Tag: 2016

  • እኛ ነን (ሰን 2016)

    ለአገሬ መበጥበጥ ለሰላም ማጣቷ
    እኛ ነን ልጆቿ ጦስና ውጋቷ

    በሆነ ባልሆነው ነገር እየፈተልን
    ፖለቲካ አረግነው ይኸው ኑሯችንን

    እኛን ፍፁምና ከሃጢያት የነፃን
    እንከን የሌለብን አድርገን አየሳልን

    ሌሎችን በመውቀስ ጥላሸት ስንቀባ
    ግልጽ ማሳያ ነው ተራ እንደሆንና እንደማንረባ

    ሁሉም በየጎራው እየተካሰሰ
    የስንቱ ምስኪን ደም በክንቱ ፈሰሰ

    በመቶ ሺዎቹ የሰው ህይወት ጠፍቶ
    በሚልዮኖቹ የሚቆጠር ዜጋ ከቀየው ተገፍቶ
    አሁንም አላቆምን ፉከራ ቀረርቶ

    ሁሌም ፀሎቴ ነው ልቦና እንዲሰጠን
    ከዚህ እብደት ወጥተን እንደ ሰው እያሰብን
    እንድንታደጋት ውድ አገራችንን

  • የህልም እንጀራ (ግንቦት 2016)

    አልጨበጥ አለኝ መላ ቅጡ ጠፋኝ
    ህልሜ አልያዝ ብሎ ስደርስ እየራቀኝ

    ይኸው አገኘሁት ያዝኩት ብዬ ሳስብ
    ጭራሽ ይርቀኛል አጠገቡ ስቀርብ

    ምን ያህል ቢያስጎመጅ ሊበላ እንደማይችል
    የልም እንጀራ ትርጉም ይኸው ግልጽ ሆነልኝ

  • የእውቀት ትውልድ (ግንቦት 2016)

    ይኸ ተርብ ትውልድ እውቀት የተጠማ
    በፍጥነት ለመውጣት ወደ ስኬት ማማ
    ለትምህርት ያውላል ያለውን በሙሉ ምንም ሳያቅማማ

    ጊዜ ይሁን ገንዝብ ወይም ሌላ ሙያ
    መስዕዋት ያደርጋል ለአላማው ማሳኪያ

    ኮሌጅ ውስጥ ገብቶ ጠንክሮ እየሠራ
    ቢጤውን ፈልጎ እየተሰለፈ በመረጠው ጎራ
    ሁሉም ሰቃይ ሆኗል ለሌላ ‘ማይራራ

  • እራስን ጥየቃ (ሐምሌ 2016)

    የእኔ ምሁር መባል ዲግሪ መጫኔ
    ምንም ካልጠቀመ ለአገር ለወገኔ

    ፊድል ካልቆጠሩት ምስኪን ወገኖቼ
    አርቄ ካላሰብኩ ስልጣንን ፈርቼ

    በተናገርኩ ቁጥር ማን ይሆን የሰማኝ እያልኩ እንዳልቆዝም
    ግራ ቀኜንና ፊትና ሁዋላየን ማማተር እንዳቆም

    ሰው ሆኜ ለመኖር በቀሪው ህይወቴ
    የነፃነት አየር መትንፈስ እንድችል እንደ ልጅነቴ

    ልሂድ ወደ ቀዬ ወደ ዘመዶቼ
    ቢያንስ ይወጣልኛል እንደልቤ አውግቼ
    ምንም አልፈየድኩም እዚህ ተጎልቼ

  • የለውጥ አዙሪት (ሐምሌ 2016)

    እስራት ግድያ ግፍና ጭቆና
    ህገወጥ አሰራር ጉቦና ሙስና
    የነፃነት እጦት የመብት አፈና
    ይሉኝታ ቢስነት ፍፁም ውንብድና

    በበደል ላይ በደል ተደራርቦ ሞልቶ
    ዙሪያው ገደል ሆኖ መፍትሄ ‘ሚባል ጠፍቶ
    ህዝቡ ትግዕስቱ አልቆ ሆ ብሎ ተነስቶ
    ስርአቱን ሲጥለው ከአናቱ ጎትቶ

