በጋራ ጉዳይ ላይ ሰዎች ተገናኝተው
ውይይት ሲያደርጉ ጊዚያቸውን ወስደው
የሚመስላቸውን አስተያየት ሰጥተው
ጠቃሚ ያሉትን ሀሳብ ተለዋውጠው
ተግባብተውም ይሁን በአቋም ተለያይተው
ቁም ነገር ላይ ብቻ ውይይት አድርገው
በመሰነባበት ይሄዳሉ ማለት ወደየፊናቸው
የሰውን ተፈጥሮ ጭራሽ ያለማወቅ ያለመረዳት ነው
የአብዛኛውን ህዝብ ልምድ ስንፈትሽ በጥልቀት
ሰዎች ተሰባስበው ሲያደርጉ ውይይት
በውይይቱ ወቅት ስለሌሉ ሰዎች በመጸከላቸው
ግን ስለሚያውቋቸው ከዚያ ቀደም ብለው
ስለባህርያቸው ወይም ድርጊታቸው
አንስተው መቆዘም የተለመደ ነው
በጣም የሚገርመው ግራ የሚያጋባው
ሰዎች ስለ ሰዎች የሚወራላቸው
ምንጩ ከየት እንደሁ ሳይነገራቸው
ወይም ሀሰት ይሆን የሚል ጥርጣሬ ፍጹም ሳይገባቸው
የሰሙትን ሁሉ እንደ እውነት ወስደው
ለሌሎች ላልሰሙት ማሰማታቸው ነው
ምንም ሳያጣሩ ስለ ሰዎች ማውራት
አዲስ መጠሪያ ሥም ማውጣትና መስጠት
እንዲሁ በጅምላ በጥልቀት ሳያዩÜት
መረጃ ሳይዙ ገለልተኛ ሆነው ቀርበው ሳያጠኑት
በጭምጭምታ ብቻ ከሰዎች በሰሙት
የተነገራቸው እውነት ይሁን ሀሰት
ሳያረጋግጡ ተገፍው በስሜት
ሰዎችን መፈረጅ በጥፋተኝነት
ሌላ ስም የለውም የዚህ አይነት ድርጊት
ሀሜት እንደሆነ መታወቅ አለበት
ሀሜትን ከስድብ ለየት የሚያደርገው
የሚታሙት ሰዎች ከፊት ለፊታቸው
ማየት የሚችሉት ቅር የሚያሰኛቸው
ምንም ነገር የለም የሚያስቀይማቸው
ድርጊቶችን ሁሉ በደንብ ስናያቸው
ሁሉም የሚሆኑት አፈጻጸማቸው
ከእነሱ እውቅና ውጭ ከበስተጀርባ ነው
በእነሱ ጉዳይ ላይ ሌሎች ሲመክሩበት
አስተያየት እንኳን መስጠት እንዳይችሉ ጭራሽ በሌሉበት
ዕድል ሳያገኙ እውነቱን በዝርዝር በግልጽ ለማሰረዳት
ወይም ከሳሻቸው ማን እንደሁ ሳያውቁት
መጥፎ ተግባራትን ፈጽመዋል ማለት
እያብጠለጠሉ በመጥፎ ድርጊቶች ስማቸውን ማንሳት
በማያውቁት ነገር ቁም ስቅል ማሳየት
ሰድቦ ለሰዳቢ አሳልፎ መስጠት
ስለሚያከናንብ ጭንቀትና ሃፍረት
በጣም ይጎዳዋል የሰዎችን ስሜት
አስፈላጊው እርምት ጸልተደረገበት
በማመሰቃቀል የሰዎችን ህይወት
ሊያስከትል ይችላል ከፍተኛ ጉዳት
ስለዚህ ሁላችን ይህን ተገንዝበን
ሀሜት መጥፎ ልማድ መሆኑን በማመን
በተቻለን አቅም መዋጋት አለብን
Leave a Reply