ስሜቱ ገፋፍቶት በቶሎ ለመርጸት
ፍቅርን ከገበያ በገንዘብ ለመግዛት
የሚባዝን አለ ብዙ የሚንከራተት
ሰው እንዳያውቅበት ሚስጥሩ አንዳይባክን
ተገን ያደርግና ውድቅት ጨለማን
ፍቅር ለመሸመት ይወጣል ብቻውን
የፍቅርን ገበያ ከሩቅ ሲመለከት
ያለውን ትርምስምስ የሸማቹን ብዛት
ወዲያው ይጀምራል በስሜት መመራት
ፈጥኖ በመራመድ ጠጋ ብሎ ቀርቦ ገበያውን ሲቃኝ
መቅበጥበጥ ያበዛል መመልከት ግራ ቀኝ
በማለት መጨነቅ ሰው አየኝ አላየኝ
ብዙ አውጥቶ አውርዶ ፀንቶ በውሳኔው
ፍቅርን ለመሸመት ይቀጥላል ጉዞው
በፍጥነት እርምጃ ዘው ብሎ ሲገባ ከፍቅር ገበያው
የደራው ገበያ አፉን የከፈተው
በአዲሱ ደንበኛ ደስታ የተሰማው
ማቅረብ ይጀምራል ሞቅ ያለ አቀባበል
በጊዜያዊ ደስታ ሸማቹን ማታለል
አይዞህ ድፈር ማለት ደገጋግሞ መደለል
የያዘውን ገንዘብ ለማጥፋት እንዲችል
በጣም የተሳበው በዚህ አቀባበል
ፍቅር ገዥው ጀግና በስሜት ይሞላል
ከዚያም በመቀጠል ፍርሀቱን ለማጥፋት
ወዲያው ይጀምራል አልኮሉን መጎንጨት
ገበያውን ማየት ቀኝ እና ግራውን
በፍቅር እቃዎች ጭንቅንቅ ያለውን
አምረው ተኳኩለው አጊጠው አፍጥጠው
የሸማቹን መምጣት የሚጠባበቁት ወንበር ላይ ቁጭ ብለው
የፍቅር እቃዎች የስሜት ማርኪያዎች
ፍፁም ያልታደሉት ከርታታ ከንቱዎች
ይጠቃቀሳሉ እርስ በራሳቸው
ስለአዲሱ እንግዳ ስለሚቃኛቸው
ጭራሽ ባለማወቅ ማንን እንደሚመርጥ ከመጸከላቸው
በሚያደርጉት ድርጊት ግራ የተጋባው
ፍቅርን ለመሸመት ቆርጦ የተነሳው
በድፍረት ሲሞላ ደጋግሞ መጠጡን
መምረጥ ይጀምራል የፍቅር እቃውን
ቅፅበታዊ ደስታ የምትሸጥለትን
ከጎኑ አስቀምጦ ከመጸከላቸው መርጦ ያወጣትን
እየደባበሰ ፀጉር እና ገላዋን
ወደድኩሽ ይላታል ከዛሬ ቀን በፊት አይቶ የማያውቃትን
ይሉኝታ ረስቶ በመጠጡ ብዛት
ሲዳራ ሲተሻሽ ያለ ምንም ፍርሀት
የወንድነት ስሜት ገፍቶ ሲመጣበት
ትውስ ይለውና ያ ያለበት ቦታ የተቀመጠበት
ፍቅር በገንዘብ ሃይል የሚታፈስበት
የፍቅር እቃዋን አይን አይኗን እያያት
ስንት ልክፈል ይላል ሌሊቱን በሙሉ ለማሳለፍ አብሯት
ድርድሩ አብቅቶ ሲስማሙ በዋጋ
ለማደር ወስኖ ይከራያል አልጋ
እየመሸ ሲሄድ ድክምክም ሲለው
ሂሳቡን ከፋፍሎ ይሄዳል ወደ አልጋው
ትእዘዛዝ ይሰጥነና ያ‚ የፍቅር እቃ እንድትከተለው
ይህን ስትሰማ ወዲያው ከመቅስበት
ትጠይቀዋለች ሂሳብ እንዲሰጣት
የስሜት ማርኪያውን የፍቅር ዋጋውን
ቆጥሮ ይሰጣታል የተስማሙበትን
ገንዘብ አገናኝቶ አፋቅሮ አዋዷቸው
ሌሊቱን ተቃቅፈው አብረው አሳልፈው
ሁለቱም ተነስተው ይሄዳሉ ጠዋት ወደየፊናቸው
ፍቅርን የሸመተው ያ ብቸኛ ወጣት
ሮጦ ይወጣል ከዚያ ጸደረበት
ፍፁም ባለማወቅ የሸመተውን ነገር ደስታ ይሁን ፀፀት