    ገዥዎች ከስልጣን ተገፍተው ሲለቁ
    ለአደረሱት ጥፋት በህግ ሲጠየቁ
    ሁሉም መስሎት ነበር አዲስ ቀን የመጣ
    ከእስከፊ ባርንት አርዕነት የወጣ

    በዚያ በአፍላው ዘመን ሁሉም በለውጡ ኃይል እንደተጎተተ
    በደስታ ሰክሮ አቅሉን እንደሳተ
    ማንም ያልጠበቀው ነገር ተከሰተ

    በአዲስ መሪዎቹ የተሰጠው ተስፋ
    የዜጎችን ህይወት መለወጥ መቻሉ ሳይታይ በይፋ
    እንደ ጉም በፍጥነት ብን ብሎ ሲጠፋ

    ህዝቡ ተጠራጥሮ አካሄዱ ሁሉ እንደሌለው ፋይዳ
    ማድፈጡን ቀጠለ ነገሩ በሙሉ ሆኖበት ዱብ ዕዳ
    ድምጹን ጥፍት አርጎ ለሌላ ዙር ትግል እየተሰናዳ

    እንደ ገለልትኛ ታዛቢ ግለሰብ
    ስለሆነው ሁሉ በጥሞና ሳስብ
    ትሻልን ሰድጄ ትብስን አመጣሁ
    ብዬ እንደ አባቶቼ እየተረትኩ አለሁ

  • ይች ናት አገሬ (ሰኔ 2016)

    ይች ናት አገሬ የማይታይባት ሰው በሰውነቱ
    የሚፈረጅባት በዘሩ በቋንቋው ወይ በሃይማኖቱ
    ከቀየው ተገፍቶ የሚባረርባት ታይቶ ማንነቱ

    ይች ናት አገሬ!

    ፍትህ በአደባባይ የሚነፈግባት
    የተበዳይ ጩኸት የማይሰማባት
    ወንጀለኛ ዳኛ ሆኖ የሚያጏራባት

    ይች ናት አገሬ!

    ባልስልጣናቷ የሚያሽሞነሙኗት አድጋለች እያሉ
    በኑሮ ውድነት የሚጠበስባት ተራው ዜጋ ሁሉ
    ያለምንም እክል ከቤት ወጥቶ መግባት
    እንደ ትዓምር ነገር የሚቆጠርባት

    ይች ናት አገሬ!

    የነፃነት ቀንዲል ተብላ የተጠራች
    ለሰው ልጆች መብት በአለም ዙሪያ ሁሉ ጥብቅና የቆመች
    ቅኝ የተገዙትን ዓርነት ለማውጣት ዋጋ የከፈለች
    በዚህ በእኛ ዘመን ይህ ሁሉ ተረስቶ ሁሉም ተቀያይሮ
    በትውልድ ትስስር የታነፀ አንድነት ከውስጥ ተቦርቡሮ
    መገዳደል ሆኗል የምስኪን ዜጎቿ የእለት ከእለት ኑሮ

    ይች ናት አገሬ!

    ከልብ የማፈቅራት የእኔ ውድ አለኝታ
    ሁሌ የምመኝላት ሰላምና ደስታ
    አልጠራጠርም ይህ ማዕበል አልፎ
    እንደምታበራ ጨለማው ተገፎ

  • የመኖር ትርጉሙ (ሰኔ 2016)

    ወገኔ እንደቅጠል ሲረግፍ እያየሁ
    መታደግ ይቅርና ስላላልኩት አለሁ
    ወኔ ቢስነቴን አምርሬ ረገምኩት
    ለመኖሬ ትርጉም ፈጽሞ አጣሁለት
    እራሴን ከእንስሳ አቃተኝ መለየት

  • የለውጥ አዙሪት (ሐምሌ 2016)

    እስራት ግድያ ግፍና ጭቆና

    ህገወጥ አሰራር ጉቦና ሙስና

    የነፃነት እጦት የመብት አፈና

    ይሉኝታ ቢስነት ፍፁም ውንብድና

    በበደል ላይ በደል ተከማችቶ ሞልቶ 

    ዙሪያው ገደል ሆኖ መፍትሄ ‘ሚባል ጠፍቶ

    ህዝቡ ትግዕስቱ አልቆ ሆ ብሎ ተነስቶ

    ስርአቱን ሲጥለው ከአናቱ ጎትቶ

    ገዥዎች ከስልጣን ተገፍተው ሲለቁ

    ለአደረሱት ጥፋት በህግ ሲጠየቁ

    ሁሉም መስሎት ነበር አዲስ ቀን የመጣ

    ከእስከፊ ባርንት አርዕነት የወጣ

    በዚይ በአፍላው ዘመን ሁሉም በለውጡ ኃይል እንደተጎተተ 

    በደስታ ሰክሮ አቅሉን እንደሳተ

    ማንም ያልጠበቀው ነገር ተከሰተ

    በአዲስ መሪዎቹ የተሰጠው ተስፋ

    የዜጎችን ህይወት መለወጥ መቻሉ ሳይታይ በይፋ 

    እንደ ጉም በፍጥነት ብን ብሎ ሲጠፋ 

    ህዝቡ ስለገባው አካሄዱ ሁሉ እንደሌለው ፋይዳ

    ማድፈጡን ቀጠለ ነገሩ በሙሉ ሆኖበት ዱብ ዕዳ 

    ድምጹን ጥፍት አርጎ ለሌላ ዙር ትግል እየተሰናዳ

    እንደ ገለልትኛ ታዛቢ ግለሰብ 

    ስለሆነው ሁሉ በጥሞና ሳስብ 

    ትሻልን ሰድጄ ትብስን አመጣሁ

    ብዬ እንደ አባቶቼ እየተረትኩ አለሁ

  • ይች ናት አገሬ (ሰኔ 2016)

    ይች ናት እግሬ የማይታይባት ሰው በሰውነቱ 

    የሚፈረጅባት በዘሩ በቋንቋው ወይ በሃይማኖቱ

    ከቀየው ተገፍቶ የሚባረርባት ታይቶ ማንነቱ

    ይች ናት አገሬ!

    ፍትህ በአደባባይ የሚነፈግባት

    የተበዳይ ጩኸት የማይሰማባት

    ወንጀለኛ ዳኛ ሆኖ የሚያጏራባት

    ይች ናት አገሬ!

    ባልስልጣናቷ የሚያሽሞነሙኗት አድጋለች እያሉ 

    በኑሮ ውድነት የሚጠበስባት ተራው ዜጋ ሁሉ

    ያለምንም እክል ከቤት ወጥቶ መግባት 

    እንደ ትዓምር ነገር የሚቆጠርባት 

    ይች ናት አገሬ!

    የነፃነት ቀንዲል ተብላ የተጠራች

    ለሰው ልጆች መብት በአለም ዙሪያ ሁሉ ጥብቅና የቆመች

    ቅኝ የተገዙትን ዓርነት ለማውጣት ዋጋ የከፈለች

    በዚህ በእኛ ዘመን ይህ ሁሉ ተረስቶ ሁሉም ተቀያይሮ

    በትውልድ ትስስር የታነፀ አንድነት ከውስጥ ተቦርቡሮ

    መገዳደል ሆኗል የምስኪን ዜጎቿ የእለት ከእለት ኑሮ

    ይች ናት አገሬ!

    ከልብ የማፈቅራት የእኔ ውድ አለኝታ

    ሁሌ የምመኝላት ሰላምና ደስታ

    አልጠራጠርም ይህ ማዕበል አልፎ

    እንደምታበራ ጨለማው ተገፎ

  • የመኖር ትርጉሙ (ሰኔ 2016)

    ወገኔ እንደቅጠል ሲረግፍ እያየሁ

    መታደግ ይቅርና ስላላልኩት አለሁ

    ወኔ ቢስነቴን አምርሬ ረገምኩት

    ለመኖሬ ትርጉም ፈጽሞ አጣሁለት

    እራሴን ከእንስሳ አቃተኝ መለየት