሉት

    ለአሁኑ ደረጃው እንዲደርስ ያበቁት

    በህይወት ያሉና እንዲሁም የሞቱት

    ምስጋና ይግባቸው ሁሉም ላደረጉት

    በዚህ በእኛ ዘመን ይህን ሁሉ እረስተን

    ያልሆንነውን መስለን መታየት እያሰብን

    የእራሳችን ምስል ታትሞ ሲሰጠን

    እኛን አይመስለንም ብለን እየዋሸን

    ጭራሽ በማናውቀው በሰው ሥራ ገብተን

    አስተያየት ስንሰጥ ምንም ቅር አይለን

    በፎቶ የምናየው ምስል ደስ ጸላለን

    ወይም ለመደበቅ የምንፈልገውን

    ቁልጭ አርጎ እንዳለ በግልጽ ጸሳየብን

    አልያም ያረጀን በእድሜአችን የገፋን

    ወይም በብስጭት በሀዘን የተጎዳን

    አድርጎ አቅርቦናል የሚል እምነት ጸለን

    እንዲያው በአጠቃላይ ፍፁም ጸልተስማማን

    የምንፈልገውን መሆን ጸልቻለልን

    እውነቱን እንዳለ መቀበል ሲገባን

    ፎቶው ጭራሽ እኛን አይመስለንም ብለን

    የዚህ አይነት አቋም ለምን እንደወሰድን

    ፎቶውን የሚያዩት ሰዎች እንዲያምኑልን

    መሰረት የሌለው ምክንያት ፍለጋ እንባዝናለን

    አንዴ ጸሜራውን ችግር እንዳለበት

    እስከ ዛሬ ድረስ አንዴ እንኳን በስህተት

    ጥሩ የሚባል ፎቶ እንዳልተነሳበት

    መረዳት እንደቻልን በቅርብ ከሚያውቁት

    በይፋ ስንለፍ ያለምንም ሀፍረት

    ሌላ ጊዜ ደግሞ ያንን ፎቶ አንሽውን

    ስሙን ስናጠፋው ከመሬት ተነስተን

    የሙያ ብቃቱን በተመለከተ ጥርጣሬ እንዳለን

    ጤነኛ ነው ብለን ፍፁም እንደማናምን

    ወይም ሆነ ብሎ ፎቶውን በተንኮል እንዳበላሸብን

    አሳማኝ የሆነ መረጃ እንዳገኘን

    እንዲሁ በድፍረት ስናወራ ፈጥረን

    ውስብስብ ችግር ውስጥ እንዘፈቃለን

    ያልሆንነውን መስለን መታየት ፈልገን

    በደንብ ሳናስበው እንደ ቀልድ ዝም ብለን

    የጀመርነው ውሸት ተጠናውቶ ይዞን

    ማንነታችንን አምነን ለመቀበል በጣም ሲቸግረን

    ከዚያም አልፎ ተርፎ ሰዎች ሲታዘቡን

    የምንይዘውና የምንጨብጠው መላው ሲጠፋብን

    ይበልጥ እየዋሸን ከእውነት እየራቅን

    በአጉል ድርጊታችን ብዙ ገፍተንበት

    ከሰዎች በማለፍ እራሳችንንም በጣም እያታለልን

    ያለምንም ችግር መኖር እንችላለን የሚል አቋም ይዘን

    ደፋ ቀና ብንል ውጤት አይኖረውም ይኸ ጥረታችን

    ትዝብትና ቅሌት ይሆናል ትርፋችን

  • ሰልባጅ (ህዳር 1999)

