እናውቅልሀለን (ሀምሌ 1994)

ፖሊሲ ሲቀረጽ ሥራ ላይ እንዲውል

በጥናት ታግዞ ሁሉን አገናዝቦ ሊሆን ይገባዋል

ፖሊሲው እንዲሰምር እንዲመታ ግቡን

ማጤን ያስፈልጋል በደንብ መፈተሽ ጠቅላላ ይዘቱን

የሚያስገኘው ጥቅም የሚያመጣው ጉዳት

ችግርን ለመፍታት የሚሰጠው ትኩረት

ከአገር ዕራይ ጋር ተዛማጅነቱ

መሰረታዊ ለውጥ በሂደት ማምጣቱ

በተጠቃሚው ዘንድ ተቀባይነቱ

በደንብ ተመርምሮ ጸልታዬ በእርጋታ

ከመሆን አይድንም በውጥን የሚቀር ያለዘለቄታ

ቶሎ ተጀምሮ በቶሎ የሚፈርስ የዕቃ ዕቃ ጨዋታ

ከፖሊሲው ጋራ ቁርኝት ያላቸው

በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አቅፎ የሚይዛቸው

ተሳትፎ እንዲያደርጉ እድል ተሰጥቷቸው

ጸልተጸተተበት አስተያያታቸው

በእናውቃለን ስሜት በተወሰነ አጸል

ፖሊሲ ተቀርጾ በሥራ ላይ ሲውል

አይቀበሉትም የእራሳቸው አርገው

በግድ ከላይ በሀይል እስኪጫንባቸው

በጥቂቶች ብቻ ፖሊሲው ረቅቆ ተዘጋጅቶ ሲቀርብ

ሙያተኞች እንኳን ሳይሰጡበት ሃሳብ

ይጠቅመኛል ብሎ ሳይቀበለው ህዝብ

በባለቤትነት እውቅና ሳይሰጠው ሳያምንበት ከልብ

በትዕዛዝ መልክ ወርዶ በተግባር ላይ ሲውል

ከጥቅሙ ጉዳቱ እጅግ ያመዝናል

ፍጹም ያልጠበቁት ውጤት ሲገጥማቸው

ስህተት መስራታቸው በደንብ ሳይገባቸው

ፖሊሲ አውጪዎቹ በአቋማቸው ጸንተው

ይከራከራሉ ያወጡት ፖሊሲ እንከን እንደሌለው

ያገጠመው ችግር የአፈጻጸም ብቻ እንደሆነ አድርገው

ፖሊሲው ጥሩ ነው እኛ አምነንበታል

ሥራ ላይ ቢያውለው ህዝቡ ይጠቀማል

አለ የተባለው የአፈጻጸም ችግር በሂደት ይፈታል

አያስፈልገውም ፖሊሲው መሻሻል

ሁሉም ሊቀበለው ሊያምንበት ይገባል

በማለት ሲያቀርቡት እንደፈጣሪ ቃል

የበለጠ ህዝቡን በጣም ያስቆጣዋል

ይህን የህዝብ ስሜት ለማብረድ በማስብ

ችግርህ ገብቶናል በፍጹም አታስብ

በደንብ አውቀነዋል የምትፈልገውን

ምንም አትጨነቅ ከጎንህ እኛ አለን

ሁሉን ለእኛ ተወው ሙሉ እምነት ጣልብን

ተገቢውን መፍትሄ እንሰጥሀለን

ብለው ቢደልሉት በተስፋ ቢሞሉት

የገቡለትን ቃል እንደማያከብሩት

ጊዜ አይወስድበትም ህዝቡ ለመረዳት

የሰሚ ያለህ ሲል ለመግለጽ ሃሳቡን

ያለበትን ችግር ጠቅላላ ብሶቱን

አይዞህ የሚል ሲያጣ የሚቆም ከእሱ ጎን

በገሀድ ያሰማል ህዝቡ ተቃውሞውን

ያኔ የበለጠ ግራ በመጋባት

ከራሳቸው ጋራ ይገጥማሉ ሙግት

ከቶ ለምንድን ነው እኛን የማይሰማን

እንዴት አይረዳም ለእሱ የሚጠቅመውን

ከዚህ የበለጠ ምን ፍጠሩ ነው የሚለን

በማመስገን ፋንታ ለምን ነው የሚወቅሰን

በማለት ደጋግመው ጥያቄ ጠይቀው

የሚሰጡት ምላሽ አላጠግብ ሲላቸው

በጣም በመናደድ እልህ በመጋባት

ህዝቡ ይህን ፖሊሲ ወደደውም ጠላው መቀበል አለበት

እንደማንቀይረው ሊረዳው ይገባል ግልጽ ሊሆንለት

ከዚህ የተለየ ሌላ ልዩ ተዓምር መቼም አንፈጥረለት

ብለው ይህን አቋም ይፋ አርገው ሲያወጡት

ህዝቡ የበለጠ እልህ በመጋባት

ሀሳቡን ይገልጻል ያለምንም ፍርሀት

ፖሊሲውን ፍጹም እንደማይቀበል

ሁሉም እንዲረዱት በግልጽ ይናገራል

በሚመስለው መንገድ በሚችለው አቅም

ድምፁን ለማስከበር ወደ ኋላ አይልም

ከዚህ ሁሉ ጣጣ የማይበርድ ሁከት

የመወሰን ስልጣን ጠቅልለው የያዙት

ጆሮአቸውን ለህዝብ ምን አለ ቢከፍቱት

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *