ታላቁ ፈጣሪ ታጋሹ አምላጸችን
እኛን ልጆችህን የምታይ በእኩል አይን
ፍርድህን የምትሰጥ እንደየሥራችን
ድፍረት ባይሆንብኝ እስኪ ልጠይቅህ
እስከነጭራሹ የለህም እያለ ህዝብ ፊት የጸደህ
ሥራህን በሙሉ የሚያንቋሽሽብህ
የሰዎች ፈጠራ አድርጎ የሚያይህ
የአንተ ተከታዮች ወይም አማኞችህ
ፀጋ እንዳያገኙ በነፃ አምልከውህ
ወከባና ጫና የሚያበዛባቸው አንተን እንዲክዱህ
እንዲያው በአጠቃላይ የሚፈታተንህ
እራሱን አዋቂ አድርጎ የሚያየው የዚህ አይነቱ ሰው
ሊወጣው የማይችል ችግር ሲያጋጥመው
ክመጨነቅ ብዛት ሲተክዝ ለብቻው
ዙሪያው ገደል ሆኖ መፍትሔ አልታይ ሲለው
ወደ አንተ በመዞር አለሁ እንድትለው
ከገባበት ችግር እንድታላቅቀው
ልመናውን ቢያቀርብ እንድትታደገው
አትታዘበውም ይህን አይነቱን ሰው?
ምንስ ይሰማሀል በድንገት ተነስቶ ሲንበረከክልህ
በተስፋ ተሞልቶ ጓጉቶ ሲጠብቅህ
ድረስልኝ የሚል የጭንቀት ጥሪውን ልመናውን ሰምተህ
ጥፋቱን በሙሉ እርግፍ አርገህ ትተህ
አለሁ ትለዋለህ እጅህን ዘርግተህ?
ሰው ሲቸገር አይተህ ፈፅሞ መጨከን ስለማይሆንልህ
አልጠራጠርም ቀና ይዘት ያለው እንደሚሆን መልስህ
በገሀድ የሚያሳይ ወሰን እንደሌለው ይቅር ባየነትህ
ድፍረት ባይሆንብኝ እስኪ ልጠይቅህ
የሰውን ልጅ በውነት ከፈጠርክ በአምሳያ
ከቶ ለምን ይሆን በድርጊቱ ሁሉ አንተን የማይመስልህ
ሚስጥሩ ምንድነው እንዳንተ ቸርና ይቅር ባይ እንዲሆን ማድረግ የተሳነህ
ወይስ ሆነ ብለህ የሰውን ከንቱነት ማሳየት ፈልገህ
በቂም በቀልና በተንኮል ሲዘፈቅ ዝም ብለህ ታያለህ
Leave a Reply