ቀይ ሽብር (ህዳር 1992)

በዚህ በእኛ ዘመን ጭጸኔና ትዕቢት በተንሰራፉበት

እንደ ትልቅ ነገር እየተወሰደ የሀሳብ ልዩነት

ለሰው ህይወት መጥፋት ይሆናል ምክንያት

የቅርብ ታሪጸችን እኛም ያለፍንበት

በደንብ ሲመረመር ሲፈተሸ በጥልቀት

ማመን ያስቸግራል እውነት ነው ለማለት

በሀምሳዎቹና ስልሳዎቹÜ አመታት

ያረጀውን ስርዓት በአዲስ በመተጸት

ሥር ነቀል የሆነ ወሳኝ ለውጥ ለማምጣት

መልጸም ምኞትና አገራዊ ራዕይ ይዞ በመነሳት

ሌት ተቀን ሲታገል የተማረው ወጣት

በሙሉ ልብና ፍጹም ቁርጠኝነት

ድብደባና እስራት ሳይበግረው ፍርሀት

በሁሉም አቅጣጫ ትግሉን አቀጣጥሎት

ህዝቡን በቅስቀሳ ለአመጽ አነሳስቶት

ከስር መሰረቱ ስርአቱን አናግቶት

የሚቀረው እድሜ በወራት ደረጃ በሚቆጠርበት

ልክ እንደ ዱብዕዳ ለውጡ ሳይታሰብ ተከስቶ ድንገት

አገሪቱን ባንዴ የለውጡ ማዕበል ጥልቅልቅ አድርገ*ት

ሁሉም ነገር ገና በደንብ ሳይለይለት

ህዝቡ ሲፈነድቅ ብሩህ ተስፋ ታይቶት

በጣም መጥፎ ወሬ ጀመረ መሰማት

ያንን ብሩህ ተስፋ ገደል ውስጥ የሚከት

ለውጡን ያመጣነው እኛ ነን በማለት

ከሠራዊቱ ውስጥ ተመርጠው የመጡት

ከዚያም ተሰባስበው ቡድን የፈጠሩት

ወጣት መኮንኖች ስልጣኑን ጠቅልለው ለብቻ ይዘውት

በጀመርነው መንገድ ለውጡን እንድንመራው በባለቤትነት

ታሪክ ጥሎብናል ታላቅ ኃላፊነት

መወጣት ያለብን ሌት ከቀን በመሥራት

አስፈላጊም ሲሆን በመክፈል መስዋዕት

ይህን ኃላፊነት አሳልፎ መስጠት

አይተናነስም አገርን ከመክዳት

የሚል መርህ ይዘው ቡድን በመለየት

ይፈጽሙ ጀመር ወሰን የለሽ ጥፋት

በያዙት አላማ በአቋማቸው ምክንያት

ሌሎችን ወገኖች በጅምላ መፈረጅ በፀረህዝብነት

ያም አልበቃ ብሎ በየምክንያቱ ማሠር ማንገላታት

ህዝብ እንዲጠላቸው ስማቸውን ማጥፋት

እንዲያው በአጠቃላይ ተቃዋሚዎችን የመበቀል ሂደት

ይታይ ነበረ እንደ ጥሩ ዘዴ ፍቱን የትግል ስልት

በጋራ ውይይት ችግሩን ለመፍታት

ብዙ ቢሞክሩም ገለልተኛ አጸላት

ሁለቱም ወገኖች እየደረደሩ ያልረባ ምክንያት

ወይም መጀመሪያ ከውይይት በፊት

መደረግ አለበት ብለው ያስቀመጡት

ቅድመ ሁኔታ ላይ ጠፍቶ ስምምነት

ጥረቱ ሲከሸፍ ቆይቷል በሂደት

ባለጊዜው ወገን ስልጣን በእጁ ያለው

እየቆየ ሲሄድ ስልጣኑ እየጣመው

ህይወቱን በሙሉ ለብቻው ሊይዘው

ተቀናቃኞችን የሚያስወግድበት

እቅድ አዘጋጅቶ ተግባራዊ ሊያደርግ ቆርጦ በመነሳት

ለሀቅ መቆማችን የሚታወቅበት

ጠላቶቻችንን አከናንበን ውርደት

እርቃን እንዲቆሙ የምናደርግበት

ቀይ ሽብር ነው ለእኛ ፍቱህኑ መድሀኒት

ብለው በመወሰን የተለየ አላማ ወይ አመለጸከት

ያላቸውን ሁሉ እስከመጨረሻው ከምድር ለማጥፋት

የእርስ በእርስ ጦርነት በገሀድ በመክፈት

በየመንገዱ ላይ ተው ባይ በሌለበት

ወጣቱን በግላጭ ሲያረግፉት በጥይት

ከዚያም እሬሳውን በጥይቱ ዋጋ ለወላጅ ሲሸጡት

ወገን በወገኑ እንዲህ ይጨክናል ብሎ ለመገመት

በጣም ያስቸግራል አምኖ ለመቀበል ድርጊቱን ላላዩት

ተቃዋሚው ወገን ይህ የሞት አደጋ ያነጣጠረበት

በዚህ ጽንፈኛ አቋም ግራ በመጋባት

የአልሞት ባይ ተጋዳይ ምላሹን በመስጠት

የሀይል ጥቃትን በሀይል ሲመክት

ከሁለቱም ወገን ጠፍቷል ብዙ ህይወት

ልዩነታቸውን በውይይት ብቻ ሲችሉ ለመፍታት

በዚያ በፈታኝ ወቅት ጎራ በመለየት

በሆነ ባልሆነው ሰንጸላ ምክንያት

ወገን የወገኑን ሲቀጥፍ እምቡጥ ህይወት

አይሰጠውም ነበር ምንም አይነት ስሜት

ይህ የታሪጸችን ትልቁ ጠባሳ መሆኑን ተረድተን

ዳግም እንዳይመጣ መጠንቀቅ አለብን

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *