Tag: Family

  • እህቴ (ታህሳስ 1999)

    ከቼርች እንደመጣሁ እሁድ ቀን ከስአት

    ከጓደኞቼ ጋር በጭቃ ስጫወት

    ጥሩ ቤት ሰርቼ እህቴን ባስቀናት

    እንደ እኔ ቆንጆ ቤት መሥራት ስለአቃታት

    በጣም ተበሳጭታ ምንም ሳላስበው

    ያን የመሰለ ቤት በእግሯ አፈረሰችው

    እኔም ተናድጄ በእሷ መጥፎ ድርጊት

    ተንደርድሬ ስሄድ በዱላ ልመታት

    አባቴ ስለአየኝ አለኝ እንዳትነጸት

    ምክሩን ተቀብዬ ስመለስ በፍጥነት

    እሷን ጠራትና እንዲህ ሲል መከራት

    በጣም ያሳፍራል ያጠፋሽው ጥፋት

    የሱን ቤት ማፍረስሽ ተነስተሽ በቅናት

    ከአንች አይጠበቅም የዚህ አይነት ድርጊት

    አሁንም ቶሎ በይ ይቅርታ ጠይቂው

    የዚህ አይነት ጥፋት አይለምደኝም በይው

    በመጸከላችሁ ሰላም የሚወርደው

    ጥፋተኛነትሽን ስተቀበይ ነው

  • ትምህርት፣ጨዋታ፣ እናት፣ ሳንቡሳ (ህዳር 1999)

    በጠዋት ማለዳ ቁርሴን እንደበላሁ

    ወደ ትምህርት ቤት በቶሎ እሄዳለሁ

    ከክፍል ስወጣ ጨርሼ ትምህርቴን

    እጫወተዋለሁ ያን ዥዋዥዌዬን

    ከቤቴ ስወጣ ጠዋት በማለዳ

    እናቴን አየሁዋት ውሀ ስትቀዳ

    ቁርስ ብላ ብላ ሰታቀርብልኝ

    ይህን ስላለችኝ እኔም ደስ አለኝ

    በጠዋት ማለዳ ከቤቴ ስወጣ

    እናቴን አየኋት ወደ እኔ ስትመጣ

    እንኳን መጣሽልኝ ብዬ ሄጄ ሳቅፋት

    እሷም በእኔ ድርጊት ደስታ ተሰማት

    ከዚያም ቀስ ብላ እጇን ስታሳየኝ

    ለጸስ ሳንቡሳ ነው የመጣች ይዛልኝ

  • እናቴ ሜልዬ አባቴ በላይ

    ሜላት መንግስቱ ጌዲዮን በላይ ጸሣ

    እናቴ ሜልዬ አባቴ በላይ

    ነስንሴ መሆኔን ታውቃላችሁ ወይ?

    ማንም የማይችለኝ ጀግና ስለሆንኩኝ

    የክፍሎቼ ልጆች በጣሙን ቀኑብኝ

    አንዳንዴ ለስናኬ በርበን እየበላሁ

    የብዙ ልጆችን ለሀጭ አስመጣለሁ

    ሌላ ጊዜ ደግሞ ስገምጥ ቸኮላት

    አጸፍለን እያሉ ይነሱኛል እረፍት

    በዚህ የተነሳ አንድ ቀን ሆን ብዬ

    ጊሮ ሰጠሁዋቸው እንኩ ብሉት ብዬ

  • ዳዊት (ሐምሌ 1997)

