Tag: 1993

  • ዝምታ (ሰኔ 1993)

    ብሶቴን አምቄ አንገቴን ደፍቼ

    ምላሴን አስሬ ልሳኔን ዘግቼ

    ሁሉን ነገር ጥዬ ልኑር ስል ሠርቼ

    የዝምታዬን ምንጭ ለማወቅ ሚስጥሩን

    ፍጹÜም ጤና ነሱኝ አበዙት ስቃዬን

    ክቶ ያለ ወትሮው ምን ዝም ያሰኘዋል?

    ከቅርብ ቀን ወዲህ ሰዎችን ይሸሻል

    ሚስጥር ይኖረዋል ደብቆ የያዘው

    ብቸኛ የሚያደርግ ፋታ የሚነሳው

    ሰው እንዳያውቅበት የሚሸፋፍነው

    ሀሳቡ እንዲታወቅ ሚስጥሩ እንዲወጣ

    ክትትል ያሻዋል ሲገባ ሲወጣ

    ብለው ወሰኑብኝ በማላውቀው ነገር

    ማስረጃ ሳይዙ ሳይጠሩ ምስክር

    ሃሳቤን ለመግለፅ እድል ሳይሰጠኝ

    ያጠፋሁት ጥፋት ሳይገለፅለኝ

    ማወቅ እንኳን ሰሳልችል ማን እንደከሰሰኝ

    ወይም የክስ መጥሪያ በፅሁፍ ሳይደርሰኝ

    ከሳሽ እና ዳኛ ሆነው ፈረዱብኝ

    ከዛ በኋላማ በሄድኩበት ሁሉ

    እንደ እራሴ ጥላ እየተከተሉ

    እንቅስቃሴዬን በጥብቅ ይቃኛሉ

    ድርጊቴን በሙሉ ይቆጣጠራሉ

    ትንሽ ስህተት ሲያዩ እሷን በማጋነን

    እጅግ በጣም ጎዱት የስራ ሞራሌን

    ፋታ ስላሳጡኝ በክትትል ብዛት

    መስራት አቅቶኛል ተውጬ በፍርሀት

    በአጭሩ ለመግለፅ የደረሰብኝን

    ሰው ተጠራጣሪ ሌሎችን የማላምን

    ጭንቀታም ሆኛለሁ ያጣሁ ነፃነቴን

    ዝምታ ወርቅ ነው እንዳልተባለለት

    ይኸው ወንጀል ሆኖ አበሳ አየሁበት

  • ዝምታ ወርቅ ነው (መስከረም 1993)

    በምኔ ልናገር አፌ ተሸብቦ

    በፍርሃት ተውጬ ወኔዬ ተሰልቦ

    በእኔነቴ አምኜ እራሴን እንዳልችል

    የሚሉኝን ሁሉ በሙሉ እንድቀበል

    የሰውነቴ አርማ የእኔን መገለጫ

    የግል አእምሮየን የሃሳቤን ማመንጫ

    የራሳቸው አድርገው እንዳሻቸው ሊያዙት

    ፍፁም እንዳይኖረኝ የማሰብ ነፃነት

    እንዳላመዛዝን ህሊናዬን ስቼ

    እነሱን እንዳመልክ ሁሉን ረስቼ

    ተስፋዬ እንዲጨልም በሀሳብ ሎሌነት

    አንደበቴ ታስሮ የሞት ሞት እንድሞት

    ስሜቴ እንዲኮላሽ ፍፁም ፈሪ እንድህን

    በየደረስኩበት የምናገረውን

    ይከታተላሉ ከአፌ የሚወጣውን

    አንድ ነገር ብዬ ከገለፅኩ ሃሳቤን

    ይጨምሩበታል እኔ ያላልኩትን

    አለ የተባልኩት በወሬ ቀበኞች አምሮ ተከሽኖ

    ጣፍጦ ስለሚቀርብ ተባዝቶ ተጋኖ

    ብዙ ጊዜ ሳይቆይ ቶሎ ያራቡታል

    እየሰነጠቁ ትርጉም ይሰጡታል

    እኔን ለመወንጀል ይጠቀሙበታል

    ጆሮውን ቀስሮ የሚያሳድድ ነገር

    ምላሱን አሹሎ ተናግሮ የሚያናግር

    ወሬ የሚለቅም የሰው ወፍ ሲመጣ

    ጥርጣሬ ነግሶ መተማመን ታጣ

    ብሶቴን አውጥቼ እንዳልናገረው

    የማን ምንነቱን ስላልቻልኩ ላውቀው

    መመሪያዬ ሆኗል ዝምታ ወርቅ ነው

  • ድሮና ዘንድሮ (ሰኔ 1993)

    ዘመን አለፈና ሲተጸ በዘመን

    ሰዎች ተመሳስለው በጣም ግራ አጋቡን

    እነኛ ደግ ሰዎች ድሮ የምናውቃቸው

    የተመሰገኑት በጥሩ ስራቸው

    ሰዎችን በእኩል አይን የሚመለከቱት

    ለሌሎች አርአያ በመሆን የኖሩት

    ከቶ ለምን ይሆን ዛሬ የማይታዩት

    ችግራችን ሰፍቶ ሁሉም ሲል እነሱን

    በሌሎች ተውጠው ጭራሹን ጠፉብን

    ዛሬ በዚህ ዘመን በዝተው የሚታዩት

    የምናገኛቸው በየደረስንበት

    ለኔ ከሚል ቃል ውጭ ሌላ የማይገባቸው

    ቆርጠው የተነሱ ለግል ደስታቸው

    የሌሎች መቸገር ደንታ የማይሰጣቸው

    ለጥቅም የቆሙ ስግብግቦች ናቸው

    ታላቆችን ማክበር እግዚአብሄርን መፍራት

    ችግረኛ መርዳት የተራበ ማብላት

    ለሌሎች የማሰብ የመቆርቆር ስሜት

    ምነው አይታይም አሁን እንደ ድሮው

    ከቶስ ለምን ይሆን ሰወ“ የጨከነው

    ወገኑ ሲቸገር እያየ እንዳላየ ጥሎት የሚሄደው?

