መሬት ልጠይቅሽ ንገሪኝ ግልፅ ሆነሽ
የሰው ልጆች ሁሉ የኔ ናት የኔ ናት የኔ ናት የሚሉሽ
ለምን እንደ ሆነ ሚስጢሩን ታውቂያለሽ?
ወይስ ለምን ይሆን ሰዎች በአንች ፍቅር ቶሎ የሚያዙት
ከዚያም አልፈው ተርፈው የሚያስቡበትን አዕምሮ የሚስቱት
ይሉኝተታን አውልቀው እርቃን የሚቆሙት
በአንች የተነሳ ከመጣላት አልፈው የሚገዳደሉት
ከቶ ለምንድን ነው ከሰውነት አልፈው እንስሳ የሚሆኑት?
እኔ አልጠይቅሽም ስለባለቤትሽ
ከልብ ስለማምን የሁሉም እንደሆንሽ
ለአዳም ዘር በሙሉ አምላክ የፈጠረሽ
ተጨንቆ ተጠቦ በደንብ ያዘጋጀሽ
ከልደት እስከ ሞት እንዲጠቀሙብሽ
አስቦ እንደሆነ ግልፅ ጸልሆነልሽ
ልንገርሽ እወቂው ይኸው ነው ግዴታሽ
ለሰዎች ተቆርጦ እድሜ ሲሰጣቸው
የሚፈልጉትን ፍሬ እንድትሰጫቸው
ተንከባክበሽ ይዘሽ እንድታኖሪያቸው
ጊዚያቸው ሲፈፀም የተጻፈላቸው
እቅፍ አርገሽ ይዘሽ እንድትደብቂያቸው
የዘለአለም እንቅልፍ የሚያንቀላፉብሽ እንድትሆኝ ቤታቸው
መሆኑን አትርሽ ዋነኛው ተግባርሽ ከአንች የሚጠበቀው
የአንችን ሀላፊነት በደንብ ላስተዋለው
የተፈጥሮን ሚስጥር በግልጽ ነው የሚያሳየው
ሁሉም ሰዎች በእውነት እኩል መሆናቸው
ያለጥርጣሬ የሚረጋገጠው
ህይወታቸው አልፎ ሲቀር በድናቸው
ሆድሽን ክፍት አርገሽ ስትደብቂያቸው ነው
ታዲያ ይህ ከሆነ የሚጠበቅብሽ
እስኪ ልጠይቅሽ የማን ነኝ ትያለሽ
በእውነት ሁሉንም በእኩል አይን ታያለሽ?
ወይስ እንደ ሰው ልጅ አድልኦ ታውቂያለሽ
አንዱ ተደስቶ ሌላው ሲከፋብሽ
በግዴለሽነት ዝም ብለሽ ታያለሽ?
ህይወቱ ጸንች ጋር ትስስር ሳይኖረው
በአንች ላይ ለማዘዝ ስልጣኑ ያለው ሰው
ያለብዙ ድጸም የምትሰጭው ጥቅም ሰለሚያስጎመዝው
ስለአንች ለማሰብ ጊዜውም አይኖረው
ሁሌ አምጭ ነው እንጅ አንዴም እንች አይልሽ
ያለሽን ጠራርጎ ባዶ ነው የሚያስቀርሽ
በምንኖርበት በዚህኛው ዘመን
ፖለቲከኞቹ እኛን የሚመሩን
ጎራ በመለየት በስፋት ክርክር የሚያጸሂዱበት
የልዩነታቸው ትልቁ ምክንያት አርገው የሚያቀርቡት
የመሬት ባለቤት ማን መሆን አለበት
ለሚለው ጥያቄ መልስ ነው የሚሉት
የግል ወይ የመንግሥት መሆን ይገባዋል
የሚል አቋማቸው እየሆነ መጥቷል
በደንብ ስንመረምር የታሪክን ሂደት
መንግስት ተቆጣጥሮ መሬትን ሲያዝበት
የተፈለገውን አያመጣም ውጤት
የቀሰምነው ትምህርት በሠላሳ ዐመት ውስጥ
በቂ ማስረጃ ነው እንደሚያስፈልግ ለውጥ
ገጠሩ እንዲለማ እንዲያድግ በፍጥነት
የአርሶ አደሩም ኑሮ እንዲሻሻልለት
መሬት ለአራሾቹ መሰጠት አለበት
Leave a Reply