እሱው ይመልሰው (ጥር 1990)

ባልፈፀመው ወንጀል ጭራሽ በማያውቀው

ተከሰሀል ተብሎ ሰው መጥሪያ ሲሰጠው

ወይም ከባድ በደል አድርሰሀል የሚል ወቀሳ ሲደርሰው

ያጋጠመው ነገር ዱብዕዳ ሆኖበት ፍጹም ያልጠበቀው

ቅዠት እንጅ እውነት መስሎ አልታይ ሲለው

ለምን እንደሆነ ባልፈፀመው ድርጊት የተወነጀለው

ለማወቅ በመሻት በደንብ ሲፈትሸው የህይወቱን ሂደት

አልታይህ ሲለው አሳማኝ የሆነ እጥጋቢ ምክንያት

የዚህ ክስተት ምንጮች ሁለት ብቻ ናቸው ለሆኑ የሚችሉት

ወይ ውሸት በሆነ መረጃ ምክንያት የተሠራ ስህተት

አሊያም እንዲሁ በቅናትም ይሁን በመበቀል ስሜት

በደንብ ታስቦበት በተቻለ መጠን ሆን ብሎ ለመጉዳት

የተቀናበረ የጥፋት ተልዕኮ መሆን ነው ያለበት

ብሎ በመደምደም ለእራሱ ሁኔታ ከሁለቱ መሀል

የትኛው ምክንያት የበለጠ አሳማኝ ሊሆን እንደሚችል

አውጥቶና አውርዶ በደንብ አስቦበት

የጥፋቱን ዝርዝር እንዲሁም የክሱን አጠቃላይ ይዘት

ጊዜ ወስዶ በደንብ በጥልቀት በማጥናት

ስህተትን አመልጸች ምንም ፍንጭ ሲያጣበት

ተንኮል የወለደው እውነት የሌለበት

የሰዎች ፈጠራ መሆኑን አምኖበት

ለምን እንደሆነ ሆን ብለው ሊጎዱት ቆርጠው የተነሱት

መልሶ መላልሶ እራሱን ጠይቆት

ይኸ ነው የሚባል አሳማኝ ምክንያት

ማግኘት ሳይችል ሲቀር ግራ በመጋባት

ይኸ ሌላ አይደለም የእግዚአብሄር ቁጣ ነው

እራሱ እንዳመጣው እሱው ይመልሰው

ብሎ ሁሉን ነገር አሳልፎ ሰጥቶት

ጸጋጠመው ችግር እንዲገላግለው ይጀምራል ፀሎት

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *