እየሩሳሌም (የጸቲት 1998)

አንች እየሩሳሌም እስኪ ልጠይቅሽ

የሠላም ከተማ ብለው ሰይመውሽ

የብጥብጥና የእልቂት መናህሪያ ምነው አደረጉሽ?

የእምነቶች ሙዚየም የባህል አውድማ

የአንድነት ምልክት የስልጣኔ አርማ

የነብዮች ማዕከል ቅዱሷ ከተማ

በምን ምክንያት ነው በዚህ በእኛ ዘመን

ልዩ መታወቂያሽ ግርማ ሞገስሽን

ተገፈሽ እንዲሁ የቆምሽው እርቃንሽን?

የፍቅር ምሳሌ መሆንሽ ቀርቶ ነው

መጥፎ ነገር ብቻ ስለአንቺ የምንሰማው?

የዘመናችን ሰው ምን አርጊ ነው የሚልሽ

በወንድሞቹ ላይ ጦር የሚሰብቅብሽ

በሆነ ባለሆነው ሰላም የሚነሳሽ

ታሪክሽን አጉድፎ ስምሽን ያጠፋብሽ

በሀጢያቱ ብዛት በጣም ያረከሰሽ

ይህ የዛሬው ትውልድ የታሪክ ማይም

ክብርና ዝናሽን ሳይቆጥር ከምንም

አዕምሮው ታውሮ በጥላቻ መንፈስ በጊዚያዊ ጥቅም

በዘር በቋንቋና በእምነት በባህሉ ከእሱ የማይገጥም

በጉርብትና አብሮ ሊኖር አይገባም

የሚል መርህ ይዞ የተሳሳተ አቋም

ለሁለት ሊከፍልሽ በቀን ህልም ሲያልም

ይህ አስተሳሰብህ መሠረት የለውም

ልዩነት ውበት ነው እኛ ጸወቅንበት

ተከባብረንና ተሳስበን ተዛዝነን ስንፈጥር ህብረት

የጋራ እሴትና የአብሮ መኖር ስሜት የሚዳብርበት

አንተ ትብስ አንች ብለን እንደምኖር የምናሳይበት

ስለዚህ እንዲሁ ተገፍተህ በስሜት

ልዩነታችንን አግዝፈህ በማየት

አመዛዝነህ ሳታይ ነገሮችን ሁሉ ከስር ከመሠረት

ፍጹም አይገባም የቆየ ታሪክን ጥላሸት መቀባት

ብለን ሀቁን ነግረን ከስህተቱ እንዲማር ማድረግ ከተሳነን

ይዘገያል እንጂ በፍጹም አይቀርም የአንች መበተታተን

በምንችለው መንገድ ባለ በሌለ አቅም

ነገ ዛሬ ሳንል ጊዜ ሳንሰጥ ምንም

ይህን አፍራሽ ሂደት ጸቃተን ለማስቆም

ይህ የታሪክ ስህተት እንዳላይ ሲፈፀም

እድሜ ስጠኝ ብዬ ጭራሽ አልለምንም

አሁን እንኳን ብሞት ምንም አይቆጨኝም

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *