ድሮና ዘንድሮ (ሰኔ 1993)

ዘመን አለፈና ሲተጸ በዘመን

ሰዎች ተመሳስለው በጣም ግራ አጋቡን

እነኛ ደግ ሰዎች ድሮ የምናውቃቸው

የተመሰገኑት በጥሩ ስራቸው

ሰዎችን በእኩል አይን የሚመለከቱት

ለሌሎች አርአያ በመሆን የኖሩት

ከቶ ለምን ይሆን ዛሬ የማይታዩት

ችግራችን ሰፍቶ ሁሉም ሲል እነሱን

በሌሎች ተውጠው ጭራሹን ጠፉብን

ዛሬ በዚህ ዘመን በዝተው የሚታዩት

የምናገኛቸው በየደረስንበት

ለኔ ከሚል ቃል ውጭ ሌላ የማይገባቸው

ቆርጠው የተነሱ ለግል ደስታቸው

የሌሎች መቸገር ደንታ የማይሰጣቸው

ለጥቅም የቆሙ ስግብግቦች ናቸው

ታላቆችን ማክበር እግዚአብሄርን መፍራት

ችግረኛ መርዳት የተራበ ማብላት

ለሌሎች የማሰብ የመቆርቆር ስሜት

ምነው አይታይም አሁን እንደ ድሮው

ከቶስ ለምን ይሆን ሰወ“ የጨከነው

ወገኑ ሲቸገር እያየ እንዳላየ ጥሎት የሚሄደው?

ዘመን ያስቆጠረው ያ የምንኮራበት

የወረስነው ባህል ጸያት ከቅድም አያት

ዛሬ በእኛ ትውልድ ተሽቀንጥሮ ወድቋል

እንዲያውም ኋላ ቀር ተብሎ ተፈርጇል

ዛሬ በምትኩ ግለኝነት ነግሷል

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *