Tag: 1983

  • ጀግናው (መጋቢት 1983)

    በአዕምሮው ያለውን ማለት የሚሻውን

    ማንንም ሳይፈራ ሲገልጽ ሃሳቡን

    አይቼ አላልፍም ሲል ግፍና በደልን

    ህይወቱን በሙሉ ሲታገል ለወገን

    ለእኛ ለፈሪዎች ድፍረቱ ለሌለን

    በቀልን በመሸሽ መናገር ላቃተን

    ልሳናችን ሆኗል አባደፋር መሥፍን

    ባለጊዜዎቹ ስልጣኑን የሙጥኝ አንለቅም የሚሉት

    በቅናት በትዕቢት ማንአለብኝነት የተተበተቡት

    ከመናገር በቀር መስማት የማያውቁት

    አርቀው ለማሰብ ፍጹም ያልታደሉት

    ለስቃይ ለውርደት ህዝብን ሲዳርጉት

    የትም አይደርስ ብለው ሲመፃደቁበት

    ከፊት ለፊታቸው በመቆም በድፍረት

    ተሳስታችኋል ብሎ የሚሟገት

    ጊዜ የማይቀይረው በአቋሙ የሚፀና

    ከቶ የት ይገኛል እንደ መሥፍን ጀግና

    መቼም ጊዜ ቢሆን የትም ይሁን የትም

    በዘመድ በጥቅም ጉዳይ የሚፈጽም

    ህዝብን የሚበድል ሆዳም የመንግሥት ሹም

    ድንገት ጸጋጠመው ዝም ብሎ አያልፈውም

    አጸሄዱን ሁሉ ጠቅላላ ድርጊቱን

    ሰው ሁሉ እንደሚያውቀው የእውነት ማንነቱንÜ

    መረዳት አለበት ብሎ ስለሚያምን

    በእሱ የተነሳ በጣም ብዙ ሰዎች መማረራቸውን

    ያለምንም ፍርሀት ይነግረዋል ሀቁን

    ከዚያም በመቀጠል ይጨምርለታል ወንድማዊ ምክሩን

    እርግፍ አርጎ እንዲተው ያን መጥፎ ድርጊቱን

    ይቅርታ እንዲጠይቅ የበደላቸውን

    እራሱን ቀይሮ አዲስ ሰው እንዲሆን

    ፈቃዱ ጸልሆነ ይህን ለመቀበል

    በፈፀመው ድርጊት ባደረሰው በደል

    ምንም ጊዜ ቢወስድ ቢያድርና ቢውል

    ከተጠያቂነት ሊያመልጥ እንደማይችል

    መልሶ መላልሶ በግልጽ ይነግረዋል

    ነገሩ ግልጽ ነው መደበቅ አይወድም

    እያየ እንዳላየ ጥፋትን አያልፍም

    በይሉኝታ መተው ከቶ አይሆንለትም

    ቆራጥነቱና ልበ ሙሉነቱ እረፍት ያሳጣቸው

    ማንንም አልፈራም የሚለው አቋሙ ያልተዋጠላቸው

    የእውነት ስብዕናውን ማወቅ ተስኗቸው

    የእነሱ ሊያደርጉት በስልጣን ደልለው

    ብዙ ሞክረዋል ከጎናቸው ቆሞ አለሁ እንዲላቸው

    ይህም አልሰምር ሲል ተገፍተው በስሜት

    በብቀላ መንፈስ ተቃጥለው በንዴት

    እስከ መጨረሻው ተስፋ ሊያስቆርጡት

    የቻሉትን ሁሉ ጫና ሲያደርጉበት

    ድርጊታቸው ሁሉ አይሰጠውም ስሜት

    እንዲያውም በአንፃሩ እልህ በመጋባት

    ምንም ሳይረበሽ በአቋሙ በመጽናት

    አላጎበድድም የፈለገው ይምጣ ብሎ በመነሳት

    ለአመነበት ጉዳይ መስዕዋት ለመክፈል

    ተዘጋጅቶ ሲቀርብ ለበለጠ ትግል

    በሁሉም አቅጣጫ ስሙን ያጠፉታል

    ያላለውን አለ ብለው ይከሱታል

    ይህን ሁሉ አድርገው ዝም አልል ሲላቸው

    ወይም አሻፈረኝ አልሰማም ብሏቸው

    ማንነታቸውን ህዝብ በደንብ እንዲያውቀው

    ድብቅ ሥራቸውን ፍርጥርጥ ሲያደርገው

    እብድ ነው ይሉታል እራሱን የማያውቅ

    ነገሮቹ ሁሉ ያሉበት ድብልቅልቅ

    ይህ አልበቃ ብሎ ከዚያም አልፈው ተርፈው

    ልብሱን ጥሎ መሄድ ብቻ ነው የቀረው

    ብለው ሲፈርጁት በቂም ተነሳስተው

    በጣም በመገረም በእኩይ ድርጊታቸው

    ያን ያሳለፈውን የፈተና ህይወት

    ወደ ኋላ ሄዶ በትዝብት ቃኝቶት

    ስለ አንጋፋው ፍጡር ስለ ሰው ማንነት

    ክርክር ቀጥሎ ከእራሱ ጋር ሙግት

    የሰው ልጅ ጭጸኔው ገደብ እንደሌለው

    ይህም እንደሆነ ዋነኛው መለያው

    ከእንስሳት ከአራዊት የሚያመሳስለው

    በጥቅሙ ሲመጡ ባለ በሌለው ኃይል

    አምሳያውን ፍጡር ሊገል እንደሚችል

    ስሜቱ ሲነዳው ማሰብ እንደሚተው

    በጥፋት ጎዳና ገፍቶ እንደሚያስገባው

    ባጸበተው ልምዱ ባሳለፈው ህይወት

    ይህ የሰው ከንቱነት ግልጽ ስለሆነለት

    የደረሰበትን የሆነውን ሁሉ በንቀት በማየት

    ስር ነቀል የሆነ መሰረታዊ ለውጥ ለአገሩ ለማምጣት

    ተስፋ ባለመቁረጥ ሲታገል ቆይቷል እስጸለ በህይወት