ችሎታ ያለው ሰው በሥራ የሚያምን
ከሥራ ነጥሎ አያይም ህይወቱን
በደንብ ተገንዘቦ መብቱን ግዴታውን
በአግባቡ ይወጣል የሥራ ድርሻውን
ጥሩ ሠራተኛ የሚጠበቅበት
ምንም ብዙ ቢሆን መመዘኛው መስፈርት
ጥቂቶችን ብቻ ብንሞክር ለማየት
እንከንየለሽ ሆኖ መገኘት አለበት
አንድን ሠራተኛ ጥሩ ነው ለማለት
የሚፈለግበት ማሟላት ያለበት
ወይም የሚገባው እንደ መርህ መከተል
አጠር ባለ መልኩ ከዚህ በታች ቀርቧል
ችሎታን አሟጦ በሥራ ላይ ማዋል
ከጊዜ ጋር አብሮ ለመራመድ መቻል
ውሳኔ አሰጣጥ ላይ አለማወላወል
ብቃት የሚለጸው በውጤታማነት መሆኑን መቀበል
አላማ እንዲሳጸ እንዲመታ ግቡን
ዛሬ ሊጠናቀቅ ሊያልቅ የሚችለውን
ለነገ አለማለት ወዲያው ማከናወን
በአግባቡ መጠቀም ሙሉ የሥራ ጊዜን
ጥንቃቄ ማድረግ ምንም እንዳይባክን
ጠንክሮ በመሥራት ማስመስከር ችሎታን
በብቃት በጥራት ሥራን ማከናወን
ለሌሎች ምሳሌ ጥሩ አርአያ መሆን
አለቃን በመፍራት ግራ አለመጋባት
ሥራን አለቃ አርጎ ግዴታን መወጣት
የወቅቱን ሁኔታ እያመዛዘኑ መቃኘት አቋምን
በገንቢነቱ አምኖ በፀጋ መቀበል እውነተኛ ሂስን
ስህተትን ለማረም ፈቃደኛ መሆን
ድርቅ አለማለት ሰውን ለማሳመን
በራስ መተማመን ፍጹም ያለመፍራት
ለአሉባልታ ምንም ቦታ ያለመስጠት
የሃሳብ ልዩንትን በውይይት መፍታት
ከሌሎች ለመማር አዕምሮን ማድረግ ክፍት
ከባልደረቦች ጋር ተከባብሮ መሥራት
ታማኝነትንም በተግባር ማሳየት
በጊዚያዊ ውጤት ያለመዘናጋት
በቂ አይደለም ብሎ በርትቶ በመሥራት
የተሻለ ውጤት ለማምጣት መነሳት
ለችግር ፈጽሞ እጅን ያለመስጠት
ጊዚያዊ ፈተናን አልፎ በብልሀት
ብሩህ ተስፋ ማየት መምራት ጥሩ ህይወት
በቅን ልቦናና በመቻቻል ስሜት
ሥራን ማከናወን በእቅድ በመመራት
አፈጻጸሙንም መመርመር በጥልቀት
ደጸማ ጎኖቹን ለይቶ በማውጣት
ወደፊት ለማምጣት የበለጠ ውጤት
በተጠንቀቅ መቆም ለመማር ከስህተት
Leave a Reply