አይ አገሬ አበሳሽ ስንቱን ጉድ ችለሻል
ቀጣዩ ንጉሥ ነኝ የሚል እጅግ በዝቷል
እስኪታወቅ ድረስ የእውነት ንጉሡ
ጫጫታው ብዙ ነው ሁከት ትርምሱ
በምናብ እያየ በድምቀት ሲከበር ስርዓተ ንግሡ
ግዜውን ይገፋል ሁሉም ተሸክሞ ዘውዱን በየኪሱ
አይ አገሬ አበሳሽ ስንቱን ጉድ ችለሻል
ቀጣዩ ንጉሥ ነኝ የሚል እጅግ በዝቷል
እስኪታወቅ ድረስ የእውነት ንጉሡ
ጫጫታው ብዙ ነው ሁከት ትርምሱ
በምናብ እያየ በድምቀት ሲከበር ስርዓተ ንግሡ
ግዜውን ይገፋል ሁሉም ተሸክሞ ዘውዱን በየኪሱ
በዚህ በእኛ ዘመን በስልጣን ላይ ያሉት
ለአገር በማሰብ ሳይተኙ የሚያድሩት
ትውልዱ ባህሉን ረስቷል በማለት
እያስተማሩን ነው ይኸው እጅ መንሳት
የአገሬ ገበሬ ህይወቱን በሙሉ አፈሩን ሲገፋ
ያልፍልኛል በሚል ምንም ሳይቆርጥ ተስፋ
ኑሮን ለማሸንፍ ሲደክም ሲለፋ
ድንገት ከተፍ ብሎ ያ የሞት ወረፋ
ይዞት እልም ይላል ግዜ ሳያጠፋ
ንግድ ሙያ እራሱ አለው ልዩ ጥበብ
እየገዙ መሸጥ በሂደት መጨመር በገንዘብ ላይ ገንዘብ
በዚህ በኛ ዘመን የሸቀጦች ዋጋ ስለተወደደ
ፈተናው ብዙ ነው መግዛት የለመደ