እራስን ጥየቃ (ሐምሌ 2016)

የእኔ ምሁር መባል ዲግሪ መጫኔ
ምንም ካልጠቀመ ለአገር ለወገኔ

ፊድል ካልቆጠሩት ምስኪን ወገኖቼ
አርቄ ካላሰብኩ ስልጣንን ፈርቼ

በተናገርኩ ቁጥር ማን ይሆን የሰማኝ እያልኩ እንዳልቆዝም
ግራ ቀኜንና ፊትና ሁዋላየን ማማተር እንዳቆም

ሰው ሆኜ ለመኖር በቀሪው ህይወቴ
የነፃነት አየር መትንፈስ እንድችል እንደ ልጅነቴ

ልሂድ ወደ ቀዬ ወደ ዘመዶቼ
ቢያንስ ይወጣልኛል እንደልቤ አውግቼ
ምንም አልፈየድኩም እዚህ ተጎልቼ

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *