መገናኛ ብዙሀን (መስከረም 1996)

በደንብ ስንፈትሸው የታሪክን ሂደት

እድል ሰምሮላቸው ስልጣን የሚይዙት

ቶሎ ተሽቀዳድመው ትኩረት የሚሰጡት

መገናኛ ብዙሀን ተብለው የሚጠሩት

በቁጥጥራቸው የሚውሉበትን ዘዴ ማመቻቸት

እንደሆነ ማወቅ ይቻላል መረዳት

ስልጣን ተረክበው በእጃቸው ያስገቡት

ከማስ ሚዲያው ጋር በቅርበት በመሥራት

ሲፈጥሩ ይታያል በጣም ጥብቅ ቁርኝት

ባመኑበት መንገድ ሥራ ላይ ሲያውሉት

እንዳስፈለጋቸው እንደልብ ሲያዙበት

ያለተቀናቃኝ ጠቅልለው ይዘውት በባለቤትነት

ቀይደው አፍነው ነፃነቱን ሁሉ በሙሉ ገፈውት

የእነሱ ፍላጎት የሚጠበቅበት

ለሌሎች ግን መጥፊያ መሣሪያ አድርገውት

ያልሆነውን ሆነ ብለው በማስወራት

ተቀናቃኞችን ለመወንጀል በሀሰት

በሰበብ አስባቡ ሰላም ለማሳጣት

አልያም ሆን ብለው በመበቀል ስሜት

ጥሩ ሥማቸውን በተንኮል ለማጥፋት

ፍላጎታቸውን ለማሳጸት ብቻ ጥቅም ላይ ሲያውሉት

ይህን መጥፎ ድርጊት ከምንም አይቆጥሩት

ከዚያም አልፈው ተርፈው የሚዲያውን ሰው

እንዳሻቸው ታዛዥ ፍጹም ታማኛቸው

ሊሆን ይገባዋል የሚል እምነት ይዘው

በማዋከብ ብዛት ፋታ በማሳጣት

በእራስ መተማመን ወይም የሙያ ፍቅር የማይታበት

የሚፈልጉትን ብቻ የሚሠራ ሲያድርጉት ሮቦት

ስብእናው ተገፎ ሲፈራረቁበት ትዝብትና ንቀት

እርሱነቱ ቀርቶ ተላብሶ ይወጣል ሌላ አዲስ ማንነት

የዚህ አይነቱን ሰው የራሱ የሆነ አቋም የሌለውን

ሌሎች እንዳሻቸው አርገው የሚያዙትን

ፈርቶ የሚያስፈራራ ሆኖ የሚታየውን

ይሉኝታ የሚባል ያልፈጠረበትን

በሚዲያው ሥራ የተሰማራውን

ይህን ባለሙያ በደንብ ቀርቦ የሚያየው

በጤነኛ አዕምሮ የሚያስብ ማንም ሰው

ፈርጀ ብዙ ችግር ሰቅዞ እንደያዘው

ጊþዜ አይወስድበትም ይረዳዋል ወዲያው

ባህርይውን በደንብ ሲያጠናው በጥልቀት

እንደፈለጋቸው ሰዎች የሚነዱት

አስቦ የማይሰራ ይህን አርግ ጸላሉት

ጨርሶ የሌለው በእራሱ ላይ እምነት

በፍርሀት ተውጦ የወረረው ጭንቀት

መሆኑን ሲረዳ ውስጣዊ ባህርይው

የተለየ ፍጡር አርጎ ነው የሚያየው

ሙያዊ ግዴታን ወደጎን በማለት

የህዝብን የማወቅ መብት በግልጽ በመጋፋት

ስነምግባር ጥሶ ሆን ብሎ ማሳሳት

አውቆም ይሁን ሳያውቅ እንዲሁ በስህተት

በተደጋጋሚ ለሚያጠፋው ጥፋት

ማግኘት የተሳነው አጥጋቢ ምክንያት

በሚያደርገው ድርጊት ቅር የተሰኘበት

የህብረተሰብ ክፍል አስቦ መክሮበት

ሥም ያወጣለታል ተገቢ የሚለውን

ቁልጭ አርጎ የሚገልጽ ጠቅላላ ድርጊቱን

ምንም እኚህ ስሞች በርጸታ ቢሆኑም

ሁሉንም መዘርዘር ፍጹም አይቻልም

ስለዚህ ጥቂቱን መርጠን ስናያቸው

ዋናዋናዎቹ ከዚህ በመቀጠል የቀረቡት ናቸው

በሆዱ የሚያስብ ጥቅም የሚገዛው

ምግባረ ብልሹ አላማ የሌለው

ቆርጦ ቀጥል ዋሾ ትዕቢት የወጠረው

ከእርሱ በቀር ጮሌ ያለ የማይመስለው

ውሸት ሲያንጎደጉድ አፉን የማይዘው

አመዛዝኖ ማየት በፍጹም የማይችል

በብልጣብልጥነት ህዝብን የሚያታልል

ሁሌ የሚመስለው የማይነቃበት

ከአፉ የማይወጣ ምንም አይነት እውነት

ህዝብ አንቅሮ ተፍቶት የሚያየው በንቀት

ማንም የማይፈቅድ እምነት ሊጥልበት

ማሰብ የተሳነው ባዶ የወሬ ቋት

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *