Category: 1997

  • ዳዊት (ሐምሌ 1997)

    ያ ዳዊት መንግስቱ የጅጅጋው ወጣት

    ፍቅር አይነጸኝም ብሎ ባወራበት

    በዚያው በምላሱ ሴት ሲለምንበት

    በጣም ያስደስታል ሲያለቅስ መመልከት

    የተናገረውን ጭራሹን ረስቶት

    ህይወቱን ከሴት ጋር ይኸው አቆራኝቶት

    ብሞት ይሻለኛል ሰላምን ከማጣት

    እያለ ያወራል ያለምንም ሀፍረት

    ቋንቋው ተቀይሮ ሰላም ብቻ ሆኗል

    ዘመድ መጠየቁን ጭራሹን አቁሟል

    በስልክ እንዳይገኝ ስልኩ እየደወለ ዝም ብሎ ያየዋል

    እሷ ስትደውል ቶኑን ይለየዋል

    ሮጦ ተነስቶ ቶሎ ያነሳዋል

    የእሷን ድምጽ መስማት ደስታ ይሰጠዋል

    ቶሎ ነይ እኔ ጋ እያለ ደጋግሞ ግብዣውን ያቀርባል

    እንዲያው በአጠቃላይ እጁን ለእሷ ሰጥቷል

    ይህ አዲስ ፀባዩ ማንም የማያውቀው

    ወዳጅ ዘመዶቹን ምንም ቢገርማቸው

    ለእሱ የጠበቀ ፍቅር ስላላቸው

    ይለምኑለታል ፈጣሪን ደጋግመው

    ሁለቱን ፍቅረኞች እንዲባርጸቸው

    በትዳር ሰንሰለት እንዲያቆራኛቸው

    ሁሉም የሚያውቀው ሰው ለእሱ የሚመኝለት

    ልቡን የሰወረው ይህ የፍቅር ህይወት

    በደንብ የሚያረጸው ደስታ የሚያስገኝለት

    ምንም አይነት ችግር የማያመጣበት

    ፍላጎቱ ሁሉ የሚፈፀምበት

    ወልዶ የሚስምበት ሰላም የሞላበት

    እንዲሆንለት ነው ጥሩ የሚባል ህይወት

    ከ ወ/ሮ ሜላት መንግስቱ እና ከ ፕ/ር በላይ ጸሣ

  • የትምህርት ቤት ትዝታ (ታህሳስ 1997)

    በአፍላ ወጣትነት በአስራዎቹ አመታት

    የኑሮን ሚስጥሮች በደንብ ለመረዳት

    በቂ ጠቅላላ እውቀት ወይ የአዕምሮ ብስለት

    ሳይኖረን እንዲሁ ትንሽ በምናውቃት

    በእንጭጭ አስተሳሰብ በጣም በመኩራራት

    ለእራሳችን ሰጥተን እጅግ ትልቅ ግምት

    በጣም አዋቂዎች መስለን ለመታየት

    ልማዳችን ነበር ደፋ ቀና ማለት

    ጥቅሙ ባይገባንም በወላጆች ግፊት

    ግዴታ ሆኖብን ስንሄድ ትምህርት ቤት

    አንዱ አመት ያልፍና ሲተጸው ሌላ አመት

    ነፍስ እያወቅን መጥተን እያጸበትን እውቀት

    የሃይ እስኩል ትምህርት የምንጨርስበት

    የእውቀት አድማሳችን የሚመዘንበት

    ወደፊት ሊኖረን የሚችለው ህይወት

    እንዲያው በአጠቃላይ እጣና ፋንታችን ፈር የሚይዝበት

    ወሳኝ የሆነው ወቅት ደርሶብን በሂደት

    የመጨረሻውን ፈተና ለመውሰድ ስናደርግ ዝግጅት

    ክፍል ገ*ደኛሞች አብሮ አደግ የሆነው

    አንድ ላይ በመሆን አብረን የምንቆየው

    ፈተና እስክንጨርስ መሆኑን ሳናውቀው

    በፈተና ማግስት እንደ ቀልድ እንዲሁ ሳንሰነባበት

    ውጤት እስኪወጣ ከወላጅ ዘመድ ጋር አብረን ለመቆየት

    በሁሉም አቅጣጫ ወደየቀያችን ቀጥታ በማምራት

    የፈተናን ጭንቀት እርግፍ አርገን ትተን ስንጀምር እረፍት

    ያች መለያያችን በፈተና ማግስት የዋለችዋ ቀን

    ለተወሰን ሰዎች ከመጸከላችን በአጸል ተገናኝተን

    መጥፎ ይሁን ጥሩ ማውጋት እንዳንችል ስለትዝታችን

    የመጨረሻችን ትሆናለች ብለን

    በህልም አናስብም ይቅርና በእውን

  • ሰውና ኑሮው (ነሐሴ 1997)

    ረቂቅ ሥራውን አምላክ ያሳየበት

    ሰውን ከእራሱ ጋር አመሳስሎ ፈጥሮት

    ፍጡራን በሙሉ ለእሱ እንዲታዘዙት

    በኑሮው ሂደት ውስጥ ብዙ ሁኔታዎች ሲፈራረቁበት

    መራራት መፀፀት መታገስ መደሰት

    መጨከን መከፋት ማዘን መበሳጨት

    ሌሎች ልዩ ልዩ የሆኑ ስሜቶች እንዲፈጠሩበት

    ጥሩውን ከመጥፎ ለይቶ እንዲያውቅበት

    ከሁሉም የላቀ አዕምሮ እንዲኖረው

    የሰውን ልጅ ልዩ አርጎ መፍጠሩ ነው

    ከወላጆቹ አብራክ አምላክ መርጦ ፈጥሮት

    እድገቱን ሲጨርስ አልፎ ከጽንስነት

    የእናቱን መሀፀን ለቆ የሚወጣበት

    አለምን ፊት ለፊት የሚጋፈጥበት

    ጊዜው መዳረሱን የሚገልጽ ምልክት

    መታየት ሲጀምር ወዲያው ከመቅጽበት

    ያን ጊዚያዊ ቤቱን ፈጥኖ ተሰናብቶት

    ጉዞውን ጀምሮ ወደ ውጭ ለመውጣት

    ይችን አለም ገና ብቅ ብሎ ሲያያት

    ሁሉም ሁኔታዎች ከተመቻቹበት

    ተሰናብቶ ትቶት ከመጣው ቤቱ ጋር እያነፃፀራት

    በፍርሀት ተውጦ መመለስ ሲያቅተው ወደነበረበት

    ያለውድ በግድ መውጣት እንዳለበት ግልጽ ሲሆንለት

    ብዙ ፈተናዎች እንደሚጠብቁት አስቀድሞ ታይቶት

    ምርር ብሎ አልቅሶ አለም መጣሁልሽ ተቀበይኝ ሲላት

    እሷም ፈጠን ብላ መልስ ስትመልስለት

    ምክር ወይም ቁጣ ብሎ ለመለየት በጣም የሚያዳግት

    በአንፃሩ ግን ደግሞ ጠቃሚ የሆነ ትምህርት የሞላበት

    መልዕክት እንደያዘ ይቻላል መረዳት

    እማራጭ የለህም ዝም በልና ውጣ

    ምኑንም ሳታየው እንዲሁ አትንጣጣ

    ወደፊት ሲገባህ እንዴት እንደሚከብድ ኑሮ የሚባል ጣጣ

    ድጸምህ ልፋትህ ምንም ዋጋ ሲያጣ

    ያኔ ምንም አይደል እርምህን ብታወጣ

    ስለዚህ ዝም በል አሁን ማልቀስ ይብቃህ

    ጊዜ ሳታጠፋ ቶሎ ፈጠን ብለህ

    የማይቀር ነውና ከአዲሱ ኑሮህ ጋር መላመድ አለብህ

    ምክሬን ከሰማኸኝ እኔ የምነግርህ

    ፈተናና ችግር ፈጽሞ እንዳይፈታህ

    ትግፅስትና ተስፋን አድርገህ መመሪያህ

    ጠንክረህ በርትተህ መሥራት ነው ያለብህ

    ይኸ ነው ባጭሩ ማድረግ የሚገባህ

    የሚል ጠለቅ ያለ ምክር የበዛበት

    ሞቅ ያለ አቀባበል ስትዘረጋለት

    ይህ አዲስ ሁኔታ ቀልቡን በጣም ስቦት

    ምኑንም ሳላውቀው የለብኝም መፍራት

    ጥሩ ነገሮች ነው እስከ አሁን ያየሁት

    ስለዚህ ከአሁኑ ተስፋዬን አልቆርጥም ስለመጪው ህይወት

    ጭራሽ መጥፎ ብቻ አይሆንም በእኔ እምነት

    ያም ሆኖ አልቸኩልም እንዲህ ነው ለማለት

    እጠባበቃለሁ ሁሉንም በትግዕስት

    ብሎ ይጋፈጠዋል ያን አዲሱን ህይወት

    ጊዜ የሚያመጣውን በሂደት ለማየት

  • ሀሜት (ሐምሌ 1997)

    በጋራ ጉዳይ ላይ ሰዎች ተገናኝተው

    ውይይት ሲያደርጉ ጊዚያቸውን ወስደው

    የሚመስላቸውን አስተያየት ሰጥተው

    ጠቃሚ ያሉትን ሀሳብ ተለዋውጠው

    ተግባብተውም ይሁን በአቋም ተለያይተው

    ቁም ነገር ላይ ብቻ ውይይት አድርገው

    በመሰነባበት ይሄዳሉ ማለት ወደየፊናቸው

    የሰውን ተፈጥሮ ጭራሽ ያለማወቅ ያለመረዳት ነው

    የአብዛኛውን ህዝብ ልምድ ስንፈትሽ በጥልቀት

    ሰዎች ተሰባስበው ሲያደርጉ ውይይት

    በውይይቱ ወቅት ስለሌሉ ሰዎች በመጸከላቸው

    ግን ስለሚያውቋቸው ከዚያ ቀደም ብለው

    ስለባህርያቸው ወይም ድርጊታቸው

    አንስተው መቆዘም የተለመደ ነው

    በጣም የሚገርመው ግራ የሚያጋባው

    ሰዎች ስለ ሰዎች የሚወራላቸው

    ምንጩ ከየት እንደሁ ሳይነገራቸው

    ወይም ሀሰት ይሆን የሚል ጥርጣሬ ፍጹም ሳይገባቸው

    የሰሙትን ሁሉ እንደ እውነት ወስደው

    ለሌሎች ላልሰሙት ማሰማታቸው ነው

    ምንም ሳያጣሩ ስለ ሰዎች ማውራት

    አዲስ መጠሪያ ሥም ማውጣትና መስጠት

    እንዲሁ በጅምላ በጥልቀት ሳያዩÜት

    መረጃ ሳይዙ ገለልተኛ ሆነው ቀርበው ሳያጠኑት

    በጭምጭምታ ብቻ ከሰዎች በሰሙት

    የተነገራቸው እውነት ይሁን ሀሰት

    ሳያረጋግጡ ተገፍው በስሜት

    ሰዎችን መፈረጅ በጥፋተኝነት

    ሌላ ስም የለውም የዚህ አይነት ድርጊት

    ሀሜት እንደሆነ መታወቅ አለበት

    ሀሜትን ከስድብ ለየት የሚያደርገው

    የሚታሙት ሰዎች ከፊት ለፊታቸው

    ማየት የሚችሉት ቅር የሚያሰኛቸው

    ምንም ነገር የለም የሚያስቀይማቸው

    ድርጊቶችን ሁሉ በደንብ ስናያቸው

    ሁሉም የሚሆኑት አፈጻጸማቸው

    ከእነሱ እውቅና ውጭ ከበስተጀርባ ነው

    በእነሱ ጉዳይ ላይ ሌሎች ሲመክሩበት

    አስተያየት እንኳን መስጠት እንዳይችሉ ጭራሽ በሌሉበት

    ዕድል ሳያገኙ እውነቱን በዝርዝር በግልጽ ለማሰረዳት

    ወይም ከሳሻቸው ማን እንደሁ ሳያውቁት

    መጥፎ ተግባራትን ፈጽመዋል ማለት

    እያብጠለጠሉ በመጥፎ ድርጊቶች ስማቸውን ማንሳት

    በማያውቁት ነገር ቁም ስቅል ማሳየት

    ሰድቦ ለሰዳቢ አሳልፎ መስጠት

    ስለሚያከናንብ ጭንቀትና ሃፍረት

    በጣም ይጎዳዋል የሰዎችን ስሜት

    አስፈላጊው እርምት ጸልተደረገበት

    በማመሰቃቀል የሰዎችን ህይወት

    ሊያስከትል ይችላል ከፍተኛ ጉዳት

    ስለዚህ ሁላችን ይህን ተገንዝበን

    ሀሜት መጥፎ ልማድ መሆኑን በማመን

    በተቻለን አቅም መዋጋት አለብን

  • ሠፈራ (ጥቅምት 1997)

    የችጋር የጠኔ የሰፈራ ጣጣ

    አሁንም እንደ አዲስ እንደገና መጣ

    ድርቅ ርሃብን ወልዶ የሚበላ ጠፍቶ

    ሰው ተስፋው ሲጨልም ወገን ደራሽ አጥቶ

    በመሸነፍ ስሜት እጁን ለሞት ሰጥቶ

    ቀስ በቀስ ሲደክም ርሃቡ ጠንቶበት

    የወደፊት እጣው ሲደበዝዝበት

    ህይወቱን የሚያድን መፍትሄ ሲቀርብለት

    ምንም ሳይመዝነው ሳያየው በጥልቀት

    ተቀበልኩት ይላል ትንሽ ለመሰንበት ባደረበት ጉጉት

    ብቸኛው አማራጭ ለማትረፍ ህይወቱን

    መሆኑን ሲረዳ ቶሎ ለቆ መሄድ ቀየውን መንደሩን

    ከዚያም ሌላ ቦታ ሄዶ ራስን ማስፈር

    በማያውቁት አገር አዲስ ኑሮን መኖር

    ምን እንደሚሻለው ግራ በመጋባት

    ከዚህ ልሂድ እና ህይውቴን ላትርፋት?

    ወይስ ልቆይና እዚሁ አገር ልሙት
    በማለት ደጋግሞ እራሱን ጠይቆ

    ባማራጮች መጥበብ ከልብ ተጨንቆ

    በሃሳብ ባህር ውስጥ ስጥም ብሎ ጠልቆ

    አልታይህ ሲለው ምን እንደሚያዋጣው

    ከእንቅልፉ እንደነቃ እንደባነነ ሰው

    እየተወራጨ ተውጦ በፍርሃት

    ክርክር ይይዛል ከራሱ ጋር ሙግት

    ለመሄድ ብወስን መድረሻዬ የት ነው

    ከዚህ መሻሉንስ እንዴት ነው የማውቀው

    ስለዚህ ይቅርብኝ እዚህ እቆያለሁ

    መሞት ጸለብኝም የማይቀር ነውና እዚሁ በፀጋ እቀበለዋለሁ

    ብሎ ብዙ ሳይቆይ ለውጦ ሃሳቡን

    አሁን ለምን ልሙት መሰንበት እየቻልኩ ማቆየት ህይወቴን

    በቃ ቆርጫለሁ ልሂድ ሃገር ጥዬ

    ከመሞት መሰንበት ይሻለኛል ብዬ

    ይህ አዲስ ውሳኔው አላረጸህ ሲለው

    ማሰብ ማሰላሰል ይጀምራል ወዲያው

    ምን እንደሚመስል የወደፊት ኑሮው

    በማያውቀው ሃገር ስለሚያጋጥመው

    በዚህ አይነት መንገድ ሲቀይር አቋሙን

    መልሶ መላልሶ ሲሽር ውሳኔውን

    ከዚያም እንደገና ሲጠይቅ እራሱን

    ባቋሙ ለመፅናት ማድረግ ያለበትን

    ይህን ሁሉ አድርጎ ሲሳነው መወሰን

    ከልብ የሚያምነውን ጋሻ መከታውን

    ማማረር ይይዛል ሃያል ፈጣሪውን

    በግልፅ ይነግረዋል ጠቅላላ ብሶቱን

    ከቶ ለምንድነው እንዲህ መጨከንህ

    ምነው እረሳኸን በዘዛብን ፈተነናህ

    አንተም እንደ ሰው ልጅ አድልኦ ታውቃለህ

    ወይስ እኛን ብቻ መከራና ስቃይ ይችላሉ ብለህ

    የችግር አውድማ ልታደርገን አሰብህ?

    በረሃብ ተሰቃይተን አማቀን እንዳንሞት

    እኛን ለመታደግ ከችግር ለማውጣት

    ከአቅምህ በላይ ሆኖ እንዳላስቸገረህ

    ምስክር ነውና ተአምራዊ ሃይልህ

    በረሃብ ስንረግፍ ታዛቢ መሆንህ

    ፍፁም አልገባኝም ምንድነው ሚስጥርህ

    ፍጣሪን ተጋፋህ ተዳፈርክ ባይሉኝ

    ስላንተ ማንነት መረዳት አቃተኝ

    ሁሉን እየቃኘህ እያየህ በእኩል አይን

    ረሃብ ሲጨርሰው አምሳያ ፍጡርህን

    ዝም ብለህ ታያለህ ብዬ ስለማላምን

    እጠራጠራለሁ በእውነት መኖርህን

  • ድብቅ ፍቅር (ሰኔ 1997)

    ሰው አየኝ አላየኝ ተብሎ በማመንታት

    በሚስጥር ተይዞ ሌሎች እንዳያውቁት

    የሚጀመር ፍቅር ስሜትን ለማርጸት

    ውሎ አድሮ ሥር ሰዶ በጣም ስþደላደል

    በሁለቱም ወገን መላመድ ያመጣል

    ይህን ግንኙነት እንዴት እንደሚያዩት

    ወደፊት ምን መምሰል እንደሚኖርበት

    ሁለቱ ፍቅረኞች በደንብ መክረውበት

    ጥሩ ነው የሚሉት የማይቀያይሩት

    አቋም ይይዛሉ ከልብ የሚያምኑበት

    ገሀድ እንዳይወጣ የፍቅር ህይውታቸው

    በሚስጥር ለመያዝ ምለው ተገዝተው

    ይቀጥሉበታል ከሰው ተደብቀው

    ጥርጣሬ ገብቶት ለሚጠይቃቸው

    የዚህ አይነት ቅርበት በመጸከላቸው

    ፍጹም እንደሌለ ሲገልጹ ደጋግመው

    የሚያውቁት ሰው ሁሉ አምኖ እንዲቀበለው

    ማድረግ እንችላለን ብለው በማሰብ ነው

    ጊዜ ጊዜን ወልዶ ሲነጉድ በፍጥነት

    ሳምንታት ተቆጥረው ሲተኩ በወራት

    ድብቅ ፍቅረኞቹ በጣም ተቀራርበው

    ከመቼውም ይበልጥ ደስተኞች ሆነው

    ነፋስ እንዳይገባው ግንኙነታቸው

    ምክንያት እንዳይኖር የሚለያያቸው

    እክል እንዳይገጥመው የፍቅር ህይውታቸው

    ወይም ለሎች ሰዎች አውቀው ችግር ፈጥረው

    ጠብ እንዳይነሳ በመጸከላቸው

    ይጠባበቃሉ በተጠንቀቅ ቆመው

    ድብቁ ፍቅራቸው በሚስጥር የያዙት

    አድጎ ሲጠነክር በረዥሙ ሂደት

    ሲፈጥር ይታያል በመጸከላቸው የሃሳብ ልዩነት

    በይፋ እናሳውቅ ወይም እንደድሮው እንቀጥልበት

    በሚል መጨቃጨቅ ጎራ በመለየት

    እንዲህ ተሸፋፍኖ የእኛ ግንኙነት

    መቀጠል አይችልም እንስጠው እልባት

    እኛ ከተፋቀርን ሌላው ምን አገባው

    እወቁልን እንበል ጉድ አንድ ሰሞን ነው

    ምን ይሁን ብለን ነው የምንሳቀቀው

    ድብብቆሽ ይብቃ ይፋ አርገን እናውጣው

    ብሎ ሃሳብ ሲያቀርብ ከሁለቱ አንደኛው

    በቀረበው ሃሳብ እንደማይስማማ ይገልጻል ሌላኛው

    ይህንን ማድረጉ ለምን ያስፈልጋል

    በለመድነው መንገድ ብንቀጥል ይሻላል

    ልብ ለልብ ተዋውቀን ተሳስበን ተፋቅረን

    ሦስተኛ ወገን እንዳይገባ አድርገን

    ይህን ያህል ጊዜ ስናሳልፍ አብረን

    የፍቅር ህይወታችን እንከን የለሽ እንዲሆን

    ድብቅ መሆኑ ነው በጣም የጠቀመን

    ስለዚህ በእኔ እምነት የእኛ ግንኙነት

    ልክ እንዱሮአችን መቀጠል አለመት

    ብሎ ምላሽ ሲሰጥ ሁለተኛው ወገን

    ሁለቱùም ያያሉ በተቃራኒነት መሰለፋቸውን

    ድብቅ ፍቅረኞቹ አጥተው ስምምነት

    በተደጋጋሚ ሲያደርጉ ውይይት

    ስለማይፈልጉ የተሸናፊነት ፍንጭ ለማሳየት

    ወይም ከአቋማቸው ፍንክች ለማለት

    በጣም ያስቸግራል የተፈጠረውን ልዩነት ለመፍታት

    በዚህ የተነሳ ድብቁ ፍቅራቸው ሲጀምር መቀዝቀዝ

    ነግሠው ይታያሉ ኩርፊያና ንዝንዝ

    ግንኙነታቸው እያደር ሲሻክር

    መተሳሰብና መደማመጥ ሲቀር

    የፍቅር ህይወታቸው እንዲያ የሚኮሩበት

    የጠብ የንትርክ ጥላ ሲያጠላበት

    አንዱ አንዱን ይወቅሳል በጥፋተኛነት

    ከዚያም አልፎ ተርፎ እልህ በመጋባት

    ስድብና ግልምጫ እየጨመሩበት

    ስለሚያበላሹት የነበራቸውን ጥሩ ግንኙነት

    የሰዎች እርዳታ ሳይጨመርበት

    በፍጹም አይችሉም መፍጠር ስምምነት

    የተፈጠረውን ልዩነት የሚያጠብ

    አማራጭ ሲጠፋ አስታራቂ ሃሳብ

    ሰዎች ይወቁልን የሚል አቋም ያለው

    በሚችለው መንገድ አመቺ በሚለው

    እንዲታወቅለት ድብቁ ፍቅራቸው

    ገሀድ ያወጣዋል ለሚያውቀው ሁሉ ሰው

    ሌላኛው ወገን ግን በአቋሙ በመጽናት

    አሁንም ሚስጥር ነው ብሎ በመገመት

    ወዳጅ ዘመዶቹ ቀርበው ሲጠይቁት

    እውነት እንደሆነ ሰዎች የሚያወሩት

    ስለድብቅ ፍቅሩ የሚንሾጸሾኩት

    እርግጡን ንገረን ብለው ሲያፋጥጡት

    በመቅበጥበጥና በጣም በመቆጣት

    ሆን ብለው አስበው የእሱን ስም ለማጥፋት

    የማይወዱት ሰዎች ያቀነባበሩበት

    የፈጠራ ወሬ ነው ብሎ ማጭበርበር

    ህዝብ ያወቀው ሚስጥር የሆነውን ነገር

    ሁለቱ ፍቅረኞች በአቋማቸው ፀንተው

    በአመለጸከትም እጅግ ተራርቀው

    እየላላ ሲሄድ ግንኙነታቸው

    ተቻችሎ መኖር በጣም ሲከብዳቸው

    ወደ ጠብ ያመራል የዱሮው ፍቅራቸው

    ይኸ ግንኙነት ቶሎ ታስቦበት

    አስፈላጊው እርምት ጸልተደረገበት

    ሊያስከትል ይችላል ከፍተኛ ጥፋት

    ቀላል ስለማይሆን ጥፋቶችን ሁሉ በዝርዝር ለማየት

    ጥቂቶችን ብቻ ስንሞክር ለማውጣት

    በንፁህ ልቦና አንዱ አንዱን ለመስማት

    ፈጹም ያለመፍቀድ ወይም ትግዕስት ማጣት

    ለተራው ንግግር ሌላ ትርጉም መስጠት

    ከዚያም አልፎ ተርፎ መሰለፍ ለጥፋት

    አንዱ ሌላኛውን ማየት እንደ ጠላት

    በመበቀል ስሜት ለጥቃት መነሳት

    በዚህ ግንኙነት ግራ የተጋቡት

    ሁለቱን ፍቅረኞች የሚያውቁ በቅርቡት

    ይለግሷቸዋል ምክርና አስተያየት

    ምንድነው ንትርክ እንዲህ ሰላም ማጣት

    እናንት እራሳችሁ ጠብና ጭቅጭቅ የምትጋብዙት

    አብራችሁ በደስታ መኖር ስትችሉ

    በሆነ ባልሆነው እንዲህ ስትጣሉ

    ይታዘቧችኋል የሚያዩአችሁ ሁሉ

    ስለዚህ እስጸሁን የተፈጠረውን በሙሉ ትታችሁ

    ስላምን አስፍኑ በመጸከላችሁ

    እኛም ዝግጁ ነኝ ልንቆም ከጎናችሁ

    በማለት የሚጠቅም ምክራችውን ሰጥተው

    ይማፀና*ቸዋል እንዲቀራረቡ ልክ እንደ ዱሮአቸው

    ከዚያም ለዚህ ጉዳይ ልዩ ትኩረት ሰጥታ

    እምዬ ተፈጥሮ መሀላቸው ገብታ

    ፍሬ ስትሰጣቸው እጆቿን ዘርግታ

    የመደንገጥ ስሜት ስታነብባቸው

    በዚህ አዲስ ክስተት እንዳይሸበሩ ልታረጋጋቸው

    ሳይጠቅም አይቀርም ልምዴን ላጸፍላችሁ

    ረጋ ብላችሁ ስሙኝ እባጸችሁ

    መፍትሔ የምለውን በግልጽ ልንገራችሁ

    ፍቅር ስምምነት የሚፈጥርላችሁ

    ቢቸኛው አማራጭ ይህ ነው የቀራችሁ

    ስለዚህ ይህ እድል እንዳያመልጣችሁ

    እንዳትዘናጉ ያዙት አጥብቃችሁ

    የፈጣሪም ምክር ብዙ ተባዙ ነው

    በፍጹም አትፍሩ ልጅ መውለድ ፀጋ ነው

    ብላ ምክርና ድፍረት ስትሰጣቸው

    ሁለቱም ፍቅረኞች ምክሯን ተቀብለው

    አንድ ጋ ለመኖር ባልና ሚስት ሆነው

    ቆርጠው ይነሳሉ ማሪኝ ማረኝ ብለው

    በስተመጨረሻም በመጸከላቸው የተፈጠረውን

    እርግፍ አርገው ትተው ዱሮ የሆነውን

    በተግባር ላይ ሲውል ይኸ ወሳኔአቸው

    በይፋ ይወጣል ድብቁ ፍቅራቸው

  • ይች ናት ጨዋታ (ሰኔ 1997)

