ስዎች ሲናገሩ ታጋይ ነን እያሉ
የዚህን ቃል ትርጉም ጠንቅቀው ያውቃሉ
የሚል የፀና እምነት ሁሉም ሰው ስላለው
ስለፈፀሙት ጀብድ ወይም ድርጊታቸው
አስረዱን በማለት ቀርቦ የሚያዋያቸው
ብዙ ሰው አይደለም የሚጠይቃቸው
ታጋይ ለሚባሉት ህዝቡ ያለው ግምት
ሊሆኑ ይገባል ብሎ የሚያምንበት
ከእውነታው ጋራ ምንም የለው ቅርብት
ብዙ ታጋዮች ዘንድ ያለ አመለጸከት
የትግል አላማቸው ግቡን እንዲመታ ድሮ ላደረጉት
አሁን ያለድጸም ጥሩ ጥቅም ማግኘት
የፈለጉት ሁሉ እንዲሟላላቸው በተቻለ ፍጥነት
ወይም መቀበል ነው ጉርሻና ዳረጎት
የዚህ አይነት አቋም ፍጹም ግለኝነት
የትግል ተሳትፎን የጡረታ መብት
አድርጎ በማየት ሁሉን ለእኔ ማለት
አላማን የመሳት የዝቅጠት ምልክት
እንደሆነ ማወቅ በደንብ መረዳት
በጣም ይጠቅመናል እንዳንሠራ ስህተት
አስመሳይ ታጋዩን ለይተን ለማውጣት
ጊዜን ተከትሎ አቋም ከመቀየር
ጭራሹን ትግል ውስጥ ሳይገባ ቢቀር
ትዝብትና ንቀት ቢያንስ ስለሚያስቀር
በሁሉም ረገድ ያ ይመረጥ ነበር
ትግል ውስጥ ለመግባት ሰው ሲያደረግ ዝግጅት
ብዙ ውጣ ውረድ ደፋ ቀና ማለት
ደከመኝ ሳይሉ ያለምንም እረፍት
መሥራት እንደሚኖር በደንብ ተረድቶት
ሙሉ ቁርጠኝነት ማሳየት አለበት
ይህ ሲሆን ብቻ ነው የሚገኘው ውጤት
ማምጣት የሚቻለው ለአገር ፈጣን እድገት
አገራዊ ራዕይ ይዞ የሚራመድ
ግቡን ለማስፈጸም የሚሄድበት መንገድ
ብዙ መሰናክል ስለሚኖርበት
ያን ሁሉ ጠራርጎ በደንብ በማጥራት
በድል አድራጊነት በኩራት ለመውጣት
ህዝባዊ መሆኑ እንዲታወቅለት
ለይስሙላ ሳይሆን በሙሉ ሀቀኝነት
ግለኝነቱንም አሽቀንጥሮ ጥሎት
ለእኛ የሚል መርህ መቀበል አለበት
ተገቢው አጸሄድ መከተል ያለብን
ህዝብን ማገልገል ነው በሙሉ አቅማችን
ከዚህ መስመር ወጥተን ወለም ዘለም ማለት
ለአገርና ለህዝብ ያስከትላል ጉዳት