Tag: short

  • የፖለቲካ ሞት (የካቲት 2017)

    የፖለቲካ ሞት ብሎ ሰው ሲናገር
    ትርጉሙ ፈጽሞ አይገባኝም ነበር
    ለካስ መተፋት ነው ተንቆ መወርውር
    ያለምንም ሰሚ ሞትላይቀር ማንቋረር

  • እንባ (መጋቢት 2017)

    የአብሮ አደጌ አፈራ እሸቱ ቀብር ላይ የታዘብኩት

    ሀዘን ምናባቱ የሰው ቅስም ይሰብራል
    ፊትን በእንባ አርሶ አንጀትን ያቆስላል
    እንባስ ወጥቶ ፈሶ ደርቆ ይታጠባል
    ስሜት ነው ታምቆ ቆሽትን የሚያቃጥል

  • የሚአሸብረው ሥም (ግንቦት 2007)

    ጅግናው አባኮስትር የሶማው አንበሳ

    በአገሩ ጉዳይ ለነፍሱም አይሳሳ

    ጠላት እሱን በአካል እይቶት ይቅርና

    ብርክ ነው የሚይዘው በላይ ሲባል ገና

  • በላይ ከላይ ሲሆን (ጥር 2014)

    ምን ሃሳብ አለበት ምን ይሆናል ፋኖ

    የጦር ምትሃተኛው በላይ ከላይ ሆኖ

  • በላይ ማርና እሬት (ግንቦት 2008)

    አባኮስትር በላይ የጦሩ መድሃኒት

    ለወዳጆቹ ማር ለጠላቶቹ እሬት

    ያንገበግበኛል የሱ በግፍ መሞት

    ሁሌም ፀሎቴ ነው እንዲቀለው መሬት

  • ያለስስት መስጠት (ሐምሌ 2004)

    ስንቱ ባለፀጋ ሀብትና ንብረቱን ለልጆቹ ሲያወርስ

    አባኮስትር በላይ ተጨንቆ የማያውቀው ስለ ምድራዊ ቁስ

    ምንም እድሜው ቢያጥር በግፍ በአደባባይ ህዝብ ፊት ተስቅሎ

    ስምና ሥራውን ትቶ ነው ያለፈው ለድፍን ኢትዮጵያ ያውላችሁ ብሎ

  • እጅ መንሳት (ጥቅምት 2016)

    በዚህ በእኛ ዘመን በስልጣን ላይ ያሉት

    ለአገር በማሰብ ሳይተኙ የሚያድሩት

    ትውልዱ ባህሉን ረስቷል በማለት

    እያስተማሩን ነው ይኸው እጅ መንሳት 

  • የንግድ ሥራ (ጥቅምት 2016)

    ንግድ ሙያ እራሱ አለው ልዩ ጥበብ

    እየገዙ መሸጥ በሂደት መጨመር በገንዘብ ላይ ገንዘብ

    በዚህ በኛ ዘመን የሸቀጦች ዋጋ ስለተወደደ 

    ፈተናው ብዙ ነው መግዛት የለመደ