    ያ ዳዊት መንግስቱ የጅጅጋው ወጣት

    ፍቅር አይነጸኝም ብሎ ባወራበት

    በዚያው በምላሱ ሴት ሲለምንበት

    በጣም ያስደስታል ሲያለቅስ መመልከት

    የተናገረውን ጭራሹን ረስቶት

    ህይወቱን ከሴት ጋር ይኸው አቆራኝቶት

    ብሞት ይሻለኛል ሰላምን ከማጣት

    እያለ ያወራል ያለምንም ሀፍረት

    ቋንቋው ተቀይሮ ሰላም ብቻ ሆኗል

    ዘመድ መጠየቁን ጭራሹን አቁሟል

    በስልክ እንዳይገኝ ስልኩ እየደወለ ዝም ብሎ ያየዋል

    እሷ ስትደውል ቶኑን ይለየዋል

    ሮጦ ተነስቶ ቶሎ ያነሳዋል

    የእሷን ድምጽ መስማት ደስታ ይሰጠዋል

    ቶሎ ነይ እኔ ጋ እያለ ደጋግሞ ግብዣውን ያቀርባል

    እንዲያው በአጠቃላይ እጁን ለእሷ ሰጥቷል

    ይህ አዲስ ፀባዩ ማንም የማያውቀው

    ወዳጅ ዘመዶቹን ምንም ቢገርማቸው

    ለእሱ የጠበቀ ፍቅር ስላላቸው

    ይለምኑለታል ፈጣሪን ደጋግመው

    ሁለቱን ፍቅረኞች እንዲባርጸቸው

    በትዳር ሰንሰለት እንዲያቆራኛቸው

    ሁሉም የሚያውቀው ሰው ለእሱ የሚመኝለት

    ልቡን የሰወረው ይህ የፍቅር ህይወት

    በደንብ የሚያረጸው ደስታ የሚያስገኝለት

    ምንም አይነት ችግር የማያመጣበት

    ፍላጎቱ ሁሉ የሚፈፀምበት

    ወልዶ የሚስምበት ሰላም የሞላበት

    እንዲሆንለት ነው ጥሩ የሚባል ህይወት

    ከ ወ/ሮ ሜላት መንግስቱ እና ከ ፕ/ር በላይ ጸሣ

  • እናት (መጋቢት 2000)

    የትውልድ መሠረት

    የፍቅር የውበት የደስተኛነት

    የተስፋ የብርታት የአርቆ አሳቢነት

    የሰላም የትግዕስት የሆደ ሰፊነት

    የንፁህ ልቦና የይቅር ባይነት

    ሰዎችን የማክበር ፈጣሪን የመፍራት

    ግራ ቀኝ የማየት ፍፁም ጠንቃቃነት

    የጥሩ ስብዕና በቃል የመገኘት

    የእኔ አለሁ ባይነት ቁም ነገረኛነት

    የመልካም ባህርይ የጥሩ ዳኝነት

    ያለማወላወል ውሳኔ ሰጪነት

    የህይወት ፈር ቀዳጅ መልካም መምህርነት

    ጊዜ የማይሽረው የልብ ወዳጅነት

    የመስዕዋትነት ቀድሞ የመገኘት

    የደግነት የእምነት የፍፁም ቅንነት

    የማስተዋልና እንዲሁም የፅናት

    መተኪያ የሌላት ጥሩ ምሳሌ ናት

  • ልጅ ወላጅ ሲያስተምር (ታህሳስ 2017)

    እዚህ አሜሪካ ወገኖቻችንን ሳያቸው በቅርበት
    ሁሌም ይገርመኛል ከልጆቻቸው ጋር ያላቸው ተግባቦት

    በቋንቋ በራዕይ በአስተሳሰብ ሁሉ
    ልጆች ከወላጆች በጣም ይለያሉ
    አብረው አየኖሩ ልጄ ወላጆቼ እየተባባሉ
    የሁለት አለም ሰው መስለው ይታያሉ

    ወላጆች ተነስተው በፈረንጅ ቋንቋ እንድ ነገር ሲሉ
    ልጆት ቶሎ ብለው እርምት ይሰጣሉ

    ምን ነካህ አባዬ ምን ነካሽ እማዬ
    ስንቴ ነገርኳችሁ እንደዚህ አይደለም የሚባለው ብዬ

    እያሉ ንትርክ ጭቅጭቅ ሲፈጥሩ
    ግራ ግብት ይላል በእውነት ነገሩ

    እንዲህ ያለ ዘመን የተገላቢጦሽ ግራ የሚያጋባ
    ልጆች ወላጆችን የሚያስተምሩበት በነጋ በጠባ