የለውጥ አዙሪት (ሐምሌ 2016)

እስራት ግድያ ግፍና ጭቆና

ህገወጥ አሰራር ጉቦና ሙስና

የነፃነት እጦት የመብት አፈና

ይሉኝታ ቢስነት ፍፁም ውንብድና

በበደል ላይ በደል ተከማችቶ ሞልቶ 

ዙሪያው ገደል ሆኖ መፍትሄ ‘ሚባል ጠፍቶ

ህዝቡ ትግዕስቱ አልቆ ሆ ብሎ ተነስቶ

ስርአቱን ሲጥለው ከአናቱ ጎትቶ

ገዥዎች ከስልጣን ተገፍተው ሲለቁ

ለአደረሱት ጥፋት በህግ ሲጠየቁ

ሁሉም መስሎት ነበር አዲስ ቀን የመጣ

ከእስከፊ ባርንት አርዕነት የወጣ

በዚይ በአፍላው ዘመን ሁሉም በለውጡ ኃይል እንደተጎተተ 

በደስታ ሰክሮ አቅሉን እንደሳተ

ማንም ያልጠበቀው ነገር ተከሰተ

በአዲስ መሪዎቹ የተሰጠው ተስፋ

የዜጎችን ህይወት መለወጥ መቻሉ ሳይታይ በይፋ 

እንደ ጉም በፍጥነት ብን ብሎ ሲጠፋ 

ህዝቡ ስለገባው አካሄዱ ሁሉ እንደሌለው ፋይዳ

ማድፈጡን ቀጠለ ነገሩ በሙሉ ሆኖበት ዱብ ዕዳ 

ድምጹን ጥፍት አርጎ ለሌላ ዙር ትግል እየተሰናዳ

እንደ ገለልትኛ ታዛቢ ግለሰብ 

ስለሆነው ሁሉ በጥሞና ሳስብ 

ትሻልን ሰድጄ ትብስን አመጣሁ

ብዬ እንደ አባቶቼ እየተረትኩ አለሁ

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *