አላማው ተሳክቶ እቅዱ ሰምሮለት
ሰው እርጸታ ሲያገኝ በድጸሙ ውጤት
በውስጡ ተፈጥሮ እጅግ ልዩ ስሜት
ደስታውን ሲያበስር በየደረሰበት
ለሚያውቁትም ሆነ ለሚቀርቡት እሱን
እንኳን ደስ አላችሁ ደስ ብሎኛል እኔን
ብሎ በመፈንደቅ ሲገልፅ ስሜቱን
መስሎ ይታየዋል ሁሉም የሚታመን
ደስታውን ተጸፍሎ የሚቆም ከእሱ ጎን
የእሱ ደስታ ሀዘን የሚፈጥርባቸው
ወይም የእሱ ውጤት የሚያበሳጫቸው
ይኖራሉ ብሎ ፍፁም ስለማያምን
ይጋብዛቸዋል ወዳጅ ጓደኞቹን
ብዙ ሳይሰነብት ወዲያው በዚያው ሰሞን
በደንብ አጣጥሞ ሳይጨርስ ደስታውን
መስማት ይጀምራል አስቀያሚ ወሬ የሚንድ እምነቱን
አንዳንድ የሚያውቃቸው በደንብ የሚቀርቡት
በቅናት ተገፍተው እነደተነሱበት
ስራውን ማንቋሸሽ እንደተያያዙት
ሰዎች ሲገልፁለት ስለድርጊታቸው
ማወቅ ይቸገራል ምን እንደታያቸው
ወይ ምን እንደሆነ ዋናው አላማቸው
በደንብ ላስተዋለው በጥሞና ላየው
ይህን የሚያደርጉት በተራ ቅናት ነው
ለምን ተደሰተ እንዴት ተሳጸለት
ለኛ ሳይሆንልን ለእሱ እንዴት ሆነለት
እኛ እናውቀዋለን ይህን እሱ አልሰራም
በምንም መስፈርቱ እሱ ከእኛ አይበልጥም
ሊሸለምም ሆነ ወይም ሊመሰገን ፍፁም አይገባም
በሚል መጥፎ ስሜት ተራ ምቀኝነት
እየተገፋፋ የውስጥ ስሜቱን ስብእናውን መጉዳት
ይህ አልበቃ ብሎ ተራ ወሬ ማውራት
በሆነ ባልሆነው ጥሩ ስሙን ማጥፋት
እንዲያው በአጠቃላይ ሊያጠፉት መነሳት
በሁሉም አቅጣጫ ለእኩይ ተግባር መዝመት
ምን ሊባል ይቻላል የዚህ አይነት ድርጊት
ሰውን ጥምድ ማድረግ ስላገኘ ብቻ በስራው ላይ ውጤት
አይዞህ በርታ ቀጥል እንደማለት ፋንታ
ሰውን እንደማድነቅ ባሳየው ችሎታ
አሁን ምን ይጠቅማል የወሬ ጋጋታ
የሃሰት ውንጀላ ተራ ምቀኝነት
ስም የማጉደፍ ተግባር የፈጠራ ድርጊት
ያስከትላልና በጣም ብዙ ጉዳት
መወገድ አለበት በተቻለ ፍጥነት
ፈፅሞ እንደþጠፋ ተራ ምቀኝት
የሰዎች ችሎታ የሚመዘንበት
ውጤታማ መሆን የስራ ላይ ብቃት
ሊሆን ይገባዋል አይነተኛው መስፈርት
Leave a Reply