እኛ ነን (ሰን 2016)

ለአገሬ መበጥበጥ ለሰላም ማጣቷ
እኛ ነን ልጆቿ ጦስና ውጋቷ

በሆነ ባልሆነው ነገር እየፈተልን
ፖለቲካ አረግነው ይኸው ኑሯችንን

እኛን ፍፁምና ከሃጢያት የነፃን
እንከን የሌለብን አድርገን አየሳልን

ሌሎችን በመውቀስ ጥላሸት ስንቀባ
ግልጽ ማሳያ ነው ተራ እንደሆንና እንደማንረባ

ሁሉም በየጎራው እየተካሰሰ
የስንቱ ምስኪን ደም በክንቱ ፈሰሰ

በመቶ ሺዎቹ የሰው ህይወት ጠፍቶ
በሚልዮኖቹ የሚቆጠር ዜጋ ከቀየው ተገፍቶ
አሁንም አላቆምን ፉከራ ቀረርቶ

ሁሌም ፀሎቴ ነው ልቦና እንዲሰጠን
ከዚህ እብደት ወጥተን እንደ ሰው እያሰብን
እንድንታደጋት ውድ አገራችንን

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *