ጽንፈኛው (ሐምሌ 1994)

የዘመናችን ሰው ስልጡን የተባለው

በፈጠራ ሥራ በጣም የመጠቀው

ሳይንስን በሰፊው ጥቅም ላይ ያዋለው

ከመቼውም በላይ ኑሮውን በእጅጉ በእቅድ የሚመራው

በወሳኝ ጉዳይ ላይ አቋሙን ማሳወቅ የግድ ሲኖርበት

በሰከነ መንፈስ በደንብ አስቦበት

ከሁሉም አቅጣጫ ጉዳዩን በሰፊው መርምሮ በጥልቀት

የኑሮው ነፀብራቅ ሆኖ የሚታይና ከልብ የሚያምንበት

በሌሎች ሰዎች ዘንድ እሱነቱ በደንብ የሚገለጽበት

አቋም መያዝ ሲችል ያለ ምንም ግፊት

በገሃድ ይታያል አዕምሮውን ስቶ ሲነዳ በስሜት

ማሰብ ማመዛዘን ነገሮችን ሁሉ በጥሞና ማየት

የእራስን ችሎታ ከሌሎች የበታች አድርጎ መመለከት

ወይም በሰዎች ፊት ታማኝነት ማጣት መስልው እየታዩት

የእኔ የሚለውን ሀይማኖትም ይሁን የፖለቲጸ እምነት

እንዲሁ በጭፍን ያለምንም መስፈርት

ከሌሎቹ ሁሉ በጣም የተሻለ ድክመት የሌለበት

ያለጥርጣሬ የሰው ልጅ በሙሉ መቀበል ያለበት

አማራጭ የሚባል የማይገኝለት

እንከን የለሽና ሙሉ በሙሉ እውነት

እንደሆነ አምኖበት ከልብ ተቀብሎት

ለዚህ ጉዳይ ብቻ ትኩረቱን በመስጠት

በአቋሙ በከፊል አሊያም በሙሉ የማይስማሙበት

እምነቱን የሚንድ ሀሳብ ሲያቀርቡለት

ወይም በመረጃ እየተደገፉ በጣም ሲሞግቱት

አሳማኝ የሆነ ሳይሰጥ በቂ ምክንያት

ሁሉንም በጅምላ ይፈርጃቸዋል በግል ጠላትነት

ይባስ ብሎ እንዲያውም በጣም በመቆጣት

ቁርጥ አቋም ይይዛል አንድ በአንድ ለማጥፋት

አመለጸከቱ እየተበረዘ ቀስ በቀስ በሂደት

ሰው የማያውቅለት ዱሮ ያልበረበት

የጥፋት ባህርይ ተጠናውቶ ይዞት

በሆነ ባልሆነው ብሰጭትጭት በማለት

ከመናገር በቀር የሌሎችን ሀሳብ በትዕግዕስት ለመስማት

ወይም እነደገና የያዘውን አቋም ለመፈተሽና በጥልቀት ለማየት

ፍጹም የማይፈቅድ አዕምሮው የሞላ በመበቀል ስሜት

ቅንጣት ታህል እንኳን ርህራሄ የሚባል የማይታይበት

ከሰው የተለየ እንደ ሌላ ፍጡር የሚቆጠርበት

ብዙ ምልክቶች እየታዩ ሄደው ቀስ በቀስ በሂደት

ስብዕናው ተማ*ጦ እየነዳው ስሜት

ሲሳተፍ ይታያል በአሳፋሪ ድርጊት

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *