እግዜርን እንደሰው (የጸቲት 1998)

ብልጣብልጡ ፍጡር የሰው ልጅ ቅጥ ያጣው

ምን ልሁን ብሎ ነው በፈጣሪ ሥራ ጣልቃ የሚገባው

ፍላጎቱን ሁሉ ስኬታማ እንደዲያደርግ የሚጨቀጭቀው

ችግር ሲያጋጥመው ምነው አንተ እያለህ ብሎ የሚወቅሰው

በደላው ጊዜ ግን እስከመኖሩ እንኳ የማያስታውሰው

በምን ምክንያት ነው ይህን የሚያደርገው

አምላክን እንዳሻው ሊያዘው የሚቃጣው

ይሉኝታን ረስቶ ለእኔ ብቻ የሚለው

በሥራ ምክንያት ወይም በግል ህይወት

ከሌሎች ሰዎች ጋር ባለው ግንኙነት

ፈጣሪ ሁልጊዜ ዘብ እንዲቆምለት

ሌሎችን በድሎ ለእሱ እንዲያደላለት

ይወተውተዋል ያለምንም እረፍት

ያ ያሰበው ጉዳይ የሚጨነቅበት

በአሉታዊም ሆነ በአወንታዊ መንገድ እስኪያገኝ እልባት

ልመናና ፀሎት ውጤት አላመጣ ብለው ሲያስቸግሩት

እራሱን ከአምላክ ጋር በእኩል አይን በማየት

ድርድር ይይዛል የጥቅም ውይይት

ልመናዬን ሰምተህ ጸሳጸህ እቅዴን

ፍጹም አልረሰሳውም ይህን ውለታህን

እኔም በተራዬ አቅሜ የሚፈቅደውን

እንዲህ ላደርግልህ እሰጣለሁ ቃሌን

ብሎ እንደሰው ልጆች ኃያሉ ፈጣሪን

በእራስ መውደድ ስሜት አሳንሶ ማየት

በጥቅም ለመግዛት ደፋ ቀና ማለት

በአንድዮሽ ድርድር መልስ አልባ ውይይት

አደራህን ማለት ደጋግሞ መወትወት

መጥፎ በሽታ ነው የሌለው መድሐኒት

ልክን ያለማወቅ የእራሱን ማንነት

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *