የስልጣን ባለቤት ህዝብ መሆኑ ቀርቶ
ስልጣን የተሰጠው ይኖራል ተዝናንቶ
በአደራ መሆኑን ስልጣኑን የያዘው
ጭራሹን እረስቶ የግሉ ሲያደርገው
ለፈለገው ተግባር እንዳሻው ሲያውለው
ጸለቆቹ በቀር ሌላ የሚጠይቀው
ማንም አጸል ያለ በፍፁም ሳይመስለው
የእድሉ ወሳኞች አለቆቹ ናቸው ብሎ ስለሚያምን
ማምለክ ይጀምራል እንደአምላክ እነሱን
በሚችለው መንገድ አቅሙ በፈቀደው
እነሱን ማስደሰት ይመስለዋል ስራው
ባገኛቸው ቁጥር መርበትበት ያበዛል
አክብሮቱን ሊያሳይ ይሰግድላቸዋል
ታማኝነቱንም በአፅንኦት ይገልፃል
ይህን አድርግ የሚል ትእዛዝ ሲመጣለት
እርግጠኛም ቢሆን የተሰጠው ትእዛዝ ስህተት እንዳለበት
ድፍረቱ አይኖረውም ጥያቄ ለማንሳት
ውይም አይሰነዝር ይህ እንዲህ ቢደረግ የሚል አስተያየት
የመጣውን ትእዛዝ እንዳለ መቀበል
ምንም ሳይቀይሩ በስራ ላይ ማዋል
ይህ ስለሚመስለው የሚጠበቅበት
ውጤታማነቱ የሚመዘንበት
አለቆቹ ብቻ የሚፈልጉትን
የሚያስደስታቸው መስሎ የታየውን
መጥፎ ይሁን ጥሩ ውጤቱን ሳይገምት
መስራት ይጀምራል ምንም ሳያምንበት
ከበላይ አለቆች ምስጋና ለማግኘት
ያቀርብላቸዋል በጥሩ ሁኔታ የተፃፈ ሪፖርት
ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ የሚፈልጉትን እነሱ ለመስማት
ለአለቆቹ ሽጦ ሙሉ ስብእናውን
ጭራሽ ይረሳዋል ዋነኛ ስራውን
በቅን ለማገልገል ቃል የገባለትን
በስሙ ሃላፊነት የወሰደበትን
ተራውን ህዝብ ሁሉ በንቀት በማየት
ምንም አያመጡ በሚል አጉል ትእቢት
ፈቃደኛ አይሆንም እነሱን ለመስማት
ወይም ቦታ አይሰጠው ለነሱ አስተያየት
የግድ ሆኖበት በአጸል ጸገኛቸው
ከፍ ዝቅ አድርጎ ሲያመናጭቃቸው
ከፍትፍቱ ፊቱ እንደሚባልለት
የመጡበት ጉዳይ ሳያገኝ እልባት
ጥለው ይሄዳሉ ተቃጥለው በንዴት
ክብር የሚነጸ የዚህ አይነት ድርጊት
በባለ ስልጣኑ የተፈፀመበት
የዜግነት መብቱ የተረገጠበት
አቅም ስለሌለው የሚጠየቅበት
ወይም ስልማይችል ከሶ ለማስቀጣት
እንደተለመደው ሁሌ እንደሚያደርገው
ብሶቱን መግለጫ መንገድ ስለሌለው
ለፈጣሪ ጌታ አሳልፋ ሰጥቶ
ኑሮውን ይገፋል ሁሉን ነገር ትቶ
Leave a Reply