የሰው ልጅ ተፈጥሮ ይላል ግራ ግብት
የመበቀል ስሜት ይዞ በመነሳት
የራሱን ደብቆ ያለበትን ድክመት
ሲያጋንን ይታያል የሌሎችን ጥፋት
የሱን ጥፋት ሰዎች አያውቁትም በሚል
ቃሉን የሚያከብር ፍፁም የማያብል
ስህተት የማይሰራ ሰው የማያታልል
ንፁህ ሰው አድርጎ እራሱን ያቀርባል
ያልሆነውን ሆኖ መታየት ሲጀምር
የእውነት ማንነቱን ያደርገዋል ሚስጥር
ከዚያም በሙሉ ልብ ያለ ምንም ስጋት
ስራው ያደርገዋል የሌሎችን ጥፋት መፈለግ በመብራት
በማነፋነፍ ብዛት ሲያገኝ ትንሽ ስህተት
የሆነ ያልሆነውን ጨማምሮ በማውራት
ሰዎችን መወንጀል ስማቸውን ማጥፋት
ያጎናፅፈዋል ልዩ የእርጸታ ስሜት
አእምሮው ተጋርዶ በራስ መውደድ ብዛት
ምንም አይመስለውም የሚያደርገው ድርጊት
አርቆ ለማሰብ ፍፁም ስለማይችል
በጭጸኔ መንፈስ ብዙ ሰው ይጎዳል
በልቡ እያወቀው የራሱን ማንነት
ፍፁም እንዳልሆነ በሚያደርገው ድርጊት
ሰው በሰውነቱ ጥፋት እንዳለበት
ለምን ይሳነዋል አዙሮ መመልከት
እራሱን መጠየቅ እኔ ማነኝ ማለት
ፈልጎ ለማግኘት የሰዎችን ጥፋት
ወይም ለመወንጀል ታጥቆ ከመነሳት
ሊቀድም ይገባል አስተውሎ ማየት
እራስን ፈትሾ በደንብ መረዳት
እኔ ምን አጠፋው ሌሎችስ ምን ሰሩ
ብሎ በጥሞና በደንብ መመርመሩ
ተገቢ ነገር ነው ከስህተት የሚያድን
በስሜት ተገፍቶ ከመወንጀል ሰውን
Leave a Reply