ጥገኛ (ሚያዚያ 1996)

አለቃ ከሌለ ፈጥኖ የሚሰወር

በየምክንያቱ ከሥራ የሚቀር

በስህተት ጸልሆነ ሰዐት የማያከብር

መኖር የሚፈልግ ሁሌ በማጭበርበር

ዘግይቶ የሚገባ ቀድሞ የሚወጣ

አርፎ የማይሠራ የሚል ገባ ወጣ

መብቱን ለማስከበር ሁሌ የሚሟገት

ፍጹም የማይመስለው ግዴታ ያለበት

ሥራውን የሚሸሽ ከስንፍና ብዛት

አስቦ የማይሠራ ይህን አርግ ጸላሉት

ሊባል አይገባም ይህ ሰው ሠራተኛ

ሳይሠራ የሚበላ ፍጹም ነው ጥገኛ

ማህደሩ ሞልቶ ባሰት ያኪም ፈቃድ

ማንም አይቀድመውም ደመወዝ ለመውሰድ

የዚህ አይነቱ ሰው ጉብዝናው የሚታይ

በወሬ ነው እንጅ አይደለም ሥራ ላይ

ሥራ የሚያከብሩ ትጉህ ሠራተኞች

መስለው ይታዩታል ቀንደኛ ጠላቶች

የነሱ አርአያነት ሲመስለው እንቅፋት

ግልጥልጥ የሚያደርግ የሱን ደጸማነት

መፍትሄ ይመስለዋል መንፈሳዊ ቅናት

በሆነ ባልሆነው የሰውን ስም ማጥፋት

በወሬ ለመኖር ደፋ ቀና ማለት

ጎበዝ ሠራተኛ መስሎ ለመታየት

በየስብሰባው ላይ ሁሌ በመገኘት

የሚፈልገውን አለቃው ለመስማት

ምክር ለበስ ሃሳብ ተሽቀዳድሞ መስጠት

ደጋገግሞ መናገር ማቅረብ አስተያየት

አቋሙን መቀየር በማንበብ የሰው ፊት

መርህ አድርጎታል የዚህ አይነቱን ስልት

ክብርን ሸጦ መኖር መስሎት ብልህነት

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *