ሰው ለምርጫ ሲቀርብ ህዝብ ለማገልገል
ሰዎች አያውቁኝም አይመርጡኝም በሚል
ወይም ከተመረጥኩ ማንም አያስታውስ የገባሁትን ቃል
በማለት ተነስቶ ሁሉን አደርጋለሁ ብሎ ቃል ይገባል
ይህን እያወቀ አንተን መራጩን ህዝብ ሊያታልል ሲሞክር
በጥሩ አነጋገር ሊስብህ ሲጣጣር
ሌት ከቀን ስለአንተ አስባለሁ ሲልህ
በጭራሽ አትስጋ ፍፁም ቅር አይበልህ
ገና ለወደፊት ምን ይመጣል ብለህ
ብዙ ሀሳብ አይግባህ እኔ አለሁ ከጎንህ
ብሎ በምርጥ ቃላት ሲሸነጋግልህ
ስህተት ውስጥ እንዳትወድቅ መጠንቀቅ አለብህ
ይህ ላንተ ቆሜያለሁ አስብልሀለሁ ብሎ የሚያወራው
ቀላል ሰው አይደለም የሩቅ አላማ አለው
ሰው እንዳያውቅበት በሚስጥር የያዘው
አጋጣሚ ሲያገኝ ገሃድ የሚያወጣው
የሚያነበንበው በግልፅ የሚሰብከው
ፍትህ እኩልነት ሰላም ብልፅገናን ሰፍነው ለማየት ነው
ሃሳቡ እስኪሳጸ እቅዱ እስኪፈፀም
ጸንደበቱ ፍፁም ሌላ ቃል አይወጣም
ይህ ሁሉ ውትውታ በቂ አልመስልህ ሲለው
ሌላ እቅድ ያወጣል አንተ እንድትመርጠው
ጭራሽ እንደሌለህ ማሰቢያ ጭነቀላት
እንደማትችል ሁሉ ሃሳብን ለመግለፅ በራስህ እንደበት
ያ ላንተ አስባለሁ እጨነቃለሁ ባይ
ለእኔ ተወው ይላል የራስህን ጉዳይ
እየደጋገመ እጅ እጅ እስከሚልህ
ለህዝብ እንደቆመ መግለጫ እየሰጠህ
እያዥጎደጎደ ምርጥ ምርጥ ቃላትን
ሊያሳምን ሲþሞክር ትልቅ ሰውነቱን
የሱን ጎበዝነት ያላማ ፅናቱን
ቀጠል ያደርግና
እኔ ነኝ የማውቀው መሆን ያለበትን
የህዝብ ችግሮች የሚፈቱበትን
በጣም በአጭረ ጊዜ ጥሩ ለውጥ ለማየት
እናንተ አትድከሙ ሁሉን ለኔ ተውት
ወሰን የለሽ ስልጣን ስጡኝ ሃላፊነት
ማለት ይጀምራል ደጋግሞ መወትወት
አጋጣሚ አግኝቶ ስልጣን ከጨበጠ
አጭበርባሪ የለም ከሱ የበለጠ
ሰውን ለመመዘን ባዘጋጀው መስፈርት
እሱ ነው አዋቂ ብቸኛው ሳይንቲስት
ሁሉም ሰው ማሙሽ ነው አርቆ የማያስብ
ሊታለል የሚችል ያለምንም ገደብ
ስለዚህ ይሆናል ፈላጭ ቆራጭ ዳኛ
ማንም የማያዘው የስልጣን ቀበኛ
እሱን ለሚቃወም ጭራሽ የማይተኛ
ይሉኝታ የሌለው ትልቅ ወንጀለኛ
ለረጅም ዘመናት ደብቆ የያዘው
ይወጣል ፀባዩ ፍፁም እውነተኛው
መስገብገብ ያበዛል ሀብት ለማጸበት
በስልጣን መባለግ ሁሉን ለእኔ ማለት
ተቃዋሚን ማፈን በሃይል ዝም ማሰኘት
የቀረውንም ህዝብ መሸንገል በቃላት
ሁሌ እየመሰለዉ የማይነቃበት
ችግሩ ብዙ ነዉ ጊዜ ስጡኝ ማለት
ሽንገላዉ ድለላዉ ብሶቱ ሲበዛ
ማሙሽ የተባለዉ ይነሳል በቁጣ አይደም የዋዛ
በስሙ የሚነግድ ያኔ ወየዉለት
ማጣፊያዉ ያጥረዋል ይወጣል በፍርሀት
በብልጣብልጥነት ለሚያደርሰዉ ጥፋት
የእጁን ያገኘዋል ተገቢዉን ቅጣት
Leave a Reply