    ከእለታት አንድ ቀን በደንብ የማላውቀው

    አንድ ሰው መጣና አለኝ ስምህ ማነው

    በዚህ ሰው ጥያቄ ግራ በመጋባት

    ስሜን ለምን ማወቅ አስፈለገህ አልኩት

    የመለስኩለት መልስ ስላስደነገጠው

    መልሴን እንደሰማ ፈገግ ብሎ እያየኝ

    ይቅርታ አድርግልኝ አጥፍቻለሁ አለኝ

    ከዚያም በመቀጠል ዘርግቶ ቀኝ እጁን

    አለ እንተዋወቅ ነግሮኝ ማንነቱን

    እጁን ጨበጥኩና ስገልጽለት ስሜን

    ትኩር ብሎ እያየኝ ለቀቅ አርጎት እጄን

    ስምህን ስሰማ የማውቅህ መሠለኝ

    በመልክ ደግሞ ሳይህ ጥርጣሬ ገባኝ

    ያንተ ስም በፍጹም ለእኔ እንግዳ አይደለም

    ግን በእርግጠኝነት የት እንደሰማሁት መናገር አልችልም

    ይህን ብሎ ወዲያው አይን አይኔን እያየ መልሴን ሲጠባበቅ

    ምንም ሰፈራችን አንድ እንደሆነም ባውቅ

    ጭራሽ አይመስለኝም ከዛሬ ቀን በፊት የምንተዋወቅ

    ብዬ ተናግሬ ሳልጨርስ ሃሳቤን

    ቀበል አረገና ቀጠለ ማውራቱን

    በጣም ያስገርማል የእኔና አንተ ነገር

    ለረዠም ዘመናት ስንኖር አንድ ሰፈር

    ሰላምታ ሳይኖረን ሳንጫወት አብረን

    ዛሬ ባጋጣሚ በድንገት ተዋወቅን

    የቅርብ ጓደኛ ወይ ዘመድ የሚባል

    እዚህ ስለሌለኝ ብቸኛ መሆኑ በጣም ሰልችቶኛል

    ስለዚህ እባክህ ያለፈውን ትተን

    እየተመጸከርን የእረፍት ጊዜያችንን

    አብረን በመጫወት ማሳለፍ አለብን

    እያለ ሲያግባባኝ ጓደኛ እንድሆነው

    ተወኝ አልፈልግም ሰልችቶኛል ስለው

    ብሎ መለሰልኝ እባክህ ሞኝ አትሁን መጫወት ጥሩ ነው

    ብቸኛ መሆኑ ብዙ መዘዝ አለው

    የሰው ልጅ ያለ ሰው ጭራሸ ዋጋም የለው

    ምንም አይጎዳህም የኔ ጓደኝነት እባክህ ሞክረው

    እያለ መላልሶ ስለወተወተኝ

    እሽ ልሞክረው ብዬ ተስማማሁኝ

    እንዲህ ተጀምሮ ጓደኝነታችን

    ብዙ ጊዜ ሳንቆይ መስማማት አቃተን

    ጨዋታ ስንጀምር ይለኛል አፍ አፌን

    እኔን ብቻ ስማኝ አድርግ የምልህን

    እንዳትጠይቀኝ ብለህ እንዴት ለምን

    እያለ ደጋግሞ ሲገልጽ ፍላጎቱን

    በደንብ ተረዳሁት የውስጥ ስሜቱን

    ድብቅ ስብዕናውን የእውነት ማንነቱን

    እንዲሁም አስተዋልኩ በመጸከላችን እንዳለ ልዩነት

    ጨርሶ እንደማያምን በእኔ ጓደኝነት

    ለይስሙላ ብቻ መስሎ ለመታየት

    እንደሚሽቀዳደም ወዳጅ ነኝ ለማለት

    ትውውቅ ስናደርግ የተባባልነውን

    ተሳስበን ተፋቅረን እንኑር ተከባብረን

    ብለን ሁለታችን የተስማማነውን

    ይህን የጋራ አቋም በመተው ወደ ጎን

    ሌላ ሃሳብ አመጣ እኔ ያልጠበቅሁትን

    ከልምድ አንፃር ሳየው እኩል ስላይደለን

    አንተ ተከተለኝ እኔ መሪ ልሁን

    በማለት እቅጩን ነግሮኝ ያሰበውን

    ፋታ እንኳን ሳይሰጠኝ ለመግለጽ ሃሳቤን

    አመለጸከቱን በእኔ ላይ ሲጭነው

    አዲስ ሰው ሆነብኝ ጭራሽ የማላውቀው

    በዚህ አይነት መንገድ ቶሎ ተረሳና ጓደኝነታችን

    ህጉንና ደንቡን ስቶ ጫዋታችን

    እንፋጠጥ ጀመር መቻቻል አቅቶን

    እስክናምን ድረስ በስሜት ተገፍተን

    አንድ ጋ አብረን መኖር አንችልም ብለን

    ቁርጥ አቋም በመያዝ ወስነን ተነስተን

    አንዱ አንዱን ለማጥፋት እንሯሯጣለን

    በዚህም ድርጊታችን ከፍተኛ ጉዳት እናስከትላለን

    በሁለቱም ወገን ቶሎ የማይጠፋ ጠባሳ እንተዋለን

    የእኛ አልበቃ ብሎ ሌሎችንም ሰላም እንነሳቸዋለን