ዛሬ በዚህ ዘመን ሰለጠን ባልንበት
አገሮች በሙሉ በመረጃ መረብ በተሳሰሩበት
የትም ይሁን የትም በአራቱም ማዕዘናት
የሰዎችን ስሜት ሊስብ እንደሚችል የሚታመንበት
አዲስ ክስተት ሲታይ ወዲያው ከመቅጽበት
የአለም ህዝብ እንዲያውቀው በሚደረግበት
ሚዲያው ፈርጥሞ እራሱን የቻለ መንግስት በሆነበት
አለም ተጥለቅልቃ በመረጃ ፍሰት
ጠባብ መንደር ሆና በምትታይበት
እውነትን መደበቅ በማይቻልበት
በጋዜጠኝነት ህይወትን ለመምራት
በራሱ ብቻውን በቂ አይደለም ትምህርት
ሙያው ይጠይቃል በጣም ብዙ መስፈርት
ጥሩ ጋዜጠኛ ሆኖ ለመገኘት
ጥልቅ የሙያ ፍቅር ችሎታና ብቃት
በራስ መተማመን የአስተሳሰብ ብስለት
መልጸም ስነምግባር ቅን አመለጸከት
በገለልተኛነት መረጃን ማጣራት
እውነቱን ፈልፍሎ አበጥሮ ማውጣት
አቋምን ግልጽ አርጎ በአላማ በመጽናት
ለዛቻ ለጫና ወይም ማስፈራራት
ፍንክች ያለማለት እጅን ያለመስጠት
ያለማንም ግፊት ሥራን አውቆ መሥራት
አመለጸከትን ወይም የራስን እምነት
ከሙያው ነጥሎ ለይቶ መመልከት
ጊዜን ወስዶ አስቦ በደንብ ማመዛዘን ውሳኔ ለመስጠት
ይህንን ሁሉ ነው ማሟላት ያለበት
የእውነት ጋዜጠኛ መሆን የሚፈልግ በዚህ በታሪክ ወቅት
የህዝብ ከበሬታን እምነቱን ለማግኘት
እራስን ነፃ አርጎ ከወገንተኛነት
የሰውን ልጅ ሁሉ በእኩል አይን በማየት
የግል ፍላጎትን ስሜትን በመግታት
በሰከነ መንፈስ ረጋ በማለት
ምንም ያልተዛባ ዘገባ በመሥራት
ሁሌም ሚዛናዊ ሆኖ በመገኘት
ጥብቅና በመቆም ለሀቅና ለእውነት
ማስመስከር ይገባል የእራስን ማንነት
Leave a Reply