    ኑሮ እጅግ ተወዶ አልቀመስ ብሎን

    ጠግበን የምናድር አልመስል እያለን

    በጣም ስንጨነቅ ስለ እለት ጉርሳችን

    የሆዳችን አንሶ ልብሳችን ሲያልቅብን

    የምንጨብጠው የምንይዘው አጥተን

    ምን እንደምናደርግ ግራ ግብት ብሎን

    ወደድንም ጠላንም የምንበላውን ማስቀደም አለብን

    ሆዳችን ከሞላ መሄድ እንችላለን ቀዳዳ ልብስ ለብሰን

    ብለን በአዕምሮአችን ውሳኔ አሳልፈን

    ስለልብስ መጨነቅ እርግፍ አርገን ትተን

    ገቢያችንን ሁሉ ለምግብ እያዋልን

    በለመድነው መንገድ ስንጋፈጥ ኑሮን

    በቅርበት የሚያውቁን በአለባበሳችን ግራ የተጋቡት

    ለምን ብላችሁ ነው የተቀደደ ልብስ የምታዝወትሩት

    ከእብደት አይለይም እራቁትን መሄድ ሰልባጅ በሞላበት

    በዚህ ድርጊታችሁ ልታፍሩ ይገባል

    ያያችሁ ሰው ሁሉ ይታዘባችኋል

    አሁንም ፈጥናችሁ ሰልባጅ ልብስ ገዝታችሁ

    ልትለብሱ ይገባል በደንብ አጽድታችሁ

    ወደፊትም ቢሆን ልታውቁ የሚገባው

    በሰዎች እይታ የእናንተን ማንነት በደንብ የሚገልፀው

    አይነተኛው መስፈርት አለባበሳችሁ መሆኑን ማመን ነው

    ብለው ግልጽ የሆነ ምክር ለግሰውን

    በቀጣዩ ጊዜ ምክራቸውን ሁሉ ተግባር ላይ አውለን

    በጣም ተለውጠን ሊያዩን እንደሚሹ ደጋግመው ነግረውን

    በስተመጨረሻም ልንሰነባበት እንደተዘጋጀን

    በዚህ በምክራችን ቅር ከተሰኛችሁ ይቅርታ አደርጉልን

    እናንተን ለመጉዳት ሆን ብለን አስበን

    ያደረግነው ድርጊት እንዳልሆነ እመኑን

    ብለው ሲጨርሱ እኛም ቀበል አርገን

    በለገሱን ምክር እጅግ ደስ እንዳለን

    ውለታ ለመክፈል እግዜር ያብቃን ብለን

    ተሰናበትናቸው በጣም አመስግነን

    ከዚያም ለብቻችን ውይይት ጀምረን

    ብዙ ተከራክረን አውጥተን አውርደን

    የተሳሳተ አቋም ይዘን እንደቆየን

    አሁን ልንቀይረው ፈቃደኛ እንደሆንን

    በአንድ ድምጽ ወስነን ወደ ተግባር ገባን

    ከዚያ በኋላማ ምኑ ይነገራል

    ጠቅላላ ውሏችን ሰልባጅ ተራ ሆኗል

    ኮት እንዲሁም ሱሪ የሱፍ አይነቶችን

    ሸሚዝ ከ ክራቫት አብሮ የሚሄዱትን

    በአይነትና ከለር መርጠን እየገዛን

    በሳምንት ሁለቴ ስንለብስ እየቀየርን

    ተሸፋፈነና የቤታችን ችግር የውስጥ ገመናችን

    ጭራሽ መስለን ታየን ኑሮ የተስማማን

    ለሰዎች የምንተርፍ ከእራሳችን አልፈን

    በአይን እንኳን ለማየት ድሮ የሚፀየፉን

    ሰልባጅ ስለለበስን ሽር ጉድ ሲሉልን

    ለእራሳችን ጭምር በጣም እስኪገርመን

    በሄድንበት ሁሉ ልዩ ክብርና ሰላምታ ሲሰጡን

    በሰው ልጅ ከንቱነት እጅግ በጣም አዘን

  • እንቅልፍ እና ድሀ (ህዳር 1999)

    እንቅልፍና ድሀ ገ*ደኛሞች ናቸው

    በጣም የጠበቀ ትስስር አላቸው

    ተብሎ በሰዎች ዘንድ ሲወራ በሰፊው

    እንዴትና መቼ እንደተጀመረ ግንኙነታቸው

    ምን እንደሁ ምክንያቱ ለዚህ ቅርበታቸው

    ምላሽ እንዲሰጠኝ ከሁለቱ አንዳቸው

    ቶሎ የማገኘውን ወሰንኩ ልጠይቀው

    ከዚያም እንደገና የቱ ይሻል ይሆን ብዬ ሳሰላስል

    ሰዓቴን አየሁት በድንገት ዞር ስል

    ጊዜው በማለፉ ከሥራ መውጫችን

    ወደ ቤቴ ስሄድ ቆልፌ ቢሮዬን

    ጊዜ አልፈጀብኝም ሳገኘው ድሀውን

    ይህን አጋጣሚ ልጠቀም በማለት

    ፈቃዱ ከሆነ ከእኔ ጋር ለማውጋት

    ግራ የሚገባኝ ምላሽ ያጣሁለት

    ጥያቄ ስላለኝ እሱን አንስቼለት

    አመለጸከቱን የእሱን የግል እምነት

    ለመስማት መሻቴን እንደገለጽኩለት

    ይህን ከማለቴ ወዲያው ከመቅጽበት

    ማውራት እንችላለን በሙሉ ነፃነት

    ብሎ በሀሳቤ እንደተስማማበት ሲያረጋግጥልኝ

    ከልብ አመስግኜው እንዲህ ስል ጀመርኩኝ

    በዚህ በአገራችን ከታላላቆቹ እንደምንሰማው

    እንቅልፍና ድሀን የሚያቆራኛቸው

    ማንም የማያውቀው አንድ ሀይል እንዳለ ነው

    በህይወት ዘመኑ ድሀ የሚባል ሰው

    በፈለገው መጠን ሊያገኝ የሚችለው

    ከሁሉም ነገሮች እንቅልፍን ብቻ ነው

    እንዲያውም በቅርበት በደንብ ጸየነው

    አብዛኛው ህዝባችን ከልቡ የሚያምነው

    እንቅልፍ ባይኖር ኖሮ ድሀ እንደሚሞት ነው

    ይህ አመለጸከት እንዴት ነው የመጣው?

    በአንተ እምነት ይህ ጉዳይ እውነትነት አለው?

    ብዬ ጨረስኩና ስጠባበቅ መልሱን

    በድንገት አየሁት ስþለዋወጥ ፊቱን

    ያየሁት ሁኔታ በጣም አስድንግጦኝ ግራ ስለገባኝ

    ምን የሚያስቀይመው ነገር ተናገርኩኝ

    አሁንስ ቀጥዬ ምን ማድረግ አለብኝ

    ብዬ መላልሼ እራሴን ጠየኩኝ

    ከሀሳብ ጉዞዬ ስመለስ በድንገት

    ዞር ብዬ ሳየው ተረጋግቶ አየሁት

    ከዚያም እንዲህ አለኝ አይን አይኔን እያየኝ

    እውነቱን ከፈለግህ በጥሞና አድምጠኝ

    ብሎ ንግግሩን ቀጥሎ በስሜት

    በጣም ተመስጦ እንዲህ ሲል ሰማሁት

    ሰዎች በዘልማድ እንቅልፍና ድሀን የሚያገናኟቸው

    ዝም ብለው አይደለም በህልም ምክንያት ነው

    ድሀ ሰው በህልሙ ያቀደው በሙሉ የሚፈጸምለት

    በጣም ሀብታምና ኑሮ የሰመረለት

    ከደስታ በስተቀር ሐዘን የሌለበት

    በሽታና ችጋር ፍጹም የማያውቁት

    እንዲያው በአጠቃላይ ሁሌ የሚሳጸለት

    ተደርጎ እየታየ እንዲሁ በግምት

    በኑሮ ደረጃ ከእሱ ከተሻሉት ለይቶ በማየት

    ጥሩና መጥፎ ህልም እንደሚያይ በመርሳት

    የህልም አለም ደስታን ስለሚያላብሰው

    በጣም ይወደዋል እንቅልፍን ድሀ ሰው

    የሚለው አባባል መጥፎ መልዕክት አለው

    ይህ ሰው እንደሌላው ስሜት እንደሌለው

    ባዶ የህልም ተስፋ እንደሚያስደስተው

    ይቆይ እንደሁ እንጂ በህልሙ የሚያየው

    በእውን መፈፀሙ ፍጹም የማይቀር ነው

    የሚል የፀና እምነት ተብትቦ የያዘው

    መላ የጠፋበት ማሰብ የተሳነው

    የተለየ ፍጡር አድርጎ የማየት መሠረት የሌለው

    ትዕቢት የሞላበት የንቀት ስሜት ነው

    ሀቁ ግን ሌላ ነው በጥልቀት ጸየነው

    የተለየ ጥቅም ሲሰጥ አይታይም እንቅልፍ ለድሀ ሰው

    እንዲያውም በአንፃሩ በአጉል ተስፋ ሞልቶት

    ከገሀዱÜ አለም ጋር በጣም አራርቆት

    የኋላ የኋላ እወነቱን መጋፈጥ የግድ ሲሆንበት

    መዳረጉ አይቀርም ለፍርሀት ለጭንቀት

    ይኸ ነው ሚስጥሩ በእኔ አመለጸከት

    እንቅልፍና ድሀን በጣም ብዙ ሰዎች የሚያቆራኙበት

    ብሎ እንደጨረሰ በጣም አስግኜው በዚያው ተለየሁት