ጊዜ (ነሐሴ 1994)

ጊዜ ያነሳውን ጊዜ እንደሚጥለው

ይህንን ቁምነገር መረዳት ያቃተው

ግራቀኙን ሳያይ በስሜት ተነድቶ

እራሱን ከፍ አርጎ ሌሎችን አጥላልቶ

የእኔ ሃስብ ፍፁም ነው እንከን አይወጣውም

ብቸኛ ነውና አማራጭ የለውም

ያለምንም ትችት ሁሉም ይቀበለው

ትኪ የማይኖረው ገዥ አርጎ ይውሰደው

በማለት ሰዎች ላይ ሃሳቡን ሲጭነው

ጊዜን ተገን አርጎ በሙሉ ልቡ ነው

ጊዜ የከዳቸው አቅም ያነሳቸው

ልሳናቸው ታስሮ ሰሚ የሌላቸው

ስለተቀበሉት አርገው ግዴታቸው

ትክክል መሆኑን ሁሌ ባለ ጊዜው

በፍፁም አይደፍሩም ተሳሳትህ ለማለት

ወይም አይሞክሩ ጥያቄ ለማንሳት

ግዴታ ነውና እንዳመጣባቸው

ማሰብ እየቻሉ አዕምሮ እያላቸው

ያጎበድዳሉ በፍርሃት ተውጠው

እየተቀበሉ ሁሉን አሜን ብለው

አንድ ቀን እስኪቆም ጊዜ ከጎናቸው

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *