ትልቅ ሰው ማን ይሆን ጥቅም የማይገዛው
በአላማ ፅናቱ የሚመሰገነው
ሰዎችን በእኩል አይን የሚመለከተው
አንዱን ወዳጄ ነው ሌላውን ጠላቴ ብሎ የማይፈርጀው
እባጸችሁ ሰዎች ትልቅ ሰው አሳዩኝ
እኔ ሳፈላልግ አመታት አለፉኝ
ሰውን መስማት እንጂ ማመን አይቻልም
ጥቅም ጸገኘበት ቢጤውን ከማጥፋት ወደኋላ አይልም
እገሌ አስተዋይ ነው በሳል ነው ለማለት
መስፈርታችሁ አይሁን የሚወጣው ሁሉ ከሰዎች አንደበት
ማጤን ያስፈልጋል በራስና ምላስ ያለውን ልዩነት
አንዳንዱ ብልጣብልጥ ጥሩ ምላስ ያለው
ብዙ ሳላወራ ጭራሽ የመስለዋል ሁሉም ሰው የሚያምነው
የዚህን አይነት ሰው ማንነት ለመንገር
ምንም አያስፈልግ ብዙ መመራመር
ተለዋዋጭ አቋም እንዳለው ለማወቅ
መፍትሄው ሌላ አይደለም ትንሽ ነው መጠበቅ
ሌላ ቀን ሄዳችሁ ብታነጋግሩት
ውይይት ብትከፍቱ ጥያቄ በማንሳት
ስለዚህ በፊቱ እንዲያብራራላችሁ ብትወተውቱት
በለመደው አፉ ብዙ ሲቀባዥር
ማስታወስ አይችልም ቆየት ያለ ነገር
መቅበጥበጥ ያበዛል ጭራሽ መደናበር
በማደበላለቅ ነገርን ከነገር
ማን ይሆን ትልቅ ሰው?
በጣም የተማረ ዲግሪ ያለው ነው?
በተሰጠው ስልጣን በጣም የሚኩራራው
ከደሃ ወገኑ ጉቦ የሚበላው
እውቀቱን አፍኖ ለጥቅሙ የቆመው
እውነትን በመጸድ አይኔን ግንባር ያርገው ብሎ የሚምለው
አዕምሮ የሌለው በሆዱ የሚያስበው
በወራዳ ስራው ፍፁም የማያፍረው
በየደረሰበት ስላዋቂቱ የሚያነበንበው
ስራው ከወሬው ጋር የማይገናኘው
ምሁር አሰዳቢው ገንዘብ አምላኩ ነው?
ወይስ በጀግንነት ብዙ ሰው በመግደል ሽልማት ያገኘው
በጨጸኝነቱ በሃላፊዎቹ የሚመሰገነው
ሰው ያልገደለን ሰው በጣም የሚንቀው
በሙሉ አፉ ደፍሮ የሚቆጥርላችሁ የገደለውን ሰው
ብጤውን በማጥፋት መሾም የለመደው
የሰውን ደም ማፍሰስ ደንታ የማይስጠው
ከመግደል በስተቀር ሌላ ህልም የሌለው
ትልቅ ሰው አይደለም ወታደር ተብየው
ማን ይሆን ትልቅ ሰው?
ፈሪሃ እግዚአብሄር ያለው
ጸለው ለሌሎቹ ቆርሶ የሚሰጠው
ግራውን ሲመታ ቀኙን የሚያዞረው
እስከማውቀው ድረስ ሃይማኖት አዋቂው አይደለም ሰባኪው
የሚያስተምረውን የማይተገብረው
በብቀላ ደዌ አዕምሮው የዞረው
በማስታረቅ ፋንታ ጠብ የሚያባብሰው
ያዳምን ዘር በአንድ አይን ፍፁም የማያየው
ሰውን በእምነት ጸራ የሚቦጫጭቀው
ጥላቻና በቀል ሁሌ የሚያስፋፋው
ትልቅ ሰው አይደለም ሀይማኖት ሰባኪው
ማን ይሆን ትልቅ ሰው?
በገንዘብ ተገዝቶ ፍርድ የማያዛባው
ለእውነት የቆመ በሀቅ የሚዳኘው
በዳይ ተበዳይን ለይቶ የሚያወጣው
ተገቢውን ቅጣት በአጥፊው ላይ የሚያዘው
ለሃሰት ምስክር እጁን የማይሰጠው
ህግን ለማስከበር ቆርጦ የተነሳው
ለባለ ስልጣኖች የማይበገረው
ፍርድን ለማጣመም መመሪያ ሲሰጠው
ተዉኝ አትጨቅጭቁኝ አልሰማም የሚለው
ለእውነት በእውነት ሁሌ የሚታገለው
እስከማውቀው ድረስ ዳኛው አይመስለኝም
ሳይኖረው የሚፈርድ ችሎታውም ልምዱም
በታዛዥነቱ ችሎት የሚሰየም
ያለማወላወል የተነገረውን ትእዛዝ የሚፈፅም
ፍትህን በመርገጥ ወንጀል የሚያፋፍም
ተበዳይን ቀጥቶ አጥፊን የሚሸልም
ከጥቅም በስተቀር የሌለው ሌላ ህልም
እንደ ጋሪ ፈረስ የማያይ ግራ ቀኝ
ከበላይ አጸላት ትእዛዝ ተቀብሎ ሰዎችን የሚዳኝ
ስራውን ለማጤን ፍፁም ያልታደለው
ከውሳኔ በፊት ያለቆቹን ፈቃድ ሁሌ የሚጠብቀው
የዳኝነት ሙያን በጣም ያረከሰው
ትልቅ ሰው አይደለም ፍርደገምድል ዳኛው
ማን ይሆን ትልቅ ሰው?
በእውቀት አባትነት እኩያ የሌለው
ጊዜና ጉልበቱን ለስራ የሚያውለው
መማር ማስተማርን በፍፁም ቅንነት እያስፋፋ ያለው
በመምህርነቱ ክብር የሚሰማው
ሁሉንም በእኩል አይን የሚመለከተው
ለተማሪዎቹ አርአያ የሚሆነው
እድገት ብልፅገናን የሚመኝላቸው
እንደግል ልጆቹ የሚሳሳላቸው
ፍፁም የማይሻ ጊዜያዊ ደስታውን
ብጥቅም ተታሎ የማይክድ እውነትን
ሁሌ የሚለግስ ያባትነት ምክሩን
ስለ መምህር ፀባይ መናገር ይከብዳል
አንዱ ሰክሮ ገብቶ በመጥፎ ጠረኑ ክፍሉን ያውደዋል
ለላኛው ቦዘኔ ከስራው ይቀራል
እንዲሁም ሌላኛው ረስቶ ሙያውን
ሲያባልግ ይገኛል የእውቀት ልጆቹን
ሙያውን አርክሶ አርክሶ አደራውን በልቶ
የእውቀት ልጆቹንም እድል አበላሽቶ
ምንም ሳይሰማው የሚኖር ተኩራርቶ
ስግብግብ አጋሰስ የሰው አራሙቻ
ሌት ተቀን የሚያስብ የሱን ደስታ ብቻ
ትልቅ ሰው አይደለም የዚህ አይነት መምህር
ቢቀር ይሻል ነበር ፍፁም ባይፈጠር
የንፁህ ልጆቹን እድል ከሚሰብር
Leave a Reply