ይኑርም አይኑርም ቆይቶ በህይወት
ገና ከመነሻው በፈጣሪ ጌታ የተወሰነለት
ነፍሱ ከስጋው ጋር የምትለይበት
እልፈተ ህይወቱ የሚፈፀምባት
የመጨረሻዋ ደርሳ ያች ስአት
ባዶ በድን ሲሆን ወዲያው ከመቅጽበት
ዘመድ ወዳጆቹ በቅርቡ የሚያወቁት
ሳያስቡት ድንገት ስለተለያቸው ከልብ አዝነውለት
ዘለአለም ማረፊያው እንዲሆን አስበው ወደአዘጋጁለት
ወደ አዲስ መኖሪያው አጅበው ወስደውት
እንባ እየተራጩ ውስጥ አስገብተውት
አፈር ስለሆነ አፈር ጭነውበት
በስተመጨረሻም ስንብት አድርገው ሲሄዱ ጥለውት
ፊታቸው ጨልሞ ሀዘኑ አጥልቶበት
ይመስሉ ነበረ እስከ ዘለአለሙ ማ*ቹን የማይረሱት
ሀቁ ግን ሌላ ነው ትዝብት ውስጥ የሚከት
ቀብሩ ተፈጽሞ ሲያመሩ ወደ ቤት
ብዙ ሀዘንተኞች ያሉበትን ቦታ ጭራሽ ረስተውት
ሰው ይታዘበናል ብለው ሳያስቡ ያለምንም ሀፍረት
ፀፀት ይሁን ቁጭት በደንብ ያለየለት
ውይይት ጀምረው ስለማ*ቹ ማውራት
ይህ ሰው የኖረበት ያሳለፈው ህይወት
ምስቅልቅል ያለ ነው ስቃይ የበዛበት
ከመከራ በቀር ደስታን ያላየበት
እያለ የሌለ ሆኖ የቆየበት
ትረጉም የለሽ ነበር የማይሻል ከሞት
እስከ ዘለአለሙ እኛን ጥሎን ሲሄድ ዛሬ ለይቶለት
ምንም ባህል ሆኖ ከልብ ብናዝንለት
ከዚህ አጉል ኑሮ ችግር ከሞላበት
እንኳን ገላገለው መባል ነው ያለበት
ብለው እነደገና መልሰው ሲገድሉት
ምንም ይዘግይ እንጅ እንደሚከተሉት
የአዳም ዘር በሙሉ እንደማይቀር ከሞት
ጭራሽ ረስተው ነው በእራስ መውደድ ስሜት
እየመሰላቸው ሁሌ የሚኖሩ ዘለአለም በህይወት
Leave a Reply