    ዘመን ያስቆጠረው ያ የምንኮራበት

    የወረስነው ባህል ጸያት ከቅድም አያት

    ዛሬ በእኛ ትውልድ ተሽቀንጥሮ ወድቋል

    እንዲያውም ኋላ ቀር ተብሎ ተፈርጇል

    ዛሬ በምትኩ ግለኝነት ነግሷል

  • ጥሩ ሠራተኛ (ሰኔ 1993)

    ችሎታ ያለው ሰው በሥራ የሚያምን

    ከሥራ ነጥሎ አያይም ህይወቱን

    በደንብ ተገንዘቦ መብቱን ግዴታውን

    በአግባቡ ይወጣል የሥራ ድርሻውን

    ጥሩ ሠራተኛ የሚጠበቅበት

    ምንም ብዙ ቢሆን መመዘኛው መስፈርት

    ጥቂቶችን ብቻ ብንሞክር ለማየት

    እንከንየለሽ ሆኖ መገኘት አለበት

    አንድን ሠራተኛ ጥሩ ነው ለማለት

    የሚፈለግበት ማሟላት ያለበት

    ወይም የሚገባው እንደ መርህ መከተል

    አጠር ባለ መልኩ ከዚህ በታች ቀርቧል

    ችሎታን አሟጦ በሥራ ላይ ማዋል

    ከጊዜ ጋር አብሮ ለመራመድ መቻል

    ውሳኔ አሰጣጥ ላይ አለማወላወል

    ብቃት የሚለጸው በውጤታማነት መሆኑን መቀበል

    አላማ እንዲሳጸ እንዲመታ ግቡን

    ዛሬ ሊጠናቀቅ ሊያልቅ የሚችለውን

    ለነገ አለማለት ወዲያው ማከናወን

    በአግባቡ መጠቀም ሙሉ የሥራ ጊዜን

    ጥንቃቄ ማድረግ ምንም እንዳይባክን

    ጠንክሮ በመሥራት ማስመስከር ችሎታን

    በብቃት በጥራት ሥራን ማከናወን

    ለሌሎች ምሳሌ ጥሩ አርአያ መሆን

    አለቃን በመፍራት ግራ አለመጋባት

    ሥራን አለቃ አርጎ ግዴታን መወጣት

    የወቅቱን ሁኔታ እያመዛዘኑ መቃኘት አቋምን

    በገንቢነቱ አምኖ በፀጋ መቀበል እውነተኛ ሂስን

    ስህተትን ለማረም ፈቃደኛ መሆን

    ድርቅ አለማለት ሰውን ለማሳመን

    በራስ መተማመን ፍጹም ያለመፍራት

    ለአሉባልታ ምንም ቦታ ያለመስጠት

    የሃሳብ ልዩንትን በውይይት መፍታት

    ከሌሎች ለመማር አዕምሮን ማድረግ ክፍት

    ከባልደረቦች ጋር ተከባብሮ መሥራት

    ታማኝነትንም በተግባር ማሳየት

    በጊዚያዊ ውጤት ያለመዘናጋት

    በቂ አይደለም ብሎ በርትቶ በመሥራት

    የተሻለ ውጤት ለማምጣት መነሳት

    ለችግር ፈጽሞ እጅን ያለመስጠት

    ጊዚያዊ ፈተናን አልፎ በብልሀት

    ብሩህ ተስፋ ማየት መምራት ጥሩ ህይወት

    በቅን ልቦናና በመቻቻል ስሜት

    ሥራን ማከናወን በእቅድ በመመራት

    አፈጻጸሙንም መመርመር በጥልቀት

    ደጸማ ጎኖቹን ለይቶ በማውጣት

    ወደፊት ለማምጣት የበለጠ ውጤት

    በተጠንቀቅ መቆም ለመማር ከስህተት

  • ተስፋ (ጥቅምት 1993)

    ተስፋ ለሰው ልጆች ብርቅዬ አለኝታ ናት

    እስትንፋስ የምትሰጥ ለመኖር በህይወት

    አንደጠዋት ፀሀይ ሁሌ ሲጠብቁአት

    ባትጨበጥ እንኳን አሁን ባትከሰት

    እይጠራጠሩም ኋላ እንደሚያገኗት

    ደምቃና ተውባ የበለጠ አምሮባት

    በተስፋ ተሞልቶ ሰው መኖር ጸልቻለ

    ምንም ቢሆን ነገ ከዛሬ ይሻላል ይበልጣል እያለ

    ጭልምልም ጸለበት የወደፊት እጣው

    ጭራሽ ጥሩ ነገር አልታይህ ጸለው

    በቃ አብቅቶለታል ይህ ሰው ተስፋ ቆርጧል

    በድኑ እየነኖረ እሱ የለም ሞቶአል